>
  • breaking: Ato Eshete Moges: a lion among men, whose courage blazed like fire across Fano 09.18.2025 | 0 comment
  • breaking: Don’t be Slaves to Fear 09.04.2025 | 0 comment
  • breaking: The Opaque New Phase of the Red Sea Competition 09.03.2025 | 0 comment
  • breaking: Amhara Fano People’s Organization (AFPO) Response to the U.S. Department of State’s 2024 Human Rights Report on Ethiopia 08.17.2025 | 0 comment
  • breaking: Journalist Getiye Yalew leaves Ethiopia in threat of government attack 08.16.2025 | 0 comment
EthioReference
  • Home
  • Categories
    • Amharic
    • Current Affairs / News
    • Videos
    • Music & Dramas
    • Articles & Opinions
    • References
    • Interviews
    • Sport
  • Bloggers
    • WONDIMU’S BLOG
  • Radios
    • 1888 Radio
    • Addis Dimts
  • Contact Us
  • Ethiopia Nege
  • Ethio360 Media
  • Ethiopia Zare
  • mejemer

ህወሃት በመቀለ ስብሰባው የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን እንዴት ጠራርጎ እንደሚያስወግድ እየተወያየ ነው (ስዩም ተሾመ)

Posted by admin | November 9, 2017 | Comments Off on ህወሃት በመቀለ ስብሰባው የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን እንዴት ጠራርጎ እንደሚያስወግድ እየተወያየ ነው (ስዩም ተሾመ)
ከዶ/ር ደረስ ጌታቸው ጋር “VOA” በጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው መሪነት ስለ #ኦሮማራ እየተወያየን ነበር፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስር-ነቀል ተሃድሶ አድርጎ አሁን ያለው የፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ ምን መደረግ አለበት በሚለው ላይ ተወያይተናል፡፡ ውይይቱን ስታዳምጡ ለብዙዎቻችሁ ጭፍን የኦህዴድና ብአዴን ደጋፊ የሆንኩ ሁሉ ሊመስላችሁ እችላለሁ፡፡ በእርግጥ ኦህዴድና ብአዴን የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እንደመሆናቸው መጠን አሁን በሀገሪቱ ለተከሰተው ችግር በቀጥታ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ህወሃት ግን ከሁለቱ በጣም በተለየ መልኩ ጨቋኝና አምባገነን በመሆኑ ዋና የለውጥ እንቅፋት ነው፡፡ ኦህዴድና ኢህአዴግ ከሚወክሉት ህዝብ ጎን አለመቆማቸው ያስወቅሳቸዋል፡፡ ህወሃት ግን ከትግራይ ህዝብ ጎን አለመቆሙ ብቻ ሳይሆን ብአዴንና ኦህዴድ ከህዝባቸው ጎን እንዳይቆሙ ማድረግ የሌት-ተቀን ሥራው ነው፡፡ በህወሃቶች ዘንድ #ተሃድሶ ማለት የሚወክሉትን ህዝብ ጥያቄ የመቀበል ወይም የድጋፍ አዝማሚያ ያሳዩትን የብአዴንንና ኦህዴድን አመራሮች መምታት ነው፡፡ ህወሃት የኢህአዴግ መስራች ድርጅት ብቻ ሳይሆን ዋና ማነቆ ነው፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ መንግስት ህልውና እንዲቀጥል በመጀመሪያ ህወሃት/ኢህአዴግ የህዝቡን ጥያቄ ተቀብሎ እንዲያስተናግድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሞላ-ጎደል አልተሳካም፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ሁለተኛ አማራጭ የለውጥ ማነቆ የሆነውን ህወሃትን ከኢህአዴግ ውስጥ ማስወገድ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከብአዴንና ኦህዴድ አንዱ ከግንባሩ ራሱን ማውጣት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ይፈርሳል፡፡ እስከ 2012 ድረስ አብላጫ ድምፅ ያለው ኦህዴድ መንግስት እንዲመሠርት ይጠየቃል፡፡ ከዛ ከብአዴን ጋር ተጣምሮ የራሱን መንግስት ይመሠርታል፡፡ በዚህም ህወሃትን ጠራርጎ ማስወገድ ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግ ከተሳናቸው ህወሃት በመቀለ ስብሰባው የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን እንዴት ጠራርጎ እንደሚያስወግድ እየተወያየ ነው፡፡ ከስብሰባው በኋላ ኦቦ ለማ ሆነ አቶ ገዱ፣ አቶ ንጉሱ ሆነ ኦቦ አዲሱ፣…ሁሉም ተጠራርገው ይወገዳሉ፡፡ ከትላንት ጀምሮ የህወሃት ሸርና አሻጥር እየተሸረበ ያለው በዚያ ላይ ነው!! ከዚህ በተረፈ ህወሃት በ1993ቱና በ2008ቱ ተሃድሶ ክፉኛ ተፀፅቶ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ ለመፈፀም እያሰበ ያለውን  ያዩታል፡፡
 
Filed in: Amharic
  • Home
  • Contact Us
  • Privacy
  • Site Admin
© EthioReference. All rights reserved.