>

ሕወሃት እንኳን ተለውጦ ሞቶም ከራሱ የበላይነት ሌላ አያሰብም፣ አያሳስበውም! (ስዩም ተሾመ)

ሕወሃት አባይ_ወልዱንከሊቀመንበርነት አወረደ፣ #አዜብ_መስፍንን ከድርጅቱ አገደ፣ #አርከበ ዕቁባይ ወጣ፣ ዶ/ር #ደብረፂዮንመጣ፣ … የአቦይ ስብሃት ቤተሰብ ሰባ፣ አባይ ፀሐዬ ገባ፣ … ወዘተ፣ ማንም ወጣ፥ ማንም መጣ፣ “#የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!” የሚል አመራር ሊመጣ አይችልም፡፡ ሰሞኑን በሕወሃት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት፣ ዛሬ ደርሶ “እከሌ ተቀጣ፣ እከሌ ደግሞ ወጣ!” የሚሉት ከትጥቅ ትግል ጀምሮ የተለመደ፣ የማይቀየር የሕወሃት ድርጅታዊ ባህላቸው (Organizational Culture) እኮ ነው፡፡ ሕወሃት በውጫዊ ሃይል አስገዳጅነት ካልሆነ በስተቀር በራሱ ተነሳሽነት ለውጥና መሻሻል አምጥቶ አያውቅም፡፡ የተለወጠ መስሎ ቢቀርብ እንኳን የቀድሞውን ዓላማና ግብ ለማሳካት እንጂ አዲስ ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ ሊሆን አይችልም፡፡

ልብ አድርጉ…ሕወሃት ከዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው #በኦሮማራ ጫናና ግፊት ነው፡፡ አባይ እና አዜብ የተመቱት ትምክህተኛና ጠባብ ሃይሎችን ለመምታት በሚደረገው ጥረት አጋዥ ሆነው ባለመገኘታቸው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ አስሬ ቢቀየር፣ ቢቀያየር “#የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!” የሚል አመራር ሊመጣ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ የተፈጠረው የኦሮሞና አማራ ህዝብን በመለያየትና በማጋጨት የራሱን የበላይነትን በማስቀጠል ላይ ነው፡፡ ስለዚህ አይደለም በአመራርና በአሰራር ለውጥ፣ ሕወሃት #ሞቶ_ቢነሳ እንኳን ለኦሮሞና አማራ ህዝብ መብትና ተጠቃሚነት መስራት ሆነ ማሠራት አይችልም፡፡ አንዳንዶች ሕወሃት ውስጥ የሚስተዋለው “ለውጥና ሽግሽግ የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል” የሚል ተስፋ አላቸው፡፡ ነገር ግን፣ ሕወሃት በህይወት እያለ ሞቶና ተቀብሮ እንኳን የራሱን የበላይነት ከማስቀጠል ያለፈ ሌላ ነገር አያስብም፣ አይሰራም፣ አያሰራም!! #ሕወሃት ሲስቅ ሆነ ሲጠላ #አያስብም ከራሱ ሌላ! ሕወሃት እንኳን ተለውጦ ሞቶም ከራሱ የበላይነት ሌላ አያሰብም፣ አያሳስበውም!!

Filed in: Amharic