>

ህውሃት የጭን ቁስል የሆነባትን ኦህዴድን ለመቋቋም  ስትራቴጅ የተዋሰች ትመስላለች (ቬሮኒካ መላኩ)

በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የ KGB ስውር እጅ መቋቋም ያስቸገራት አሜሪካ ታዋቂ ምሁሮቿን ሰብስባ መላ ስታፈላልግ ታዋቂው የዬል ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር Dulles ለአሜሪካ መንግስት አንድ ምክር ቢጤ እንደሚከተለው በማለት ጣል አደረገ
<< The government has to “fight fire with fire,” and then The CIA, by implication, had to model itself upon the Soviet State Security Service, which “is more than a secret police organization, more than an intelligence and counter-intelligence organization. It is an instrument for subversion and manipulation.”
ፕሮፌሰር ዱል “ኬጂቢን ለማሸነፍ ሲአይኤ በኬጂቤ ሞደል ራሱን ቀርፆ እሳትን በእሳት ማጥፋት አለበት!” ብሎ መከረ። የፕሮፌሰር ዱል ምክረ ሀሳብ ወድያውኑ ተቀባይነት አግኝቶ አሜሪካ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች። ያው የቀዝቃዛው ጦርነት ውጤት ሁላችንም የምናውቀው ነው።

ህውሃት አሁን በቀድሞ የደህንነት ሰዎች ታጅቦ የእግር እሳትና የጭን ቁስል የሆነባትን ኦህዴድን ለመቋቋም ወይም ለማምከን የፕሮፌሰር ዱልን ስትራቴጅ የተዋሰች ትመስላለች።

አሁን አሰላለፉ ግልፅ ሆኗል።አሰላለፉ :-
* ከኦህድድ በኩል
ለማ መገርሳ ~ የቀድሞ ደህንነት አመራር
አቢይ አህመድ ~ የቀድሞ የኢንሳ ምክትል
አባዱላ ገመዳ~ የቀድሞ ደህንነትና መከላከያ ዘመቻ መምሪያ።
*ከህውሃት በኩል 
1~ ደብረፂዮን~ ደህንነት
2~ ፈትለወርቅ ~ የፋይናንስ ደህንነት ምክትል ሃላፊ የነበረች።
3 ጌታቸው አሰፋ

ከዚህ በኋላ Invisible የሆነ በሴራ የታጀበ የእርስ በርስ ምንጠራና ማስወገድ የታጀበ ትርኢት ልንመለከት እንችላለን። የሁለቱ ጨዋታ ደህንነት ለደህንነት ነው። ሳንጃ ለሳንጃ። ከየት እንደተተኮሰ የማይታወቅ ጥይት የታጀበ ዘመናዊ ኮሎሲየም። ገና ከጅምሩ የኦህዴድ ካድሬዎች “በከፍተኛ አመራሬ የሚፈፀም ስውር የግዲያ እርምጃ ምስራቅ አፍሪካን እሳት ላይ እንደተጣደ ድስት ያንተከትከዋልና እንዳታስቡት ” በማለት በሁለተኛው የአለም ጦርነት አውስትሪያ ሀንጋሪ የሰጠችውን አይነት Ultimatum (የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

በዚህ ሁሉ የሞቀ የፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ “ታታሪው ” ብአዴን የአህያ ፓርኪንግ ግንባታ ላይ ስለሆንኩኝ አትረብሹኝ !” እያለ ሲሆን ደኢህደን ደሞ የሚወደውን ጥሬስጋ እና እንቅልፍ እያወራረደ ነው።
Filed in: Amharic