>
3:08 pm - Thursday May 19, 2022

አቆራራጩ ጌታቸዉ ረዳ እንኳን ወደ ተፋፋመዉ እሳት በደህና መጣህ። (ሃራ አብዲ)

አቆራራጬ መጣሽ ወይ፤
አጎማማጄ መጣሽ ወይ፤
ልቀበልሽ ወይ።

«በትልቁ ልጃቸዉ ሚስት ደስተኛ ያልሆኑ እናት ትንሹ ልጃቸው ሚስት አግብቶ ሙሺራይቱን ይዞ ወደ ቤት ሲመጣ የዘፈኑት ዘፈን ነዉ በማለት» የአባቴ እናት አያቴ በልጅነቴ ያጫወቱኝ ትዝ አለኝ። ላፋቸዉም ቢሆን ህዝባችን አንድ ነዉ ማለት የጀመሩት አረመኔ የወያኔ ባለስልጣኖች ነገር እጅ እጅ በሚልበት ባሁኑ ወቅት፤ አቆራራጩ ጌታቸዉ ረዳ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ ብቅ ማለቱ አጃኢብ ያሰኛል።

አቆራራጬ መጣህ ወይ፤
አጎማማጄ መጣህ ወይ፤
ልቀበልህ ወይ።
እንዴት ልቀበልህ፤
ያን እለት ሰምቸህ፤
አጉል አጉል ነገር፤
ስትለጥፍ በህዝብህ።

ሰዉ በልቡ የሞላዉን ነዉ ባፉ የሚናገረዉ። የእግዚአብሄር ቃል እንደሚለዉ ማለት ነዉ። ምንም እንኩዋን ወያኔዎች ለይስሙላ ለዉጥ እናመጣለን፤ ለህዝብ አንድነት ለመስራት ታድሰን መጥተናል ቢሉም እነሆ በልባቸዉ የሞላዉን ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸዉን ንቀትና ጥላቻ ሊደብቁት እንደማይችሉ ጌታቸዉ ረዳን ወደ ፊተኛዉ መስመር በማምጣት አሳይተዉናል።
ይህ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ (የሚሉት ሌላ የሚያደርጉት ሌላ ) የሆነዉ የመቀሌ ስብሰባ ዉጤት የህወሃትን የማይድን በሽታ በግላጭ አዉጥቶ ጸሃይ አስመትቶታል። ጌታቸዉ ረዳ አማራና ኦሮሞ እሳትና ጭድ የሆኑ ህዝቦች እንዴት በአንድነት ሊቆሙ ይችላሉ ።ይህ የሚያሳየዉ የእኛ ስራችንን በሚገባ ያለመስራታችንን ነዉ ሲል በቁጭት ተናግሮአል። በዚያ ውይይት ላይ የህዝብ ልብ የሆነዉ አናንያ ሶሪ ደግሞ ስርአቱ እሱና እሱን ለመሰሉ ከተለያየ ማህበረሰብ ለተወለዱ ኢትዮጲያውያን/ዉያት ቦታ እንደሌለዉ አሳይቶ ከእንግዲህ ወዲህ በጥልቅ መበስበስ ካልሆነ በቀር በጥልቅ መታደስ እንደማይመጣ በመናገር የጌታቸዉ ረዳን አፍ ክፍቱን ያደረ ያልታጠበ ሸክላ ድስት አስመስሎት ነበር።
መቸም ሰዉ ያለዉን ነዉ የሚሰጠዉና ህወሃትም ከበዛዉ« መታደስ« በሁዋላ ያለዉን አጎማማጅ ሰይፍ በህዝባችን ላይ በመምዘዝ ዉረድ እንዉረድ እያለን ነዉ። ጌታቸዉ ረዳ በቅጥ አልተሰራም ያለዉን የወያኔዎች የቤት ስራ በቻለዉ ሁሉ ለመስራት ሸሚዙን በመጠቅለል ላይ የሚገኝ ይመስለኛል።

የኢትዮጵያም ህዝብ የወያኔን የዛገ ስይፍ ሰብሮ ክተጫነበት የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመዉጣት ከምን ጊዜዉም በላይ ቆረጦ ተነሰቶአል። እንዲያዉ ግርም የሚለዉ ነገር ግን እነዚህ ከህዝባችን መሃል ወጥተዉ መልሰዉ ህዝባችንን የሚወጉ ከሃዲዎች ነገ የሀፍረት ሞት እንደሚሞቱ ነገ ትዉልዳቸዉ ሁሉ በነሱ እንደሚያፍርና ነገ ታሪክ እንደሚፋረዳቸዉ የሚያሳስባቸዉ አለመሆኑ ነዉ።

እስኪ ይሀን ጌታቸዉ የሚባል ሰዉ አንድ ነገር ልጠይቀዉ። አቶ ጌታቸዉ ለመሆኑ ራያ ተወልደህ ስታድግ ኦሮሞ ጎረቤቶች ወይም የሰፈር ሰዎች ወይም ኦሮሞ አስተማሪዎች ነበሩዋችሁ? ከነበሩዋችሁስ አንዳቸዉም ኦሮሞዎች ከአማራዎች ጋር በዘር ተጣልተዉ
እሳትና ጭድ ሆነዉ አይተህ ታዉቃለህ?አይተህ የማታዉቅ ከሆነ ደግሞ የወያኔን በጎሳና በነገድ ከፋፍሎ መግዛት ከግብ ለማድረስ ብለህ እንዴት ህሊናህን ሸጠህ አማራና ኦሮሞ እሳትና ጭድ ነዉ ለማለት ድፍረት አገኘህ? አሁን ነገሮች እየጠሩ መጥተዉ የወያኔ ፖለቲካ አፈር ልሶ አማራና ኦሮሞ በመካከላቸዉ የተገነባዉን የቺፕ ዉድ ግድግዳ ንደዉ የቀደመ አንድነታቸዉን፤ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነታቸዉን ወያኔ አይኑ እያየ አረጋግጠዋል። ባሁኑ ሰአት ይህን ልጠይቅህ የፈለግሁት ከዚህ ትልቅ የህዝብ ድል በሁዋላ የወያኔ/ ህወሃት ስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነህ በመመረጥህ እያወቅህ በድፍረት ሳታዉቅ በስህተት የበደልከዉን ህዝባችንን ይቅርታ ለመጠየቅ እድሉን እንድትጠቀምበት በማለት ነዉ። ካለበለዚያ ወያኔ ሲወድቅ አወዳደቅህ የሮምን አወዳደቅ ነዉ የሚሆን።

ለማንኛዉም የወያኔዎች ታጥቦ ጭቃ መሆንና ከጌታቸዉ ረዳ የተሻለ ሰዉ ማምጣት አለመቻል አሳዛኝ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ጌታቸዉም ሆነ ህወሃት የፈለጉትን አይነት ማታለያ ቢያመጡ የአትዮጵያ ህዝብ ባርነት ይብቃ ብሎ ተማምሎ ተነስቶአል። ይልቁን ጀምበርዋ ሳትጠልቅ ህወሃት ስልጣን ይልቀቅ። ይህ እኛ ካልገዛን ኢትዮጵያ እንደተበተኑት ሀገሮች ትበተናለች እልቂት ይሆናል የሚለዉን አባባል ህወሃቶች ራሳችሁን ዝቅ ሲል ሆድ አደር ደጋፊዎቻችሁን ከፍ ሲል እናንተን በጉያዉ ይዞ አድፍጦ የሚጠባበቀዉን የትግራይን ህዝብ አስፈራሩበት። የተቀረዉ የአትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያልተጋተዉ የግፍ
ጽዋ በናንተ ያልደረሰበት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋ የለም። እስካሁን በአንደኛ ዜግነት አይተዉ
የማያዉቁትን ድሎት በመለማመድ ላይ የሚገኙትን በቁጥርም ኢምንት የሆኑትንና እልቂት ቢከሰት ለዘር መትረፍ እንኩዋን የማይችሉትን የትግራይ ተወላጆችን አስፈራሩበት!!
አቆራራጩ ጌታቸዉ ረዳ እንኩዋን ወደ ተፋፋመዉ እሳት በደህና መጣህ። ማን እሳት ማን ጭድ እንደሚሆን መለያዉ ጊዜ ተቃርቦአል።

Filed in: Amharic