>

እፍረተ ቢሱ በረከት ሰምዖን (አቻምየለህ ታምሩ)

ይህ ከታች ሲናገር የምትመለከቱት ነውረኛ ፍጡር መብራህቱ ገብረህይወት ወይንም በሚኒስትር ስሙ በረከት ሰምዖን ይባላል። ይህ ፍጡር ዘሩ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊ ነው። ይህ በዘሩ ሙሉ በሙሉ ኤርትራዊ የሆነ የሰው ጠንቅ ወያኔ በአማራ ስም ያቋቋመው ድርጅትና ክልል ገዢና ፈላጭ ቆራጭ ነው። የዘር ፖለቲካ የሚያራምድ ማንም ሰው የግድ እሱም በዘሩ መደራጀትና በዘሩ የተደራጀ ፓርቲ መሪ መሆን አለበት እንጂ ዘሩ ያልሆነን ድርጅት ሊመራ አይችልም። ወያኔ ኤርትራን ካስገነጠለ በኋላ በረከት ሰምዖን ሊሆን የሚችለው በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር እንጂ በአማራ ስም ያቋቋሙት ድርጅት ገዢ ሊሆን አይችልም።

ፋሽስት ወያኔዎች «አማራ በዘሩ መደራጀት አለበት» ብለው አማራውን ሊመትሩበት በአማራ ስም ያቋቋሙትን ነውረኛ ድርጅት ላለፉት 26 ዓመታት ሲገዛ የኖረው ኤርትራዊው መብራህቱ ገብረህይወት አይኑን በጨው አጥቦ «የትኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ሌላ ብሔር ነው የሚያስተዳድረኝ ሊል አይችልም፤ ሁሉም ራሱን በራሱ ነው የሚያስተዳድረው፤ አማራ ክልል ብንመጣ [ክልሉን] የአማራ ልጆች ናቸው የሚያስተዳድሩት፤ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ማዕከል በማድረግ የተገነባው ፌድራሊዝም አንዱ ሌላውን በማስተዳደር ይጫነዋል እንዳይባል ተደርጎ የተቀየሰ ነው» ይለናል።

ይህ ከራሱ ጋር የተጣላ እፍረተ ቢስ ነውረኛ ፍጡር በዘሩ ኤርትራዊ ሆኖ የአማራ ድርጅት ብለው ያቋቋሙትን እየገዛ ነው እንግዲህ « አማራ ክልል ብንመጣ [ክልሉን] የአማራ ልጆች ናቸው የሚያስተዳድሩት» በማለት በእፍረተ ቢስነቱ ታአብዮ የሚያላዝነው። እሱ ራሱ «የትኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ሌላ ብሔር ነው የሚያስተዳድረኝ ሊል አይችልም» ሲል ባቀረበው መመዘኛ ኤርትራው በረከተ ሰምዖን ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ የለውም። እሱ የሚገዛዝ በአማራ ስም የተቋቋመ ድርጅት አላማ በአማራ መቃብር ላይ የትግራይ ሪፑብሊክ ግንባታን ማሳለጥ ስለሆነ ኤርትራዊው የአማራ ወኪል ሆኖ ላለፉት 26 ዓመታት እየመተረን የወያኔ ፍላጎት በኛ ሞት ላይ እያደላደለ ይገኛል።

ለራሱ ክብር የሌለው የአጋንንት ሎሌው በረከት ሰምዖን «የትኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ሌላ ብሔር ነው የሚያስተዳድረኝ ሊል አይችልም፤ አማራ ክልል ብንመጣ [ክልሉን] የአማራ ልጆች ናቸው የሚያስተዳድሩት» ሲል ስለተናገረለት የአማራ ክልል ተብዮው የወያኔ መፈንጫ ክልሉን የሚገዙት ከራሱ ከበረከት ጀምሮ የትግራይ ብሔር ተወላጆች ስም ዝርዝር በጥቂቱ እንደሚከተለው ይቀርባል፤

1. መብርሀቱ ገብረሕይወት [ በረከት ሰምዖን] — የብአዴን ማዕከላዊ ኮምቴ አባልና አመራር — ትግሬ

2. መኮነን ወልደ ገብርዔል— የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የአማራ ክልል ምክር ቤት ህግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ— ትግሬ

3. ከበደ ጫኔ — የንግድ ሚኒስትር የነበረ፤ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትር —ትግሬ

4. ካሳ ተ/ብርሃን— የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር— ትግሬ

5. ህላዌ ዮሴፍ— በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር — ትግሬ

6. ዮሴፍ ረታ — የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የነበረ—ትግሬ

7. ገነት ገ/እግዚአብሄር—የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ—ትግሬ

8. መለስ ጥላሁን— የብዓዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ አባልና የጥረት ኮርፖሬት ምክር ቤት ሊቀመንበር—ትግሬ

9. ታደሰ ካሳ — የጥረት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ — ትግሬ

10. ተሠማ ገ/ሕይወት— የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ —ትግሬ

11. ተተካ በቀለ — የብዓድን አባልና የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ — ትግሬ

12. ልዑል ዮሐንስ — «የአማራ ክልል» ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ክትትል — ትግሬ

13. ጸሃዩ መንገሻ — የወልዲያ ከተማ ከንቲባ— ትግሬ

የቀሩትን እናንተ ዘርዝሯቸው።

Filed in: Amharic