>

ይቅርታ ቄሮ! የተጠራውን "ሰላማዊ ሰልፍ" እቃወማለው

Niimoona Boortolaa

እኔ በግሌ ትልቅ ሰጋት አለኝ። ወያኔ ከምንም ግዜ በላይ በኦሮሞ ህዝብ እና ቄሮ ላይ ቂም ይዛለች።ከዓመት ዓመት እያወረዷት፣ እየሞቱም እየበዙም ሰለ ተፈታተኗት “አጥፍቶ ለመጥፋት” ቋምጣለች።
በተደጋጋሚ ከቤት ያለ መውጣት አድማ ሲደረግ፣ በምትክሰረው ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን አንጀቷ የሚቃጠለው፣ ፊት ለፊት ተኩሳም ሆነ ዝልዝላ የምትገለው ሰው በማጣቷ ነው።
ይሄንን ለማሰረዳት ምንም ዓይነት ዶሴ ሳናገላብጥ የዛሬ ዓመት በእሬቻ ላይ ያውም ዋቃን ለማመሰገን ተሰብሰቦ አንድ ቦታ የተገኘውን የኦሮሞ ህዝብ ፃታ እና ዕድሜ ሳትለይ በሰማይ እና በምድር እሳት አዝንባ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሟ የትላንት ዘግናኝ ታሪካችን ነው።ያንን ያደረገችው ዓመቱን ሙሉ አንጀቷን ሲያቆሰል የከረመ “ጠላቴ” የምትለው ህዝብ ነጭ በነጭ በባህል አልባሳት ደምቆ ስታይ ደሟ ፍልቶ ነው።
አሁን ደግሞ እየሰማን ያለነው በምሰራቅ ኦሮሚያ እየተደረገው ባለው እልቂት ሳብያ “መንግሰትን ለመቃወም” ሰለማዊ ሰልፍ ተጠረቷል። ይህ ለእኔ ከዓርባ እና ከሃምሳ ዓመት በፊት የነበረው የኦሮሞ ህዝብ የፖለቲካ ሞኝነት ነው። ያውም በተንኮል፣ በሴራና በክፋት ተወልዳ ያደገቸው ወያኔ ይቅርና ያኔ የነበሩትም የእሷን ያህል ሴራ ይዘው የኦሮሞን ትግል እንዴት እንዳኮላሹት እናውቃልን።
ወያኔ አሰፍሰፋ የምትጠብቀው ቄሮ ተሰብሰቦ አደባባይ እንዲወጣለት ነው።እንኳን ያለ ተፈቀደ “ሰላማዊ ሰልፍ” ይቅር እና ፍቃድ በማያሰፈልገው የአምልኮ ሰፍራ ሂሊኮፕተር እና ዓልሞ ተኳሽ የምታሰማራ ጉደኛ አሁን በሰላም ወጥቶ ቄሮ ይገባል ተብሎ ሰለማዊ ሰለፍ ይጠራል? ምን ተማምናችሁ ነው?
ለመጀመሪያ ግዜ ከቄሮ አሰተባባሪ በተቃራኒ መቆሜን ስገልፀ ከልቤ እያዘንኩ ነው። ምክንያቱም የወያኔን ክፋት ቅርጥፍ አድርጌ አወቃለው። ዳግም የኦሮሞ ህዝብ በአንድ ቦታ በአንድ ጊዜ እንዲያልቅ እና በዓመቱ የኦሮሞ እናት መሪር ሀዘን እንዲቀመጡ ማየት ሰለማልፈልግ ነው። ኦሮሞን ስነ ስርዓት ማሰተማር አይቻልም እራሱ ህዝቡ የሰፉ ባለቤት ነው። ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ብሎ መሰብክ… ፖለቲካን ማወቅ እና ወያኔን ማውቅ ለየቅል ናቸው። በየወሩ አድማ ከመጥራት ልክ እንደ ባለፈው ዓመት በሰሜታዊ ሳይሆን በተጠና መልኩ የበቀል እርምጃ መውሰድ የተሻለ ውጤት የሚያመጣ ይመሰለኛል። በዚህ ምክምያት የተጠራውን “ሰላማዊ ሰልፍ” እቃወማለው። ሰላም ለራቀው ፀብ ለመጫር ከጎሮቤት አገር ጭምር ወታደር ገዝቶ የሚያሰማራ ቡድን እንዴት ሰልፍ ይወጣለታል? ውጡ እና እለቁ ይመስላል! Dhiifaama dhiiroo! Faarisaa natii intoolee!!

Filed in: Amharic