>
10:03 pm - Wednesday February 1, 2023

መለስ አምባገነን ከሆነ ገዱ አጎብዳጅ ነው! (ስዩም ተሾመ)

የመለስ_ዜናዊ ደጋፊዎች ታላቁ መሪ፥ አባይ ደፋሪ፣ የተለየ ሃሳብ ፈሪ፣ የሃሳብ ደሃ ሆኖ “የሃሳብ ድህነትን” ያስወገደ መሪ…ጲሪሪሪ እያሉ ሲያሽቃብጡለት፥ ሲያሽቋልጡ፥ ሲያመልኩት አዝቅክት ውስጥ ጥሎን አለፈ፡፡ በመለስ ዜናዊ ላይ የስድብ መዓት ሲያወርዱ የነበሩት ደግሞ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተነካብን ብለው “ያዙኝ-ልቀቁኝ” እያሉ ነው፡፡ ይሄም እንደቀድሞ ሰው ማምለክ፥ አጎብዳጅነት…ማሽቃበጥ፥ ማሽቋለጥ፥… ነው፡፡
ማንኛውም የመንግስት ሃላፊ በሥራ አፈፃፀሙ ላይ ትችትና ነቀፌታ ሊሰነዘርበት ይችላል፡፡ በሥራው ካጠፋ በአስቸኳይ እርማት መስጠት፣ ካላጠፋ ማስተካከያ(ማስተባበያ) መስጠት በሃላፊነቱ የተጣለበት ግዴታ ነው፡፡ አቶ ገዱ ‘ያለአግባብ ተሰደብኩ ካለ፣ በዚህም ሰብዓዊ ክብሬ ተነካ  ወይም መልካም ስሜ ጠፋ” የሚል ከሆነ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርቦ መብቱን ማስከበርና ተገቢውን ካሣ መጠየቅ ይችላል፡፡
በምታዩት የክስ ቻርጅ መሰረት መሠረት አቶ እንዳልክ፣ ተመስገን እና ሰለሞን የተባሉ የባህር_ዳር ከተማ ነዎሪዎች “የፋሲል ደሞወዜን በቃኝ_ሂድልኝ የሚለውን ዘፈን አዳምጣችኋል” ተብለው የሚከስሰው ክልላዊ መንግስት ፕረዜዳንት አይደለም እንዴ? ፍፁም ብረሃኔ እና ዳንኤል ብረሃኔ ግን ዶማና አካፋ ሲሉት ዝም-ጭጭ የሚያስብለው የአፓርታይድ ስርዓት ግንባር ቀደም መሪ አይደለም! ይሄ ብቻ ገዱን ዶማ አያስብለውም? ይሄው እኔም “ዶማ፥ አጎብዳጅ!” ብዬ ሰደብኩት፡፡ ስዩም ሰደበኝ ከማለቱ በፊት በቅድሚያ እስኪ የብርሃኔ ልጆችን ከስሶ ሰብዓዊ ክብርና መልካም ስም እንዳለው ያሳየኝ፡፡ “ገዱ ተሰደበ” የሚሉ ሰው አምላኪዎች፥ ምድረ አጎብዳጆች፥ አሽቃባጭና አሽቋላጭ ሁላ፥… መጀመሪያ የአቶ ገዱ አስተዳደር “ዘፈን አዳመጣችሁ” ብሎ የከሰሳቸው አቶ እንዳልክ፣ ተመስገን እና ሰለሞን የክስ ጉዳያቸው የት እንደደረሰ ጠይቁ!!!
Filed in: Amharic