>
5:03 pm - Monday February 6, 2023

ኢትዮጵያን አትንኩ! አራት ነጥብ። (ዘመድኩን በቀለ)

ከጎንደር ክፍለ ሀገር ከሰሜን ተራሮች ፤ ከታላቁ ደብረሃሌሉያ ከቅዱስ ያሬድ ገዳም የተነሳው ስውርና ምስጢራዊ ነፋስ ዓለምን እያስጨነቀና እያወደመ ነው ። ይኽ በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ድግስ ለሚደግሱ በምድራችን ላይ ለሚገኙ ሀገራት ሁሉ ከእግዚአብሔር የተላከ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ። አሁንም እደግመዋለሁ ኢትዮጵያን አትንኩ ። አራት ነጥብ ።

ዛሬ ትንሽ ደፈር ብለን ለመነጋገር እንሞክራለን ። በዛሬው ጽሑፌ የትግራይ ወንድሞቼን በግልጽ የምነቅፍባቸው ነገር እንዳለኝ ያለ ሐሰት በእውነት ምንም አይነት የመቀባባት ፣ የመለማመጥ ፣ የመሸፋፈንና የዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳልጠቀም እቅጩን እነግራቸውና የመሸበት አድራለሁ ። ለዚህ አሁን ላለውና የኤርትራዊ ደም ኖሮአቸው ሃገሪቷን ግጠው ግጠው በቁሟ በአጥንቷ እያስቀሩዋት ለሚገኙ መሪዎችም መልእክት ቢጤም እንደ አቅሚቲ ለማስተላለፍ ሞክሬያለሁ ። በየገዳሙ የሚገኙ መንፈሳውያን አባቶች ለእነዚሁ ጉዶች ቢነግሯቸውም አልሰማ ብለዋል ። በእረኛ የሚመሰሉ አዝማሪዎችም ደፈር ብለው መናገርም ጀምረዋል። በተለይ ወጣት ሙዚቀኞች የሌለ ድፍረት አምጥተው ታይተዋል ። ለምሳሌ ጌትሽ ማሞ የተባለ አዝማሪ ከሰሞኑ ያወጣውን ሙዚቃ በሰዎች ጠቋሚነት ደጋግሜ ለመስማት ሞክሬ ተደምሜበታለሁ ።

ርዕሱ እንከባበር ይላል !!!

“አንቺን ተመርኩዘው፣ ጊዜን ቢታደሉ፣
አለቃ ሆኑብኝ ፣ዘመዶችሽ ሁሉ።
አንች ምናለብሽ በእኔ ቤት ሆነሽ፣
አንች ምናለብሽ፣በእኛ ቤት ሆነሽ፣
ዳንቴል ትሠሪያለሽ፣ለዚያኛው ቤትሽ።
በልቶት ለሚጠፋው፣ ሥራ’ት ተሰማርቶ፣
ሢኖር ዐይቻለሁ፣ሰው ለሆዱ ሞቶ።”

ይላል የአዝማሪው ስንኝ ። ሟቹ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ደብረ ብርሃን ላይ ” የዐማራ ህዝብ ያስቀመጠውን ጠመንጃ መቼ ማንሳት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል ” ያሏት ንግግር ሳትገባቸው ቀርታ ገዢዎቻችን ፕሮፌሰሩ ይኽን ንግግር ከተናገሩ ከ3 ወር በኋላ አሃ ሰውየው ለካ ደብረ ብርሃን ላይ ጦርነት ነው እኮ ያወጀብን በማለት ለንግግራቸው ትርጉም በመስጠት ፍዳቸውን አብልተው በቁማቸው እንዲማቅቁ አድርገው መግደላቸው ይታወቃል ።

አሁንም በዚህ ጌትሽ በተባለ አዝማሪ ላይ የህውሓት በቀቀን ከሆኑት መካከል የአውራአምባው ጋዜጠኛ የነበረው የአድዋው ተወላጅ ዳዊት ከበደ ከቴዲ አፍሮ በኋላ የሚጮኽበት ሰው አግኝቶ እሪሪ በማለት ልጁ ላይ እርምጃ ይወሰድበት እንጂ በማለት በግልጽ ለህወሓት ጥሪ ማቅረብ ጀምሯል ። በቃ እኔ ይሄን ይሄን ሳይ ህዝብ እየተናገረ መሆኑ ነው የሚገባኝ ። ሞት እስር አለ እየተባለ እሱን ሳይፈራ የመጣው ይምጣ አስር ሞት የለ ማለት የጀመረን ህዝብ ደግሞ መመለሻው ከባድ ነው ። ወዳጄ የግፍ ጽዋው የሞላ ዕለት መመለሻው ከባድ ነው የሚሆነው ። እናም በድጋሚ የትግራዋይ አባቶች ደፍራችሁ በነገሩ ግቡበትና እነዚህን በሟች ልጆቻችሁ ስም እየነገዱ ትግራዋይን ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጋር ለማለያየት የሚሠሩ ክፉዎችን አደብ አስጉዙልን ። እኔ ዘመዴ ተናግሬያለሁ ። እመ አምላክ ምስክሬ ናት ተናግሬአለሁ ።

እጅግ አድርጎ ከናቡከደነጾር ይበልጥ በከፋ መልኩ የሚጨቁነንን መንግሥት ፣ ሀገሪቷን እንደ ገና ዳቦ የሚሸነሽናትን መንግሥት ተብዬ ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ ከፋፍሎ ፣ ከፋፍሎ እርስ በርስ የሚያባላንን መንግሥት ፣ አንድነት የሚባል ነገር ሙልጭ ብሎ ከምድሪቱ እንዲጠፋ ሌት ተቀን የሚሠራ መንግሥት ፣ ከእኛው ከኢትዮጵያውያን መሃል መርጠው ፣ አደራጅተው ፣ ዘረኝነትን ፣ መከፋፈልን ፣ መበታተንን ፣ የእርስ በእርስ ግጭትን ፣ ዘረፋን ፣ ጭካኔን ፣ በመንግሥት ደረጃ [ ሐሰት መናገርን ] አሰልጥነው ፣ አለማምደው ገንዘብ በገፍ ሰጥተው ፣ መሣሪያ እንደጉድ እስከ አፍንጫው ድረስ አስታጥቀው ጥቂት ትምህርት ጠል የባንዳ ልጆችን ከደደቢት በረሃ እስከ ምኒሊክ ቤተመንግሥት መርተው የሥልጣን ዙፋን ላይ አውጥተው ያቺን መንፈሳዊት ሃገር አርክሰው አቆሽሸው የማንም ጋጠወጥ መፈንጫ እንድትሆን አድርገው በዓለም ህዝብ ዘንድ መሳቂያ መሳለቂያ እንድንሆን ያደረጉን ሃያላን ሀገሮች ናቸው ።

እኛ ኢትዮጵያውያን በንግሥት ሳባ ጊዜ የሚገርም የጦር ሠራዊት የነበረን ነበርን ። በአጼ ካሌብ ዘመን ተመሥርቶ ከአንደ ሺህ አምስት መቶ ዓመት ቆይታ በኋላ የፈረሰ ምርጥ የባሕር ኃይል ነበረን ። የአየር ኃይላችን በአሁኑ ሥርዓት ፍርክስክሱ እንዲወጣ ከመደረጉ በፊት ዓለም የሚደመምበት እንደነበርም ታሪክ ምስክር ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ቀን ከሌሊት ይኽን ነቀርሳ የሆነ መንግሥት በጸባይም በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ፣ በቁጣም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ፣ በምርጫም ካርዱን በመተቀም እንደመዥገር ከላዩ ላይ ተጣብቆ በአጥንቱ እስኪቀር ድረስ የሚመጠምጠውን ደም መጣጭ የወመኔዎች ስብስብ ፣ ጭራሽ ሰብአዊነት ያልፈጠረባቸውንና ኢትዮጵያዊ ማንነት የሌላቸውን የጥቁር ጨካኝ ቅኝ ገዢዎቻችንን በተለያየ መንገድ ከላዩ ላይ ለማውረድ በብዙ ደክሟል ።

እነዚህ ገዢዎቻችን ብልጭልጭና ምድራዊ ነገር ብቻ የሚያጓጓቸው እንደሆነ ኃያላኑ መንግሥታት በሚገባ አውቀዋቸዋል ። እናም ለዚህ ነው ዛሬ ገዢዎቻችን ሁሉንም ነገር ወደ ትግራይ ፣ ሁሉንም ነገር ቅድሚያ ለትግራዋይ በሚል ፍልስፍና ተለክፈው የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለየ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ለመጥቀም ሲጥሩ የምናየው ።

ትግራይ ህዝቡ በሥራ አጥነት እንዳይቸገር እጅግ ግዙፍ የሆኑ ፋብሪካዎች ተከፍተውለታል ። በጋምቤላ ለም መሬቱ በሙሉ በትግራይ ልጆች ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል ። እንዲያውም ሰሞኑን ባየሁት አንድ የኢቲቪ ቪዲዮ ዜና ላይ ትግራዋይ በጋምቤላ መንግሥት ፓርላማው ውስጥ ገብተው ” በክልላችን ” እያሉ ጥያቄ ሲያቀርቡ ታይተዋል ።

አሁን መንግሥታዊ ስልጣኑ ኤርትራዊ ደም ባላቸው በትግርኛ ተናጋሪ ሰዎች እጅ ነው ። ገንዘቡ በሙሉ በእነዚህ ሰዎች እጅ ነው ። የመከላከያ ጦር አዛዥነት እስከ ተራ ጦር መሪነት ድረስ ያለው ስልጣን በእነዚሁ ሰዎች እጅ ነው ። አየር መንገድ ፣ ቴሌ ፣ ባንክ ፣ የመሳሰሉ መሥሪያ ቤቶች ቢኬድ ከዘበኛ ፣ ተላላኪና ጽዳት ሠራተኛ እስከ ከፍተኛ አመራር ድረስ ያሉት እነዚሁ ወገኖች ናቸው ። ቤተ ክህነት ከዘበኛ እስከ ፓትሪያክነት ድረስ የተያዘው በእነዚሁ ወገኖች አማካኝነት ነው። የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳደር ፣ ከዘበኛ ጽዳትና ተላላኪ ድረስ የተያዘው በእነዚሁ ሰዎች አማካኝነት ነው ።

ገንዘብ በቃኝ የማይሉ አዲስ ፍጥረቶች ፣ ነባሩንና ያን የጥንቱን ሃይማኖተኛ የትግራይ ህዝብ የማይወክሉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆነ ይሉኝታ ያልፈጠረበት አዲስና ራስ ወዳድ ጠባብ ጎጠኛ የሆነ ጉደኛ ትውልድ ፈጥረው ነበሩን የመርካቶ ነጋዴ በጠረባ ጠርበው በጀርባው አንጋለው ከጫወታ ውጪ አድርገውታል ። ዛሬ ቀድሞ በመርካቶ በንግድ ሥራ ይታወቁ የነበሩ ማኅበረሰቦች ለማኝ የኔ ቢጤ ሆነዋል ። ግማሹ ጨርቁን ጥሎ አብዷል ። ይሄ እውነት ነው ።

ዛሬ ዛሬ በሰፈር ውስጥ ከሚገኝ ዕድር ጀምሮ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል በማኅበራዊም ሆነ በመንፈሳዊ ፣ በኢኮነሚው ውስጥ ሰብሰብ ብሎ ለመደራጀት የመሪነት ሥፍራውን አንድ የትግርኛ ቋንቋ የሚናገር ሰው በመሃል ከሌለ ውኃ ይበላሃል እንጂ ጉዳይህን የሚፈጽምልህ አካል አታገኝም ።

የእድር ዳኛ ፣ የእቁብ ፀሐፊና ሰብሳቢ ፣ የሙያ ማኅበራት ውስጥ የሚገኙ ፣ በአትሌቲክሱ ፣ በእግር ኳሱ ፣ በሚዲያው ፣ ንግዱ ማኅበረሰብ ፣ በአክስዬን ማኅበራት እና በተለያዩ ከሁለት በላይ ሰዎችን የሚሰበስብ ማንኛውም ጉዳይ ውስጥ ” እንደ ቡዳ መድኃኒት ” የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሌለበት ዋጋ አይኖረውም ።

እናም ኃያላኑ ሀገራት ሆን ብለው ይኽን አድርገዋል ። በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ቢደረግ ፣ የሚያሳዝን የረሃብ አድማ ቢጠራ ፣ የኃያላኑ ሀገራት መሪዎች የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ብሶት ለመስማት ጊዜም ሆነ ፍላጎት የላቸውም። ያስቀመጡት መንግሥት የፈለገውን ያህል የሰብአዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ቢፈጽም ፣ ቢገድል ፣ ቢያስር ፣ እነሱ እቴ ጉዳያቸውም አይደለም ። አይተው እንዳላየ ፣ ሰምተው እንዳልሰማ ዝም ። ጭጭ ፣ ጮጋ ብለው ነው የሚያልፉት ።

ይኼ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ፣ ሀገሪቱን በገፍ ለቆ በስደት ምድሪቱን እያጣበበ እያዩ ፣ በሲና በረሃ ውኃጥም ሲረፈርፈው ፣ ጊንጥና እባብ ሲነድፈው ፣ ዋባ ስትጨርሰው ፣ ዘንዶ ሲውጠው ፣ የሜዲትራንያንና የቀይ ባህሮች ሲያሰጥሙት ፣ አሳነባሪ ሲሰለቅጠው ። በሲና በረሃ በቁሙ ያለማደንዘዣ የሰውነት የውስጥ ክፍሎቹ ተቀርድደው ለሽያች ሲቀርቡ ፣ የኬንያ ፖሊስ ሲዘርፈው ፣ የታንዛኒያና የሞዛምቢክ ገበሬ ሲቀጠቅጠው ። በደቡብ አፍሪካ በቁሙ በእሳት ሲቃጠል ፣ በቆንጨራ ሲቆራረጥ ፣ በየ አረብ ሃገራቱ ከፎቅ ሲወረወር ፣ በፈላ ውኃ ሲገሸለጥ ፣ የማንም ዘላን የግመል ጭራ ተከታይ የነበረና ከድንኳን ኑሮ ወጥቶ ዛሬ ሀብታም ሲሆን አንቱታን ያተረፈ አረብ ገረድ ሲሆን ፣ በነዚሁ ሰሞነኛ ጌቶች ሴቶቻችን ሲደፈሩ ፣ ወንዶቹ በሰይፍ አንገታቸው ሲቀነጠስ ። በጣሊያን ሮም ፣ በሆላንድ አመስተርዳም በበረዶ ውስጥ ያለመጠለያ ደጅ ላይ ወድቆ ውሎ ሲያድር እያዩ የስደቱን መነሻ ምክንያትም እያወቁ ያንን ለማስተካከል ፈቃደኞች አይደሉም ። ይበሏቸው ጎሽ ብለው ኤርትራዊ ደም ያላቸውን ከበረሃ ድረስ የጥላቻ ፣ የመከፋፈልና ፣ በቃኝ የማያውቁ የዘረፋ ጎተራ የሆኑ የትግርኛ ተናጋሪ ገዢዎቻችንን አበጃችሁ በሏቸው ፣ አሳራቸውን አሳዩዋቸው እያሉ በገንዘብ ይደግፋሉ ፣ እንደ እንቁላል ወድቀው ይሰበሩ ይመስል ይንከባከቡዋቸዋል ።

አሁን እነዚህ ኃይላት ህወሓትን ከፀሐይ በታች የሚያስፈራው ኃይል የሌለ እንዲመስለው ስላደረጉትና አይዞህ ስላሉት የሚያደርግ የሚሠራውን አሳጥቶታል ። ዶክተር መራራ ጉዲናን ሲያስር እንዲሁ ዝም ብሎ አይደለም ። ምናልባትም ከምእራባውያኑ የማርያም መንገድ ስላገኘም ይሆናል ። ዶክተሩ ራሳቸው አውሮፓውያኑ በጠሩት ጉባኤ ላይ እንዲገኝ ካደረጉት በኋላ ነው በዚያ በመገኘቱ አሳበው ቂሊንጦ ያወረዱት ። ተመልከቱ ዶክተር መረራን የጠሩት አውሮፓውያን ሆነው ዶክተር መረራ ሲታሰር የፈለጉትን መንገድ ተጠቅመው ማስፈታት የሚችሉ ቢሆንም ነገር ግን የህወሓት መንግሥት ጥርስ ያለው አንበሳና ማንም በማንም የማይመራና የማይደፈር ፣ የማይታዘዝነ የማይሞከር መንግሥት ነው የሚል ቅርጽን ለመስጠት ሲሉ አፍአዊ መግለጫን በማውጣት ብቻ የሌለ ጆተኒ ይጫወታሉ ። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የመን ድረስ ሄደው እንዲይዟቸው ማን የማርያም መንገድ የሰጠ ይመስለናል.? እነሱ እኮ ናቸው ። እነሱ ምእራባውያኑ ።

ታዲያ ይሄን ሁሉ ግፍ እግዚአብሔር አየ ። ተመለከተም ። በምድር ላይ ያለችዋ የእግዚአብሔር ሐገር ኢትዮጵያ በቤተመንግሥቷም ሆነ በቤተክህነቷ ርኩሰት ቆሞ ታየ ። ኢትዮጵያ በቀድሞ ዘመን ልክ እንደ ዛሬዋ አሜሪካን ልዕለ ኃያል ሀገር ነበረች ። ባህር ተሻግራ በጦር ኃይሏ የተጨቆኑ ህዝቦችን ነፃ የምታወጣ ሀገር ነበረች ። አጼ ካሌብ ይመስክሩ ። አሁን ግን ሽባ ሆነች ። የዓለም ህዝብ ጭራ ሆነች ። የጦር ሠራዊቷ የኦሮሞ ህዝብን የሚገድል ፣ የዐማራ ህዝብን የሚጨፈጭፍ ፣ የኮንሶን ህዝብ የጋምቤላን የሚወግር የሚገድል ፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያውያንን የሚያቃጥል ። ሺዎችን በየ ካምፑ የሚያስር የቀኝ ገዢ ሠራዊት ሆነ ።

እውነት ለመናገር በአሁኑ ወቅት ረሃብ የማይሰማባት ፣ ልጆቿ የማይገደሉባት ፣ የማይታሰሩባት ፣ ነጋዴዎቿ ግብር በዛብን የማይሉባት ፣ ተማሪዎቿ በስትሬት ኤ በ 4 ነጥብ የሚያልፉባት ፣ ደስታ ፣ ፈንጠዝያ ፣ ጭፈራ ፣ አስረሽ ምቺው የበዛባት ፣ ችግር ያልነካቸው ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ወርቅ በወርቅ የሆኑባት ፣ ዘፋኝ በሰረገላ የሚከበርባት ፣ አንድ ነጠላ ካሴቱም በ50 ሺ ብር የሚሸጥባት ፣ ፎቅ እንደችግኝ ተክለው በጥላውና በፍሬው ዓለሙን የሚቀጩባት የምድራችን ላይ ያለች ልዩ ደሴት ብትኖር የትግራዋይ ምድር ብቻ ናት ። ” ውኃ ጠማን ከማለት ውጪ ልክ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ተቸገርን ሲሉ የማይደመጡ ዜጎች ቢኖሩ ትግራዋይ ብቻ ናቸው ። አራት ነጥብ ።

ዛሬ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ስለኢትዮጵያ የሚጽፍ ፣ የሚሰብክ ፣ የሚዘምር ፣ የሚዘፍን ፣ ቅኔ የሚደረድር ፣ ግጥም የሚገጥም ፣ በኢትዮጵያዊነት ስም የሚደራጅ ፣ የሚሰበሰብ ፣ ጽዋ የሚጠጣ ፣ ማኅበር የሚመሰርት ደማቸው በሚፈላ የህወሓት ባለስልጣናት ይቀሰፋል ።

ለዚህ ነገር ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን አርቲስት ቴዲ አፍሮ ነው። ቴዲ እንዲህ መከራውን የሚበላው ለምን ይመስልሃል.? ማሬ ፣ ማሬ ፣እያለ ቢዘፍን ፣ ሽንጥና ዳሌሽ ፣ እንዲያው ከፍ ፣ እንዲያው ዝቅ እያለ ቢያንጎራጉር ኖሮ ማን የሚነካው ዞርም ብሎ የሚያየው ያለ ይመስልሃል? እውነቴን ነው ማንም አይነካውም ። ዞርም ብሎ አያየውም ነበር ። ለዚህ ምስክሩ ሌሎቹን የዝሙት ማስታወቂያ የርኩሰት ስፖንሰር የመዳራት ፈረስ የሆኑትን አዝማሪዎች ያላቸውን ነፃነት ማየት ትችላላችሁ ። ልጁ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ አቀንቃኝ ፣ የኢትዮጵያዊነት ምስጢር ተንታኝ ፣ በህዝቡም ላይ የተደረገውን አዚም ያነሳ ፣ መከፋፈልን ያወገዘ ፣ ዘረኝነትን ህዝቡ እዲጠየፍ ያደረገ ፣ ኢትዮጵያችንንም ዳግም ብቻውን ከጨረቃ በላይ የሰቀለ ጀግና ስለሆነ እኮ ነው እንዲህ ደማቸው ፈልቶ የሚይዙት የሚጨብጡትን አሳጥቶ የሚንበጨበጩት ። ኦሮሞና ዐማራ በምን ተአምር ሊስማማ ይችላል ። በፍጹም እሳትና ጭድ ካደረግናቸው በኋላ ወደ አደባባይ ወጥተው አንድ ነን ደምህ ደሜ ነው ካሉ እንደ ኢህአዴግ በደንብ አልሠራንም ማለት ነው ብለው በአደባባይ ሚድያ ላይ ቀርበው የሚፎክሩት የህወሓት ሰዎች ቴዲን ሊታገሱ ይመስላችኋልን.!?

ሲመስለኝና ስጠረጥር ህወሓት ቴዎድሮስ ካሳሁን [ ቴዲ አፍሮ ] በኢትዮጵያ የቅዱሳን አበው ትንቢት መሰረት ፤ ከምሥራቅ ቴዎድሮስ የሚባል ንጉሥ ይመጣል ፣ ህዝቡንም ያለ ጦር መሳሪያ በፍቅር በአንድነት ይገዛል ።” የሚለውን ትንቢት ሰምተው ፤ ያ የተባለው ሰውም ይሄ አዝማሪ ይሆን እንዴ ብለው ይመስለኛል እንዲህ መከራቸውን የሚበሉት ። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ ቴዲ አፍሮ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ቦርድ ሳያውቀው ፣ የዓለም መንግሥታት ዕውቅና ያልሰጡት ፣ የኢትዮጵያውያን ንጉሠ ነገሥት ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ያውም ቤተመንግሥቱን በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ የሠራ ንጉሥ ነው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ። እናም ቴዲ ገና በህወሓት በደንብ ይቀጠቀጣታል ። ምክንያቱም ቴዲ ራሱን የቻለ ሀገርም ሆኗልና ። [ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ [ቴዲ አፍሮ ] ሀገር ] ። ለህወሓት የህዝብ ፍቅር ያለው ግለሰብ ሰውም ሆነ ሀገር ለእሷ ቁጥር አንድ ጠላቷ ነው ። የራሷን መሪዎች እንኳን በተለየ መልኩ መውደዱን ከገለፀ ቀርጥፋ ነው የምትበላቸው ። አርከበ ትዝ አይላችሁም ። ቢልቦርዱን በአንድ ሌሊት ድምጥማጡን ሲያጠፉት ።

በትግራይ አቶ አሰገደ ገብረሥላሴን ብቻ እያየሁ እኔ በበኩሌ የትግራይ ህዝብ ስርዓቱን እየተቃወመ ነው ብዬ ራሴን ለመሸወድ አልፈልግም ። እንዲየው የፈለጋችሁትን በሉኝ ። የፈለጋችሁትንም ስም ስጡኝ እናንተ የስርዓቱ ቁጥር 1 ተጠቃሚ ስለሆናችሁ ነው የሌላው ኢትዮጵያዊ ሞት ፣ እንግልት ፣ ስደት ፣ መራብና መጠማት ፣ የማያስጨንቃችሁ። በሌላው የኢትዮጵያ ክልል ያለማንም ከልካይ ሃብት እያፈራችሁ ፣ እያረሳችሁ ፣ እየነገዳችሁ በምቾትና በድሎት ስትኖሩ እንዴት አንዲት የአጋርነት ድምጽ ለሌላው ወንድማችሁ ማውጣት ፣ መተንፈስ ያቅታችኋል.? በህወሓት አማካኝነት እስከ አፍንጫው የታጠቀው ሱማሌ ልዩ ኃይል ምስኪን የኦሮሞን እናት በስናይፐር አናቷን ብሎ ሲደፋት እንዴት ነው እንደማያገባችሁ ሆናችሁ ተዘፍዝፋችሁ ጆሮአችሁን በጥጥ ወትፋችሁ ቁጭ ያላችሁት ።

የሱዳን ገበሬ ወታደር የጎንደር ዐማራን በጠራራ ፀሐይ ሲረሽን እንዴት ነው ይሄ ነገር ብላችሁ ያላላችሁት.? ጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ዘላኖች ሲጨፈጨፍ እናንተ ከጋምቤላ ምድር ወርቅ እየዛቃችሁ እንዴት ነው ድምጻችሁን የማታሰሙት ። ለምንድነው ዝም ጭጭ ማለትን የመረጣችሁት.? እኮ ለምንድነው.? ሻአቢያ ወረረን ባላችሁ ጊዜ ኦሮሞው ዘሎ መጥቶ ሞታችሁን ሞተላችሁ ፣ እንደ አባት ገዳይ የምትቆጥሩት ዐማራው ግር ብሎ መጥቶ እንደ ቅጠል ረገፈላችሁ ። ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ሸአቢያን ጨርግዶ ይረፈርፉ የነበረው የጋምቤላ ተወላጆች ነበሩ ። ጉራጌው ፣ ኮንሶው አንዳቸውም አልቀሩም ነበር ። እናም ያ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሲሞትላችሁ ዛሬ ምነው ዝም ማለታችሁ ። ሄይ ሄይ ደፈር ብለን እንወቃቀስ እንጂ ፣ አዎ ደፈር እንበል.!

በባድመ ጦር ግምባር ተካፍለው የተዋደቁ ብሔር ብሔረሰቦች በሙሉ አሁን በተራቸው ኤርትራዊ ደም ባላቸው በህወሓት ገዢዎቻችን አማካኝነት እየተጨፈጨፉና የተጋድሎአቸውን ሽልማት እያገኙ ይገኛሉ ። እውነታው ይሄው ነው ። አሁን ሻአቢያ ወረረን ትሉ ይሆናል ። ዛሬ የናቃችሁት ህዝብ በደሉን ሲናገር ዝም ያላችሁት ህዝብ ነገ ፊት እንዳይነሳችሁ እሰጋለሁ ። ምራቅ የዋጣችሁ የትግራይ ሽማግሌዎች ካላችሁ አሁኑኑ ከሐዲዱ እየወጣ የሚገኘውን ባቡር ፍሬኑን ያዝ አድርጋችሁ በደም ኤርትራዊ ሆነው ኢትዮጵያውያንን ከትግራይ ወንድሞቹ ጋር ደም እያቃቡ የሚገኙትን ተንከሲሶች ሃይ ልትሉ ይገባል ። ገና ለገና እናንተን ይከፋችኋል ተብሎ ተበልተን እስክናልቅ መጠበቅ የለበትም ባይ ነኝ ።

በየሥጋ ቤቱ ቁርጥ የሚበሉትን ፣ በየግሮሰሪው ዘግተው የሚጠጡት በሙሉ እነማን ናቸው እንዴ.? በቴሌቭዥን ቀርቦ የሚያስፈራራው ፣ ፖሊስ አዛዡ ፣ ዓቃቤ ህጉ ፣ የማዕከላዊ መርማሪው ፣ ዳኛው ፣ የወኅኒ ቤት ኃላፊው ማነው እንዴ.? እናም ምእራባውያኑ ተሳክቶላቸዋል ። እንደ ይሁዳ ኢትዮጵያዊ ማንነትን በብር የሸጡ በደም ኤርትራዊ በዜግነት ኢትዮጵያዊ በሆኑ ጥቂት የትግራዋይ ልጆች አማካኝነት መላው ኢትዮጵያዊ ፍዳውን እያየ ይገኛል ።

ከጉምሩክ ፍልቅልቅ እያለ የሚወጣ ነጋዴ ከያችሁ እሱ ትግርኛ ቋንቋ ይችላል ማለት ነው ። ከሃገር ውስጥ ገቢ እየፈነደቀ የሚወጣ ነጋዴ ካያችሁ እሱ ያለ ጥርጥር ትግራዋይ ነው ። ፈንክቶም ይሁን ተፈንክቶ ፣ ጠልቶም ይሁን ተጣልቶ ፣ ከሶም ይሁን ተከሶ እየፈነደቀ ከፖሊስ ጣቢያ የሚወጣ ሰው ካያችሁ በእርግጠኝነት ያ ሰው የዘመኑ ሰው ነው ። የቀበሌ ሊቀመንበር ፣ የዕድር ዳኛ ፣ የማኅበራት ፕሬዝዳንት ፣ የዕቁብ ፀሐፊ ፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ አለቅነት የትግራዋይ ካልሆነ ያልቅልሃል ።

ይኽ ሁሉ ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ እየታየ እና እየተፈጸመ የህወሓት የእንጀራ አባት ዋናዋ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጨከነች ። ሰቆቃ ዋይታውን እያየች ባላየ ባልሰማ የራሳችሁ ጉዳይ አለች ። ህወሓትን ብቻ አትንኩብኝ እንጂ ለምን እንደፈለጋችሁ አትሆኑም አለች ። አውሮፓም ዝም ጭጭ አለች ። መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ። ፊትን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ። ወደ እሱ ወደ ሰራዊት ጌታ መጮኽ ። መፍትሄው ከእሱ ዘንድ ብቻ እንደሆነ ማመን እና በንስሀ ተመልሶ ወደ እርሱ መጮኽ ነበር ።

አዎ ዋልድባን አቶ መለስ ዜናዊ ሲያሳርሱት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስም ዝም ሲሉ ፣ የዋልድባን መነኮሳት ደፋሩ የህወሓት ሰራዊት ሲቀጠቅጥ ፣ ሲገድልና ሲያስር እግዚአብሔር ተነሳ ፣ ሁለቱንም ባለሥልጣናት በአንድ ሳምንት ውስጥ በሞት ጠራቸው ።

አሁንም ትዕቢት በኢትዮጵያ ምድር እስከ ጨረቃ ደርሷል ። ቤተክርስቲያን ማፍረስ ለህወሓት ተራ ነገር ሆኗል ። በከንቲባ ጫልቱ አማካኝነት የፈረሰው የቅዱስ ዮሐንስ ታቦት እንደ ተራ ነገር ተቆጥሮ እስከአሁን ድረስ በቆሻሻ መጣያ ኮንቴይነር ውስጥ ወድቋል ። እናም እግዚአብሔር ያያል ። ይመለከታልም ። ከዚያ ፍርዱን ይሰጣል ።

አሜሪካ በአሁኑ ወቅት የሚያሰጋትና ያወድመኛል ብላ በተጠንቀቅ ቆማ እየጠበቀች የሚገኘው ከሰሜን ኮሪያ የሚተኮስ የኒዩክለር ቦንብ ተሸካሚ ሚሳኤል ነው ። አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሉን ብትተኩስ እንኳ በአየር ላይ እንዳለ የሚያከሽፍ ፀረ ሚሳኤል ሚሳኤልም አላት ። እናም የጦር ሠራዊቷ ዝግጁ ነው ። ጦርነቱ ቢጀመርም በሰው ሰውኛ እንዳይሸነፍ ያውቃል ። አይሸነፍምም ። የአሜሪካ መከላከያ ኃይላት በሙሉ ፊታቸውን ወደ ሰሜን ኮሪያ አዙረው ነው በተጠንቀቅ የቆሙት ። በተጠንቀቅ ።

ነገር ግን አሜሪካውያኑ ያልጠበቁት ጦር ከወደ ሌላ አቅጣጫ መጣባቸው ። ይኽ ጦር አይታይም ፣ አይጨበጥም ፣ አይዳሰስም ። ሲያወድም ሲያጠፋ እንጂ ፣ ሲገሰግስ ሲመጣ እንጂ ፣ ሲተኮስ አይታይም ። ፀረ ብሎ ነገር የሚያቆመው ምድራዊ መሳሪያ በምድር ላይ የሰው ልጆች ሊሠሩና በዚያም ሊያቆሙት የማይችሉት ረቂቅ መሣሪያ የታጠቀ ሠራዊት ። እውነታው ይኸው ነው ።

ዛሬ አሜሪካ በከባድ አውሎ ንፋስ እየተመታች ነው ። የዚህ አውሎ ነፋስ መጠሪያ ስሙም ሄሪኬን ኢማ የሚል መጠሪያ ሰጥተውታል ። የአውሎ ነፋሱ መነሻ ሥፍራም ኢትዮጵያ ያውም የሰሜን ተራሮች መሆኑኑን ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ዘግበውታል ። እየዘገቡም ይገኛሉ ። [ Ethiopa is the the birthplace of hurricane Irma] በማለትም እቅጩን በመናገር ላይ ናቸው ።

የሰሜን ተራሮች ኢትዮጵያ ውስጥ በሰሜን ጎንደር ግዛት ውስጥ የሚገኙ ተራሮች ያሉበት ሥፍራ ነው ። የእነዚህ ተራሮች አባታቸው ደግሞ ራስደጀን ተብሎ ይጠራል ። ህወሓት ይህን ተራራ ወደ ትግራይ ክልል ወስዶት በቅርቡ ነው በስንት ጩኸት ይቅርታ በስህተት ነው የወሰድኩት ብሎ የመለሰው ። ሆኖም ግን በአፉ እንዲያ ይበል እንጂ በተግባር ግን አሁንም የሰሜን ተራሮች በትግራይ ክልል ውስጥ እንደሆኑ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት ። ይኽን ለማረጋገጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የደባርቅ ከተማን ወጣ እንዳለ የጂፒኤስ መሳሪያ ቢከፍት ፣ እንኳን ወደ ትግራይ ክልል መጡ ፣ አሁን የትግራይ ክልል ደርሰዋል ብሎ ያረዳችኋል ። እናም ራስ ደጀን አሁንም የትግራይ ግዛት እንደሆነ ነው የሚገኘው ።

ራስ ደጀን ታላቁ የኢትዮጵያ የዜማ ሊቅ ሊቁ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ተራራ ነው ። በገዳሙ እስከ አሁን ድምጻቸው ብቻ የሚሰማ ቅዱሳን የሞሉበት ሥፍራ ነው ። እስከአሁንም የስውራኑ የመኅሌት ዜማ ይሰማበታል ። የህውሓት መንግሥት ዋልያዎች ቁጥራቸው እየቀነሰ ስለሆነ የቅዱስ ያሬድ ገዳም ከዚያ አካባቢ እንዲነሳ በማለት እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ህዝቡ ግን በዋልያ ምክንያት አንዲት ስንዝር የጻድቁ መሬት የሚነሳ ከሆነ እኛ ዋልያዎቹን በጥይት እንጨርሳቸውና እንገላግላችኋለን በማለታቸው ምክንያት ነው ጉዳዩ ፋይሉ ባይዘጋም እንዲረጋጋ የተደረገው ። በዚህ ኮሚቴ ውስጥ እኔ ራሴ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ሆኜ ጉዳዩን በቅርበት ስለማውቀው ነው የምነግራችሁ ። እናም አሜሪካንን አሁን እያወደማት ያለው ከኒውክለር ቦምብ የበለጠ አውዳሚ የሆነው የጦር መሳሪያ መነሻው ከዚህ ተራራ ነው ብለዋል ራሳቸው አሜሪካውያኑ ።

ቅዱስ ያሬድ ደግሞ በዘመናችን በገዛ ወገኖቹ እንዲናቅ ፣ ሰማያዊ ድርሰቱና ዜማው እንዲጠላ ፣ በዘፈንና በዳንኪራ እንዲተካ በምእራባውያኑ ቅጥረኞች ሰፊ በጀት ተይዞ ዘመቻ የተከፈተበት ጻድቅ ነው ። በቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ በሬጌና ራጋ ፣በቡጊቡጊም መጨፈር ከተጀመረ 25 ዓመት አለፈን ። ዘርፌ በሏት ፣ ትዝታው በሉት ፣ ምርትነሽ በሏት ብቻ ለዚህ ጥፋት ተመልምለው የተላኩ የቅዱስ ያሬድ ደመኞች ናቸው ። ስሙ ሲጠራ ደርሶ ያንቀጠቅጣቸዋል ።

ትናንት ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር እንዳልተባለች ዛሬ የማንም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ወሮበላ አደገኛ ቦዘኔ የምእራባውያን ሃይማኖት ቅጥረኛ ወጣቶች ተጥለቅልቃለች ። የነብያት ስም በኢትዮጵያ መጫወቻና መቀለጃ ሆኗል ። ክርስትና መሳቂያ መሳለቂያ ሆኗል ። ጠንቋዩ አባባ ታምራትን የሚያስንቁ የቁጩ ጠንቋዮች የቴሌቭዥን የአየር ሰዓት ተሰጥቷቸው ምድሪቷ እንድትረክስ ክርስትና በህዝቡ ዘንድ እንዲጠላና እንዲናቅ በረቂቅ ዘዴ እየተሠራ ነው ።

የሴት ነብያት ፣ አሁን ደግሞ የህጻናት ነቢያት የተባሉ ጉዶች ሱፍና ከረባት አድርገው 24 ሰዓት ህዝቡን እንዲያደነዝዙ እየተደረገ ነው ። የመንግሥት ባለሥልጣናት ፣ የፓርላማ አባላት ፣ ነጋዴዎችና ታዋቂ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የፕሮቴስታንት እምነት እንዲቀበሉ እየተደረገ ነው ። በተለይ የደቡብ ህዝብ የሽንት ጨርቃቸውን አስጥተው በመጡ ጨቅላ ህጻናት አማካኝነት መጫወቻ አሻንጉሊት እየሆነ ነው። ይሄ ሁሉ የምዕራባውያን እጅ አለበት ። ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ አቆጥቁጧል ፣ ርኩሰት ምድሪቱን እንዲሞላ በፕላንና በዘመቻ መልክ እየተሠራ መሆኑ ልብ ይሏል ። እናም ይሄ ሁሉ መከራ በምዕራባውያኑ ተንኮል መሆኑ ጥሬ ሀቅ ነው።

ታዲያ ዋናዋ አሜሪካን በለቅሶ ፣ በልመና ፣ በሰላማዊ ሰልፍ ልቧ እንዲራራልን ማድረግ አልተቻለም ። በፍጹም በፍጹም ። ይህን የኢትዮጵያን ግፍ ያየ እግዚአብሔር ግን ከሰሜን ተራሮች የሚነሳ ድብቅ ጦር አዘጋጀ ። ከኒዩክለር ቦምብ በላይ የሚያወድም ልዩ ስውር ሰራዊትም አስነሳ ። የሚገርመው ይህ ከኢትዮጵያ የተነሳው ነፋስ ጉዞውን ወደ አሜሪካ ሲያደርግ በኢትዮጵያውያን ከተሞችና ህዝቦች ላይ ያደረሰው ጉዳት አልነበረም ። በቃ ኖርማል ነፋስ ነው ። ቀዝቀዝ ደስስስ የሚል ነፋስ ፣ ከሰሜን ተራራ ከቅዱስ ያሬድ ከስውሩ ጻድቅ ገዳም የተነሳው ነፋስ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እየተጎማለለ ፣ በአፍሪካውያን ሰማይ ላይ ቀስ ብሎ አደጋና ጉዳት ሳያመጣ ሳያስከትልም እየተገማለለ ወደ አሜሪካን አቀና ። እዚያ ነው ከፍተኛ ውድመት የሚያስከትለውና ማስተማርም የፈለገው እና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ነፋሱ ነፋስ ብቻ ነው ሆኖ የተገለጠው ። እንዲያውም ይህን ነፋስ በአፍሪካ ምድር ያየውም ሰው የለም ።

አሁን በአሜሪካና በዚህ በአውሮፓ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ የግዳቸውን አዙረው እየለፈለፉ ነው ። ኢትዮጵያ የአማኞች ምድር መሆኗንና በምእራባውያን የሴራ ፖለቲካ ምክንያት ክርስትናውም እንዲጠፋ ሀገሪቷም እንድትወድም እየተደረገ መሆኑን መናገር ጀምረዋል ። ይህ የእግዚአብሔር ቁጣም ነው በማለት የተደበቀውን እውነር በአደባባይ መግለጥ ጀምረዋል ።

ይኽ ከቅዱስ ያሬድ ገዳም የተነሳው ሄሪከን ኢርማ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው አውሎ ነፋስ በአሜሪካ ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን ውድመት Admas የተባለ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል ።

1. Hurricane Irma is roaring to Atlanta. It is expected to make a landfall as a tropical storm, with heavy rain and wind as much as 60 mph. [ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር የሚገሰግሰው ሄሪከን ኢርማ ፍሎሪዳ ላይ ነው፣ ነገ ሰኞ ጆርጂያ ግዛት፣ ብሎም አትላንታ ከተማ ይደረሳል፣ ከሄሪከንነት ጉልበቱ ቢቀንስም፣ ትሮፒካል ስቶርም ሆኖ ከባድ ዝናብና ጠንካራ ንፋስ ይኖረዋል።

2- The GA governor, Nathan deal issues a state of emergency for ALL counties in GA. He advised everyone to stay home Monday and Tuesday until further notice [ የጆርጂያ ገዢ ኔተን ዲል፣ ለሁሉም የጆርጂያ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፣ ለአስከቸኳይ ሥራ የተመደባችሁ፣ (አምቡላንስ ፣ መብራት ኃይል፣ ….) ካልሆናችሁ በቀር መንገድ ላይ እንዳላያችሁ ነው ያሉት። ይህ ሰኞ ብቻ ሳይሆን ማክሰኞም ጭምር ነው።

3- Almost all schools are closed on Monday. Check with your emplyer, as the Mayor of Atlanta talks about the city would be shut [ሁሉም ትምህርት ቤቶች ነገ ሰኞ ዘግተዋል፣ ማርታ ባስና ባቡርም በአትላንታ ነገ ሰኞ አይሠራም። የአትላንታ ሜየር ከተማችን ዝግ ትሆናለች ብለዋል።]

4. If you can, have water, milk, bread at home. Flash light also incase the power went off. If not late, fill up your car gas tank. Also make sure to charge your phone when the power is still there.[ ቤታችሁ ውስጥ መሰረታዊ ነገሮች ፣ ውኃ ፣ ወተት፣ ዳቦ.. ይኑራችሁ። የእጅ ባትሪና ሻማ ቢኖራችሁም ጥሩ ነው ። ከቻላችሁ መኪናችሁ ሙሉ ነዳጅ ይኑረው ። ስልካችሁንም መብራት እስካለ ድረስ ቻርጅ ማድረግ አታቁሙ። ]

5-. Last but not least. we found some volunteers who can host any Ethiopian evacuees from Florida for a couple of days. We already received two evacuees yesterday. Specially international students [from Ethiopia] who are in Savannah and Other Florida Universities most affected and no where to go. If we hear more we will get back to you and lets us know if you can host some. [ በመጨረሻም ፣ ከፍሎሪዳ አካባቢ ተፈናቅለው የመጡና መሄጃ ያጡ ወገኖቻችን ሊኖሩ ስለሚችሉ እነሱን ለመቀበል ተዘጋጁ። ትናንት ማምሻውን ሁለት ተማሪዎች ደውለውልን የሚቀበሏቸው ሰዎች አገናኝተናል። በተለይ አለማቀፍ ተማሪዎች (ከኢትዮጵያ ለትምህርት የመጡ) ፣ ከሳቫና እና ከፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲዎች ውጡ ከተባሉ ውስጥ ይኖራሉና ፣ ከሰማን ለጥቂት ቀናት እናስተናግዳቸው። ይላል የአቶ አድማስ መረጃ.! ።

ይኽ ከኢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች የተነሳው አውሎ ነፋስ ሰሜን አሜሪካን ካወደመ በኋላም ፊቱን ወደ ካሪቢያን ሀገራት አዙሮ ባልተለመደ መልኩ ሄሪከን ሂርማ-ዝናብና ነፋስ የቀላቀለ ውሽንፍር ጭኖ ጉዞውን ወደ ኩባ በማድረግ ኩባንም ክፉኛ መትቷታል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአብዛኛው አሜሪካውያን እና የካረብያን ሀገራትን ብቻ ያጠቃ የነበረው ሄሪከን ኩባን ሲያጠቃ አይታይም ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአካባቢውን ሀገራትና ኩባን ጭምር ሲያጠቃና ሲያወድም ታይቷል ።

ይኽ አውሎ ነፋስ በእስካሁኑ ሂደትም በሰዓት 257 ኪሎ ሜትር እየተጓዘ ታላላቅ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡
በአሜሪካ ብቻ 5.6 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው እንዲሰደድ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከ40 በላይ ንጹሐን ሰዎችም ሞተዋል ፡፡
በካረቢያን ሀገራት ደግሞ እስካሁን 20 ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል፡፡

¶ በፍሎሪዳ ብቻ 6.5 milion ህዝብ መብራት አልባ ሆኖ
ፍሎሪዳ ከዳር እስከዳር በድቅድቅ ጨለማ ተውጣለች ።
ይህች የባዕለ ፀጎች መኖሪያ ምርጥ ስቴት እንዳልተባለች ሰሞኑን እንደ እቃቃ ቤቶቿ በነፋስ ኃይል ፈራርሳለች ። በውኃም ተጥለቅልቃለች ።

¶ ፎሎሪዳን Hurricane Irma ተብሎ የሚጠራው አውሎ ነፋስ ከተሞቿን በሙሉ ሰው አልባ የሙታን መንደር አድርጓትት ከርሟል ። ነዋሪው ህዝብ አካባቢውን ጥሎ እንዲሸሽ ተደረጓል ። መሸሽ ያልሆነለት ደግሞ በየከተማው በተዘጋጀለት Shelter (መጠለያ)ገብቶ እንዲሸሸግ ተነገረው ። አሁን በፍሎሪዳ ግዛት 534 የሚደርሱ መጠለያዎች ተከፍተው አውሎ ነፋሱ ቤት ንብረታቸውን ያወደመባቸውን ዜጎች በጉያቸው ሸሸገዋል ። ሰባት ሺ የሚደርሱ የፍሎሪዳ National Guard አባላት የሀገሪቱ ወታደሮች ህዝቡን ለመርዳት በሥራ ላይ ተሠማርተዋል ። ከ2 ሺ የማያንሱት በየመጠለያው የተበተኑ ናቸው።

¶ ከ5.6 milion ያላነሰ ህዝብ ሄሪኬኑ ከመድረሱ በፊት ቤቱን ንብረቱን እየጣለ እንዲሸሽ ትዕዛዝ ደርሶታል።
ሄሪኬን Irma ከፍሎሪዳ በተጨማሪ በዋናነት ደቡባዊ ምስራቅ ጆርጅያና ደቡብ ካሎራይናንም በጎርፍ አጥለቅልቋቸዋል። መንገዶቻቸውንም ወደ ወንዝነት ቀይሯል።

¶ እንደ CNN ዘገባ ከሆነ ከ5.6 milion ያላነሰ ህዝብ ሄሪኬኑ ከመድረሱ በፊት ቤቱን ንብረቱን እየጣለ እንዲሸሽ ትዕዛዝ ደርሶታል። የGeorgia Power and Georgia EMC ገለፃ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ከ1.2 milion ህዝብ በላይ በአሜሪካ ጆርጂያ ላይ የመብራት አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦበታል ።

¶ በተጨማሪም ኖርዝ ካሎራይና 62,000 ፣ ሳውዝ ካሎራይና 61,000 ህዝብ በመብራት እጦት ላይ ነው። ይኽ Irma የተባለው ሄሪኬን መጠነ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ መሬት ላይ ሲያርፍ ስፋቱ የአሜሪካዋን ሚቺጋን የተባለውን ስቴት ያህል ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ሲናገሩ ሰንብተዋል።

¶ Irma በአጠቃላይ ዘጠኝ የሚደርሱ የአሜሪካ ስቴቶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ ይገኛል። ከሰሞኑ በእነዚህ ስቴቶች ሥራ ፣ ትምህርት የሚባል ነገር አይታሰብም ። በደረሰው አደጋ ምክንያት እንዲሁም ሥራ የሚባል ነገር ባለመኖሩ የደረሰው ኪሣራ ገና በውል አልታወቀም።

¶ የአሜሪካ ጦር ሃይል አባላት የሆኑት ወታደሮች። በየመጠለያው ያለውን ህዝብ ከመርዳት ጀምሮ ትላልቆቹን አውራ ጎዳናዎች በማፅዳት እና ለህዝቡ አስፈላጊ የሆነውን ቁሳቁስ በማቅረብ ሥራ ላይ ተጠምደው ከርመዋል። ለአሜሪካውያኑ ወታደሮች ገነት የሆነችው ምድራቸው ፍሎሪዳ አፍጋኒስታን ፣ ኢራቅ ፣ ሶሪያና ሊቢያ ሆናባቸው busy ሆነው ከርመዋልም ተብሏል ። ወታደሮቹ መተኮስ አይችሉም ፣ ማንስ ላይ ይተኩሱ ፣ መያዝና ጓንታናሞ መውሰድም አይችሉም ። በግዙፍ የጦር መርከብ ፣ በታላላቅ የጦር አውሮፕላኖችና በረቀቀ አውዳሚ የኒዩክለር ቦንቦችም የሚያቆሙት የተለመደ ጠላት አይደለም የመጣባቸው ።

140 የሚደርሱ የፍሎሪዳ ስቴት መናፈሻዎች(Florida State Parks)ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው ከርመዋል።ምድሪቱን ውብ ያደረጉ እነዚህ ፓርኮች በየዕለቱ በሰው እንደማይጎበኙ ሰሞኑን ፀጥ ረጭ ብለው ሰንብተዋል። የሚገርመው ነገር
ይህች በምድራችን ላይ የሚገኙ የባዕለ ፀጎች መኖሪያ የሆነችው ስቴት ሰሞኑን በደረሰባት ከባድ አደጋ ምክንያት ለደረሰባት ጉዳት ልክ እንደ እኛ እንደ ኢትዮ ጵያውያን እርዳታ እየተጠየቀላት ነው ። www.FloridaDisasterFund.org በሚል በተዘጋጀው ዌብ ሳይት ማንኛውም ሰው ከ10 ዶላር ጀምሮ በመስጠት ተባበሩን ብለው በግልጽ የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋልም ተብሏል።

¶ ለድንገተኛ አደጋ ፈጥኖ በመድረስ ከሚታወቁ ታላላቅ የበጎ ፈቃድ የእርዳታ ድርጅቶች ጀምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ሁሉም የተቻላቸውን ለማድረግ እየተራወጡ ነው። በተጨማሪ ከ10 ስቴቶች የተውጣጡ ከ14,000 ያላነሱ ወታደሮች የፍሎሪዳን ህዝብ ለመርዳት አካባቢውን አጥለቅልቀዋል። እናም የአሜሪካንን ህዝብ እግዚአብሔር ይድረስለት

Filed in: Amharic