>
3:10 am - Wednesday February 1, 2023

የህወሃት በቀል ማቋረጫ የለውም (ሉሉ ከበደ)

የህውሀት በቀል ማቋረጫ የለውም። በኦሮሞ ህዝብ ላይ በክልል አምስት ልዩ ፖሊስ እያስፈጸመው ያለውን ጥቃት አንደገና ቀጥሏል።
በቦረና ጉጂ፤ በሞያሌ በባሌ በኢትዮጵያ ሶማሌ አጎራባች ክልልሎች ግጭቱ ተባብሶ ቀጠለ ይሉናል የኮሙኒኬሽን ጽፈት ቤት ሃላፊው የወያኔ ባለስልጣን። ። ግጭት የሚባለው ሁለት ወገኖች( conflict of interest ) በማናቸውም አይነት ይዘትና ቅርጽ ያለ ጥቅም ሲያጋጫቸው ሁለቱም ተነሳስተው አንድ ነገር ሲደራረጉ ማየት ነው። ይሄ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልልሎች መካከል የህዝብ ግጭት ተከሰተ እያለ ወያኔ የሚነግረን ውሸት በሰላማዊ ህዝብ ላይ እራሱ የሃገሩ መንግስት ያቀናበረው ወረራ ወይም ጥቃት ወይም ወታደራዊ እርምጃ ነው። በሰለጠነ ወታደራዊ እዝ የሚንቀሳቀስ ሰራዊት ትእዛዝ እየተሰጠው በሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ነው። የኦሮሞና የሱማሌ ህዝብ ግጭት አይደለም።
ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎችየመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ቢገባም ችግሩን ለማስቆም እንዳልተቻለና አሁንም እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ዶክተር ነገሬ ሌንጮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገልጸዋል። አሳት ዜና ኖቭ 25/2017።
ለምንድነው ማቆም አልቻልንም የሚሉን? እሰው ሃገር ለሰው መንግስት ጥቅም ሶማሊያ ዘምተው አልሻባብን የሚያህል ተዋጊ አስቁመው አልነበረ እንዴ? አሁንም እዚያው እየተዋጋ አይደለም ህውሃት የሚያዘው ጦር? በኢትጵያ ህዝብ ግብር የሚተዳደር የራሱን ህዝብ ሉአላዊነት እና ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ ሰራዊት ታማኝነቱ፤ ጠባቂነቱ ለማን ነው?
ውድ ወገኖቼ እስቲ አንድ ማነጻጸሪያ ልስጣችሁ። ይህ የኦሮሞን ህዝብ እንዲገድል የተሰማራው የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በ አብዲ ኢሌ ትዛዝም ይሁን በሌላ ሰው ትእዛዝት ግራይ ውስጥ ገብቶ ድንገት ኦሮሞዎችን እንዳደረገው፤ መንደሮችን ማቃጠል ሰላማዊ ዜጎችን መግደል ቀጠለ እንበል። ምን የሚከተል ይመስላችኋል? ግጭቱን ማስቆም አልተቻለም ተብሎ ህዝቡ እንዲያልቅ ይተዋል? ይደረጋል? ምን ሊሆን እንደሚችል ንገሩኝ።
በዚህ ህውሃት መራሽ ወረራ 700000 በላይ ንጹሃን ዜጎች ተፈናቅለዋል ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት ተቃጥሏል ።ተዘርፏል። ለግጭቱ ምክንያት ሆነዋል የተባሉትን ዶክተር ነገሬ መታሰራቸውን ተናግረውናል። ከኦሮሚያ 98 ከሶማሌ 5 ሰዎች ተይዘው ታስረዋል ብለውናል። እግዜብሄር ያሳያችሁ። ህዝቡን እየገደለ ካለው ወገን ከበዳዩ ወገን አምስት ሰው ፤ ሲጠየቅ ከተበዳዩ፤ ከሚፈናቀለው ከተዘመተበት ወገን 90 ሰው።
ሰራዊቱ ለምንድነው ይህን በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ወረራና ግድያ ማስቆም የማይፈልገው ? ወይም ያልቻለው? መልሱ ቀላል ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነቱንና ሉአላዊነቱን የሚጠብቅ ሰራዊት የለውም።
“በግልጽ የሚታይ ምንም ግራና ቀኝ የሌለው የፓርቲ ሰራዊት ነው። ” ብርጋዴር ጀነራል ሀይሉ ጎንፋ ነበሩ የሰብ አዊ መብት ጋዜጠኛው የኢሳቱ ወንድማገኝ ጋሹ ሲያነጋግራቸው የመለሱት። በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በወያኔ ጀነራሎች ትእዛዝ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወረራ አስመልክቶ ከልምዳቸው አኳያ እየሆነ ያለውን ትክክለኛ ነገር ሲያስረዱ ጀነራል ሀይሉ “… በሱማሌና በኦሮሞ ህዝብ መካከል አንድም የህዝብ ግጭት አልነበረም።በደንብ ፕላንድ የሆነ ፤ፕላን የወጣለት ፤በደንብ የታሰበበት ፤ በደንብ በሚሊታሪ ደረጃ ፤ …በደንብ ስትራክቸር ተደርጎ ፤ እንዲጋጩ እየተደረገ ነው ምክንያቱም የግጭቱን ኤሪያ ስናየው ከሁለት ሺህ እስከሶስት ሺህ ኪሎሜትር የሚሽፍን ቴሪቶሪ ላይ ነው። ግጭቱ እንደድሮው የብሄረሰቦች ግጭት አልነበረም።ድሮ በውሀ በሳር ወይም በከብቶች በመሳሰለው ነበር ግጭት የሚሆነው።ያሁኑ እንደዛ አይደለም። የውሃ እጥረት በሌለበትም የሚያዋስን ኤርያ ነው በማይባልበት በጣም የተገባበት፤……በጣም ትራንስፖርት የተደረገበት፤ በጣም ዌል ኦርጋናይዝድ የሆነበት፤ በጣም ዌል አርምድ የሆነ ሰራዊት የተንቀሳቀሰበት ግጭት እንዲፈጠር ከአመት በላይ የተንቀሳቀሱበት ነው።ይሄን ማነው ያደረገው? ጀነራሎች ናቸው። በደንብ ትምርት የቀመሱ። የሚያቁ። በካርታ ስእል በደንብ የሰለጠኑ…..” ይህን ሃቅ ባንደበታቸው ያስረዱን በወያኔው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እስከ ብርጋዴር ጀነራልነት የደረሱ ነገር ግን ትግሬ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ሰራዊቱን በማዘዝ ደረጃ ከተወሰነ መስመር ማለፍ ስለሌለበት፤ ቦታው ለትግሬዎች ስለሚገባ፤ ከሰራዊቱ ተወግደው እንዲሄዱ የተደረጉ ናቸው። አሁን በስደት ላይ ይገኛሉ። የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው።በየጊዜው ካስወገዷቸው የአማራና የኦሮሞ መኮንኖች አንዱ ናቸው።
ለዚህ ነው ህውሃት የሚባል ድርጅት አከርካሪው እንዲመታና ጥልቅ ጉርጓድ ውስጥ እንዲቀበር ያ ካልሆነ በኢትዮጵያ ምድር ከቶም ከቶ ሰላም ሊመጣ አይችልም የምንለው። የትግራይ ህዝብ በስሙ የሚነግዱትን እነዚህን በቁጥር የተወሰኑ ግለሰቦች ከጉያው አውጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳልፎ መስጠት አለበት።ህውሃት ማለት የትግራይ ህዝብ ማለት አይደለም። የትግራይ ህዝብ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ማለት ነው። የሚፈሰው የኦሮሞ ደም ደሙ ነው የሚፈሰው የአማራ ደም ደሙ ነው።
Filed in: Amharic