>
5:30 pm - Wednesday November 2, 3403

አማሮችን በገጀራ! ህወሃት በኢሉባቦር እየሰራ ነው (ክንፉ አሰፋ)

 

ህወሃት የአማራው ሕዝብ ላይ ያለው አቋም ከፋሺሽት ጣልያን የተወሰደ ውርስ ነው። በበላይ ዘለቀ ይመራ የነበረው ጦር ጣልያንን እስከፍጻሜው ተፋልሞ ባዋረደበት ግዜ – የጣልያኑ ጀነራል ደቦኖ የተናገረው በታሪክ መዛግብት ላይ ተቀምጧል።

“ደጋግሜ ተናግሬ ነበር። አማራና ኦርቶዶክ ቤተ ክርስትያን ካልጠፉ ሰላም ልናገኝ አንችልም። “

አቦይ ስብሃት እና አባይ ጸሃዬም ይህንኑ የደቦኖ  አነጋገር በተደጋጋሚ ሲሉት ተደምጠዋል።  የዛሬ 40 ዓመት የወጣው የህወሀት መኔፌስቶም  በገፅ 15 እና 16 ላይ  “ጨቋኟ አማራ ህብረተሰብአዊ እረፍትና ሰላም አታገኝም” ብሎናል።

ይህ ፕሮግራም  በወረቀት ላይ ብቻ ሰፍሮ አልቀረም። በተግባርም እያሳዩን ነው። በማጂ፤ ጉራ ፈርዳ ወረዳ ሠፋሪ አርሶ አደሮች በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገድደው ቀያቸውን ለቅቀው ወጥተዋል፤  በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ በአስር ሺ የሚቆጠሩ አማሮች  ላይ የማፈናቀል ዘመቻ ተደርጓል፣ ከዚህ ቀደምም በበደኖ፣ በኢንቁፍቱ፣ በወተር፣ በአርሲ፣  ወዘተ አማሮች ላይ የደረሰው ግፍ በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም። እስካሁን መልስ ያላገኘው በሕዝብና ቤት ቆጠራ 2.5 ሚሊዮን አማሮች የገቡበት ያለመታወቁም አንዱ የመሰሪ ፕሮግራም እቅድ ነው።

የህወሃት ማኒፌስቶ ወደ ተግባር ተለውጦ፣ ላለፉት 26 አመታት ግፍ እየሰራ ረጅም ተጉዟል። ወልቃይትና  ቅማንት ላይ ሲደርስ ደግሞ ማንነትን የሚፈታተን ትንቅንቅ ላይ ይገኛል።

የገጀራው እልቂት ግን ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ሳይሆን ይቀራል? ነገሩ እንዲህ ነው።  እየተንጠባጠበ ከሚወድቀው የንግድ አጋራቸው ይልቅ፤  የ”ጣና ኬኛ” ፖለቲካ እነ ደብረጽዮንን እረፍት እንደነሳቸው በስፋት ይነገራል። የማይወድዱት የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ህብረት መፈጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ገና ዳቦ የሚለበልብ ነቄ ትውልድ ሳያስቡት መጣባቸው።     ለጭንቅ ግዜ የቀመሩት የፖለቲካ ሂሳብም እንደቀድሞው ማርሽ እየቀየሩ የሚሄዱበት መንገድ አልሆን አላቸው። ስለዚህ ፊት ለፊት ገጀራ ይዘው መጨፍጨፍ/ማስጨፍጨፍ ተያይዘዋል። በዚህ ሁኔታ ስንቱን ገድለው እንደሚዘልቁት የሚያውቁት ግን አይምስልም።

ወትሮም ውርደት ጌጥ በሆነላቸው የብአዴን ዋርድያዎች ይህ  የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለም። ይልቁንም የአስደናቂው  የ”ጣና ኬኛ” ፖለቲካ አቀንቃኞች ለዚህ ጉዳይ ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚችሉ እርግጠኞች እየሆንን ነው። እነ ለማ መገርሳ ከነበሩበት የፍርሃት ቋት ራሳቸውን አውጥተው ከህወሃት እኩል መነጋገር የጀመሩ ይመስላል።

የእነ ደመቀ መኮንን ነገር ባይነሳ ይሻላል። ሲያሻው በቃርያ ጥፊ ሲያጮላቸው – ሲያሻው ደግሞ ሲተፋባቸው ይዘልቁታል እንጂ እንዲተነፍሱም እድል አይሰጣቸውም።  በዘረኝነት ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኙ ላሉት ለእነ ደብረጽዮን ከጥፊዋ ዋጋ ይልቅ የጥፊዋ ጠቀሜታ ነው የምትታያቸው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው አማራው ሲታረድ እነሆ ዝም ብለዋል።

ግዜውን ጨርሶ በባከነ ሰዓት እየተንፈራገጠ ያለው የትግሬ ቡድን ዛሬ በኢሉባቦር ከ20 በላይ ዐማሮች በአንድ ቀን ብቻ በገጀራ መጨፍጨፉ እጅግ የሚያንገበግብ ቢሆንም አዲስ አይደለም። ገዳዮቹ ግን ከቶውንም ከፍርድ አያመልጡም።   መውደቅያቸው ላይ ማጠፍያ ሲያጥራቸው ታርዶ እንደሚንፈራፈር ዶሮ የሆኑ ይመስላል… ይህ ሁሉ ሲሆን የአማራው ህዝብ ትዕግስት እንደ ፍርሃት ተቆጥሮ ከሆነ ግን ትልቅ ስህተት ነው።   ሁሉንም ግዜ ይፈታዋል!

Filed in: Amharic