>
10:52 am - Tuesday October 26, 2021

ህወሓት ተልዕኮውም፣ ታማኝነቱም ለትግራይ ብሄርተኝነት ነው (ግዛው ለገሰ)

የትግራይ በላይነት አለ

ህወሓት ተልዕኮውም፣ ታማኝነቱም ለትግራይ ብሄርተኝነት ነው

እስከ 1994 አካባቢ ደቡብ አፍሪካ የነጮች የበላይነት ነበር። ይህ በላይነት በሕግ እውቅና ያገኘ ስለነበር ብዙም አያከራክርም። ነገር ግን በነጮች በላይነት በተገነባችው ደቡብ አፍሪካ ድኃ፣ መሬት የሌለው፣ በስደት የሚኖር ነጭ የለም ማለት አይደለም። በአንፃሩም ጥሩ የሚኖሩ፣ ሀብት ያላችው ጥቁሮች የሉም ማለት አይደለም። ግን የስርዓቱ ባለቤት፣ የሀገሪቱን ዕጣ ፋንታ ለመወሰን ጥቁሮች ምንም ሚና አልነበራቸውም፣ ይከለከሉ ነበር። የደሃ፣ የልተማሩ፣ ንብረት አላባ ነጮች መኖር የነጭ በላይነት መኖሩን አያስክድም፣ አላስካደምም።
በ1860ዎቹ የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ሲያልቅ ባርነትን የሚሽር ህገመንግስታዊ ድንጋጌ 13ኛው የሕገ መንግስት ማሻሻያ (13th amendment ) ፀደቀ። ነገር ግን የተለያዩ ስቴቶች በተለይም በደቡብ የሚገኙት በዘረኝነታቸው በመቀጠል Jim Crow laws የሚባሉትን በማውጣት ጥቁሮችን መጨቆን ቀጠሉ። ይህ ሁኔታ እስከ 1960ዎቹ ቀጠለ። በነዝህ ግዜዎች ነጭ ድሆች፣ ስራፈቶች፣ ያለተማሩ፣ የሚቸገሩ ወዘተ ነበሩ። እንዲያውም የዘረኝነቱ ዋልታ እና ምሶሶዎች ደሃ ስቴቶች፣ ለምሳሌ Mississippi፣ alabama፣South Carolina Louisiana ናችው የነዝህ ነጮች ድህነት፣ ችግር፣ ሀብት ማጣት የነጮች በላየነት መኖሩን አያበስርም።
ስለዚህ የትግራይ በላይነት አለ ሲባል፣ የትግራይ ሕዝብ ድኅ ነው፣ በዙ ለማኝ ትግሬዎች አሉ፣ የትግራይ ሀዝብ ጭቁን ነው ወዘተ የሚሉት ነጥቦች እውነት ቢሆኑ እንኩአን ማስተባበያ ወይንም ማፍረሻ ሊሆኑ አይችሉም። ለእኔ የትግራይ የበላይነት መኖሩ የሚናገረው ስለትግራይ ሕዝብ የኢኮኖሚ ድህነት፣ ስደተኝነትወዘተ ሳይሆን ስለትግራይ ብሄረተኝነት ጠባብነት፣ ስግብግብነት፣ ስነልቦና ትንሽነት ነው። ተጨባጭ ማሰርጃዎች ማቅረብ ይቻላል።
1 አሁን ያለው ስርዓት ሙሉ በሙሉ ባለቤትነቱ የትግራይ ብሄረተኞች ነው። የዚህ ማረጋገጫው ሀገመንግስቱ ነው። የህወሃቱ ፃዳቃን ይህን በአንድ ፅሁፉ ላይ አረጋግጦታል። ከሀገራዊ ራእዩ፣ ከአገራዊ አወቃቀሩ፣ በህወሓት መመስረቻ ፅሁፎች ላይ የሰፈሩ ተስፋፍነቶችን እውን በማድረጉ፣ የዚህ ስርዓት፣ የሥርዓቱም ቀዳሚ መመሪያ ብቸኛ ባለቤት የትግራይ ብሔርተኘት ነው።
2 የሀገሪቱን ሁለተናዊ አቅጣጫ ላለፉት 26 አመታት የተወሰነው፣ የሚወሰነው በህወሓት ነው። ህወሃቶች ለማወናበድ የፓርላማ መቀመጫ ቁጥሩ በሀዝብ ብዛት ስለሆነ፣ ትግራይ 38 መቀመጫ ብቻ ስላላት የበላይነት የለነም ሲሉ ለእኛ ያላችውን ነቀት ከመግለጥ በስተቀር ውሸት መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። አጋርቱን የሚመሩት ፓርቲው፣ ወታደሩ፣ እና ደህንነቱ ናችው።
ፓርቲውን ስንመለከት ሁለት የትግራይ በላይነት ማረጋገጫዎችን አናያለን። አንደኛ ትግራይ ከኦሮሞ ከደቡብ ከአማራ እኩል መቀመጫ አላት። 6% ትግራይ ከ 32% ኦሮሞ 30%አማራ 28% ደቡብ እኩል ውክላና መኖሩ እና አገሪቱን የሚመራው ፓርላማው ሳይሆን ፓርቲው መሆኑ የትግራይ በላይነት መኖሩን ያረጋግጣል። ሁለተኛ ፓርቲው ውስጥ አክራሪ የትግራይ ብሄርተኞች ሲኖሩ የሶስቱ ተቀጥያ ድርጅቶች አማራሮች በቦታው የተቀመጡት ለትግራይ ብሔርተኝነት ባላቸው ታማኝነት አና እንወክላለን ለሚሉት ሕዝብ ባላቸው የተንሸዋረረ እይታ ነው። ስለሆነም የፓርቲው እውነተኛ አመራር ህወሓት ነው፣ ተልዕኮው፣ ታማኝነቱ ለትግራይ ብሄርተኝነት ነው።
በሥራ አስፈፃሚው፣ በመከላከያ፣ በፍትህ ስርዓቱ በደህንነት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወሳኞቹ የትግራይ ብሄርተኞች ናችው። ይህም የትግራይ በሄተኝነት በላይነት ማረጋገጫ ነው።
3 አገርቱ ያሉ ሚድያዎች የግልም ይሁን የመንግስት የbroadcastም ይሁን የህትመት በትግራይ ብሄርተኞች ቁጥጥር ስር ናችው። EBC፣ Walta፣ ENN፣ ረፖርተር፣ Addis Fortune፣ አዲስ ዘመን፣ ሰንደቅ ወዘተ በትግራይ ብሄርተኞች ቁጥጥር ስር ናችው።
4 የአለፈ ታሪክን ማጥቆር እንደገና ለገዥው በሚመች መልክ መፃፍ የተለመደ የድክቴተሮች ሥራ ነው። አሁን እንደምናየው ታሪካችንን ሰርዘው፣ ጀግኖቻችንን አጥላልተው በራሳችው ድርሰቶች ለመተካት የትግራ ብሄርተኝነት የሚያደርገውን ውጣ ውረድ ስናይ የትግራይ ብሄርተኝነት መኖሩን ማረጋገጫ ነው። ምንሊክ ፈሪ፣ አየር ኃይል የማይረባ ነበር አድዋ የዘመቱት ትግርኛ ተናጋሪውን ለመከፋፈል ነው፣ እኛ ጀግኖች እነሱ ፈሪዎች ወዘተ የመሳሰሉ ትረካዎች ከበላይነት የሚመነጩ ናችው።
ምናልባት ሌሎችም ሊኖሩ ይችላል። ዋናው ነጥብ ችግሩን ለመፍታት እውነት መናገር አለብን። የትግራይ በላይነት እውነት ነው።

Filed in: Amharic