>
7:47 am - Wednesday July 6, 2022

ተማሪዎች እና ‹‹ ተማሪዎች›› (ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሞረዳ)

መቱ ዩኒቨርሲቲን እንደማጣቀሻ በመጠቀም በተማሪዎች መሐከል እየተፈጠረ ስላለዉ አለመግባባት እየተወሳ ይገኛል፡፡
ዘመነ ወያኔ ከሰጠን ልምድ በመነሳት ስለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስንናገር ልንስተዉ የማይኖርብን እዉነት አለ፡፡
ትምህርት ፍለጋ መፅሐፍና ደብተር ይዘዉ ዩኒቨርሰቲ ከሚገቡት ተማሪዎች በተጨማሪ ቦምብና ሽጉጥ ታጥቀዉ ገብተዉ ለመማር ሳይሆን ለስለላና ለሽብር ተግባር ዓመት ሙሉ በየትምህርት ተቋማቱ የሚኖሩ ‹‹ ተማሪዎች›› እንዳሉ በይፋ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ደግሞ በአብዛኛዉ አንድ ቋንቋ ተናገሪ የወያኔ ግልገል ካድሬዎች ናቸዉ፡፡ አሥር ዓመት ሙሉ ‹‹ተማሪ›› እየተባሉ በዩኒቨርስቲና በኮሌጆች ዉስጥ የሚኖሩ ደመወዝተኛ ሰላዮች እንዳሉ ሀገር ያዉቃል፡፡ እነዚህ ሰዎች ተማሪዉን ብቻ ሳይሆን የየተቋማቱን ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጭምር የሚሰልሉ፣ አንዳንዴም የየተቋማቱን ኃላፊዎች የሚያዙ ስዉር ባለሥልጣናት ናቸዉ፡፡
ሌሎችም የተማሪነትና የሰላይነትም ተልዕኮ ይዘዉ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ታቅዶ የሚመደቡ ተማሪዎች አሉ፡፡ በተለይም የወያኔ ተልዕኮ ተሸካሚዎች፡፡ ለዚያዉም ዩኒቨርስቲ ሊያስገባቸዉ የሚያስችል ነጥብ ሳይኖራቸዉ፡፡ ባለፉት ዓመታት ስንት በራሳቸዉ የሚተማመኑ ጎበዝ ተማሪዎች በእነዚህ አሸባሪዎች በሚደርስባቸዉ ክትትልና ማስፈራራት የተነሳ ለሥነልቦና ቀዉስ ተዳርገዉ ትምህርታቸዉን አቋርጠዉ ወጥተዋል፡፡
ይህ ግን ‹‹የታወቀ ነዉ፣የተለመደ ነዉ›› እየተባለ መቀጠል የለበትም፡፡ ማነዉ ማንን በገዛ ቀዬዉ እያሸበረዉና እያሸማቀቀዉ እንዲኖር የተለየ ፈቃድ የተሰጠዉ? 

ወንድሞቼና እህቶቼ እርግጥ አሁን ያላችሁበትን ሁኔታ ከእናንተ የበለጠ ባላውቅም አንድት ምክር ቢጤ ግን ላስተላልፍ እሞክራለሁኝ።
ህውሃት አርቲፊሻል ግጭት ፈጥሮ በቦይንግና በV8 ኮብራ የራሱን ብሄር ተዎላጆች እየጫነ እስከ ሱዳን ድረስ በመውሰድ ሙቪ ( Muvie) እንደሚሰራ ጎንደር ላይ ባለፈው አመት ሁላችንም ተመልክተናል።
አሁንም ወያኔ አንዳንድ ኤጀንቶቹን በመላክ በብሄር መካከል ግጭት እየፈጠረ እንደሆነ እየሰማን ነው። አሁን በዚህ ወሳኝ ወቅት እናንተ በከፍተኛ ብስለትና አስተዋይነት ይሄን የተደገሰላችሁን አደገኛ ሴራ ማክሸፍ አለባችሁ። የኦሮሞ ሽማግሌዎችና አባገዳዎች የሚመክሯችሁን ስሟቸው። ግቢውን ለቃችሁ አትውጡ ። እናንተ አንድ ነገር ብትሆኑ በአፋጣኝ የሚደርስላችሁ አሳማው ብአዴን ወይም የፌስቡክ አክቲቪስት ሳይሆን በአካባቢው ያለው ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ነው። እርስ በርሳችሁ በመነጋገርና በመደራጄት መረጃ በመለዋወጥ ራሳችሁን ጠብቁ ተምሮ ራሱን፣ ሀገሩንና ወገኑን ለመጥቀም የሚፈልግ ተማሪ በፍላጎቱና በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉ ሕግና ደንብ በሚፈቅድለት አግባብ መብቱ ተከብሮለት፣ የሕግ ጥበቃ እየተደረገለት የትም የመማር መብት አለዉ፡፡

እዉቀት ፈላጊ የትግራይ ተማሪዎች መቱ፤ የኦሮሞ፣የአማራ ፣የጉራጌ…ተማሪዎችም ትግራይ ዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ በነፃነት የመማር የዜግነት መብት አላቸዉ፡፡ በዘራቸዉ ብቻ ተለይቶ የሚደርስባቸዉ አድልኦና የሚፈፀምባቸዉ ሁከት መኖር የለበትም፡፡ ካለም መወገዝ ይኖርበታል፡፡
ማፊያዉና ወንበዴዉ ግን አንድ ቦታ ላይ ‹‹ በቃህ›› መባል አለበት፡፡ ይህንኑ ወንጀል ለመሸፈንም ‹‹ የእንትና ክልል/ብሔር ተማሪዎች ጥቃት ተፈፀመባቸዉ ›› የሚባለዉ የወያኔ ስሞታ ዉኃ የሚቋጥር አይመስልም፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሕወሓት ሰላዮችና ማፊያዎች የግድ መፅዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ‹‹ ተማሪ›› ተብዬዎቹ ብቻም ሳይሆን ይህንን ቆሻሻ ተግባራቸዉን እያወቁ ለብልግናቸዉ ሁሉ ይሁንታ ሲሰጡ የኖሩ ኃላፊዎችና መምህራንም ጭምር ቆም ብለዉ ማሰብ የሚገባቸዉ ጊዜ አሁን ነዉ፡፡
ተባዩ ከየቦታዉ መፅዳት አለበት፡፡ተባይ ለምን ፀዳ ተብሎ የሚንጫጫ ለወያኔ ካድሬም ‹‹ እናዝናለን›› ማለት ብቻ ነዉ የሚቻለዉ፡፡ ተባይ እያፀዳ ያለዉን የመቱ ዩኒቨርስቲ ማኅበረሰብንም በርቱ ማለት ተገቢ ነዉ፡፡ሌሎችም አካባቢዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ያሉትን ተባዮች የማስፅዳት ዘመቻ እንደሚያካሂዱ ተስፋ ይደረጋል፡፡
ዋጋ የሚያስከፍልም እንኳ ቢሆን ዘላለም እያከኩ መኖር ይኣክል፡፡

Filed in: Amharic