>

ኬኒያ:- ሰሞነኛ ክስተቶች (ዮናስ ሃጎስ - ናይሮቢ፤ኬኒያ)

– ኡሁሩ ኬንያታና ራይላ ኦዲንጋ ብቻ የሚፋጠጡበት የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከ25 ቀናት በኋላ ይካሄዳል።
– ሰሞኑን በሁለቱ የፖለቲካ መሪዎች መሐከል የቃላት ልውውጡ ከረር ያለ ሆኗል። ኡሁሩ

ኬንያታ የፍትህ ተቋሙን (በተለይ ምርጫው እንዲደገም የወሰኑትን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች) የ8 ሚልዮን ሕዝብ ድምፅ የሰረቁ ሌቦች ሲሉ በአደባባይ የወረፏቸው ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ትላንት በሰጡት መግለጫ የፍትህ ተቋማት የሚሰሩት ሕገ መግስቱን ተከትለው እንጂ በስልጣን ላይ ያለ አካልን ለማስደሰት አለመሆኑን አስረግጠው አስረግጠው የተናገሩ ሲሆን የሐገሪቷ ፖሊስ ለዳኞቹና ቤተሰቦቻቸው አስፈላጊውን ተጨማሪ ጥበቃ እንዲያደርግ የሰጡት ትዕዛዝ ለምን እንዳልተከበረ ማወቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። የፍትህ ተቋማቱ አካላት በሙሉ ሕገ መንግስቱን ተከትለው ስራቸውን መስራት እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ዳኛው በፍትህ ተቋማቱ አካላት አሊያም ቤተሰቦቻቸው ላይ አንዳችም ዓይነት አደጋ ቢደርስ በፍትህ ተቋማቱ ላይ የስድብና ዛቻ ናዳ ሲያወርዱ የነበሩ አካላት በሙሉ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቀው መግለጫቸውን ቋጭተዋል።

– ራይላ ኦዲንጋ የባለፈውን ምርጫ እንዳሰናከለው የሚያምኑበት የምርጫ ቦርድ የተወሰኑ ሐላፊዎች ከስራ እስካልተወገዱ ድረስ የሚካሄድ ምርጫ እንደማይኖር በማሳወቅ የሰጡት መግለጫም ሌላው የኬንያን መፃዒ እድል ያንጠለጠለ ነገር ሆኗል። ኬንያታ የምርጫው ቦርድ ባለው ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ሲሉ ቢያስጠነቅቁም ራይላና ደጋፊዎቻቸው ግን እንደማይቀበሉት ደጋግመው አሳውቀዋል። የምርጫ ቦርድ የድጋሚውን ምርጫ በማስቀጠል ረገድ ስለሚኖረው ሚና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የደረሰበትን ዝርዝር ውሳኔ በአሁኑ በቀጥታ ለኬንያ ሕዝብ ሰዓት እያስተላለፈ ይገኛል።

***
ይህ ውሳኔ በመጪው ምርጫ ላይ ዋናውን ሚና የሚጫወት ይሆናል ተብሎ ይገመታል…
Filed in: Amharic