>
4:34 pm - Thursday October 16, 9090

የእስራኤልን ሀገርነት መጀመሪያ እውቅና የሰጠችው ሀገር የእየሩሳሌምን ግዛት ለዋና ከተማዋነቷ መጀመሪያ እውቅና ሰጠች

ቅዱስ  (እየሩሳሌም) አስመልክቶ ማወቅ ያለብን በትላንትናው እለት የነበሩት ሁኔታዎች በመጠኑ:-

በMay 14 , 1948 ልክ ከቀኑ በ6:00 ሰዓት እንግሊዝ ቦታውን መልቀቊን አሳወቀች፤ ከ2 ደቂቃ ቡሃላ እስራኤል ሉዓላዊ ሀገር ነኝ ስትል አወጀች፤ ከ11 ደቂቃ ቡሃላ አሜሪካ ከዓለም ሀገራት ቀድማ እውቅና ሰጠቻት።

የእስራኤል እድሜ ከአያትዎ ወይም ሰፈርዎ ካሉ የዕድሜ ባለጠጋ ያነሰ መሆኑንስ ያውቃሉ?

የአሜሪካው አወዛጋቢ ፕሬዚደንት “የእስራኤልን የእየሩሳሌም ባለቤትነት እውቅና መስጠት ማለት ለእውነት እውቅና እንደመስጠት ነው” ከማለታቸው ጋር የአሜሪካንን ኤምባሲ ከቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማዘዋወር ወስነዋል።

ይህ ውሳኔ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ቃል የገባው ነገር እንደነበር ይታወሳል። ቤንጃሚን ኔታንያሆ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመጀመሪያ ግዜ አወዛጋቢው መሪ ትራምፕ መመረጡን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት ያስተላለፉ የመጀመሪያ መሪ ናቸው።

እየሩሳሌም ለክርስትያኖች

በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ክርስትያኖች እየሩሳሌም ማለት እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት፣ የተሰቀለበት እና ያረገበት ቅዱስ ስፍራ ነው። ብዙ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችም ከዚህ ቅዱስ ስፍራ በረከትን ለማግኘት እና ፀሎታቸውን ለማድረስ አይነተኛ ውሳኔ ነው።

በእየሩሳሌም ውስጥም በጥንታዊ የግሪክ ኦርቶዴክስ ጳጳሳት፣ በኢትዮጵያ ጥንታዊ የኦርቶዶክስ ጳጳሳት፣ እንዲኩም በግብፅ፣ ሶሪካ፣ አርመናውያን ኮፕቲካ ጳጳሳት የሚመራ የአምልኮ ቅዱስ ስፍራ በዚህ አካባቢ አላቸው።

ይህ የትራምፕ ውሳኔ ምናልባት የአምልኮ ስፍራውን በፅጾዮናውያን የበላይነት ካሰፈነ የአምልኮ ቦታው በአይሁዳውያን ብቻ እንዲወድቅ ያሰጋዋል።

ይህንን አስመልክተው ጳጳስ ፍራንሲስ እንዲህ ብለዋል… “የእየሩሳሌምን ቅጥር ግቢ የሚጠብቀው አካል ሊከበር ይገባል። ጆርዳን በእየሩሳሌም ለሚገኙ የክርስትያኖች እና የሙስሊሞች መኖርያዎች ሁሉ ከ1994 እ.ኤ.አ ጀምሮ ጠባቂ ነበረች።

እየሩሳሌም ለሙስሊሞች

እየሩሳሌም ለሙስሊሞች ሶስተኛዋ ቅዱስ ቦታቸው ስትሆን ነብዩ ሙሐመድ ሁሉንም ነብያት መሪ ሆነው በስግደት እንደመሯቸው ያምናሉ። ሙስሊሞች በየዓመቱ ይህንን ቅዱስ ስፍራ ይጎበኙታል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትም የዐርብ ስግደታቸውን በስፍራው ያከናውናሉ።

ይህ የትራምፕ ውሳኔ ምናልባት የአምልኮ ስፍራውን በፅዮናውያን የበላይነት ካሰፈነ በቅርቡ እስራኤል በመስኪዱ ውስጥ ካሜራ ለመግጠም ባደረገችው ሙከራ በእጅጉ የበለጠ ደም መፋሰስን ያስከትላል።

የእየሩሳሌም ጉዳይ ከፍልስጤማውያን ክርስትያኖች እና ከፍልስጤማውያን ሙስሊሞች ባለፈ የዓለም ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መረዳት ይቻላል።

ምናልባት የዓረቡ ሀገራትን ብቻ ሳይሆን ክርስትያን የአውሮፓ ሀገራትን ጭምር አንድ የሚያደርግ እና በመንፈስ የሚያስተሳስር ሁኔታን ፈጥሮ ፕሬዚደንት ትራምፕ ካቀዱበት በእጅጉ በተቃረነ መንገድ ሊሄድ እንደሚችል እና የአሜሪካንንም የአስታራቂነት ህልውና ገደል የከተተ እንደሆነ ተንታኞች ይገልፃሉ።

የአሜሪካን ምክር ቤት በ1995 እ.ኤ.አ የአሜሪካንን ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ለማዞር ጥሪ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የትራምፕ ቀዳማይ መሪዎች ግን የደህንነት ጉዳዮችን በማንሳት በየግዜው የ6 ወራት ማራዘሚያዎችን ይወስዱ ነበር።

ትራምፕም በሰኔ ሊደረግ የነበረውን ውሳኔ ስድስት ወር በመግፋት በያዝነው ሳምንት 6ኛ ወሩን አልፎ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ New York ኒው ዮርክ ጋዜጣ በእሁድ ዘገባው እንደዘገበው ሳዑዲ ዐረቢያ እና አሜሪካ እስራኤልን ሙሉ ተቆጣጣሪ እንድትሆን በማድረግ ሰላምን ሊመልሱ እንደሆነ ዘገበ።

ብዙ የአውሮፓ እና የዐረብ የዜና አውታሮች ለትራምፕ የእንጀራ ልጅ ኩሽነር የልብ ጓደኛ የሆነው የሳውዲው ልዑል ሙሐመድ ቢን ሰልማን ጉዳዩን በባለፈው ወር ለፍልስጤሙ መሪ ሙሐሙድ አባስ አቅርቦት ነበር።
ነገር ግን ሁለቱም አሜሪካም ሳውዲም ሪፖርቱን አልተቀበሉትም።

እንዴት አሜሪካ አሁን ልትወስን ቻለች???

በእንግሊዝ በፈረንጆቹ 2008 ዓመት ከሰሜን ለንደን ወደ ደቡብ ለንደን ለማዞር አውጃ ከዘጠኝ ዓመታት ቡሃላም አልተከሰተም ነበር። ከ10 ዓመታት በኋላ በ2018 እውን ሆነ።

ታዲያ ምን የተመቻቸ ነገር ትራምፕን የልብ ልብ ሰጠው???

ብዙ የፍልስጤም ዜጎች ውሳኔው የማያስገርም እና የማይደንቅ ግን ደግሞ ሊሆን ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል እንደሆነ አበክረው ተናግረዋል።

ስታር የተባለው የሊባኖስ ጋዜጣ “ምንም አላደረጉም አቶ ፕሬዚደንት፤ እየሩሳሌም የፍልስጤም ዋና ከተማ ናት!” የሚል ፅሑፍን በትዊተሩ የፊት ገፅ አስነብቧል።

ብሔራዊ የአሜሪካ ኢራናውያን ምክር ቤት መስራች የሆነው ትሪታ ፓርሲ መግለጫው “የደደብ እንቅስቃሴዎች ሁሉ እናት ነው።” ሲል ገልጿል።

እስራኤል የተባለችዋን የዐለማችንን ጨቅላ ሀገር ለመጀመሪያ ግዜ በዘጠኝ ደቂቃ ውስጥ እውቅና የሰጠችው ሀገር አሜሪካ ነበረች። አሁንም እየሩስዓሌምን ከፍልስጤም ነጥቃ ለእስራኤል እውቅና ለመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር አሁንማ አሜሪካ ነች።

ይህንን ውሳኔ የሙስሊሙ ዓለም እና የተቀሩት ሰፊው የዓለም ክፍል በፅኑ ተቃውሞታል። ትልቅ ተቃውሞ እና ብዙ ደም እንደሚያፋስስም ገልፀዋል።

ፕሬዚደንት ትራምፕ የአሜሪካንን ኤምባሲ ከቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም በማዞር አሜሪካ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና ለመስጠት የመጀመሪያዋ የዓለም ሀገር እንድትሆን ፈቅደዋል።

የእየሩሳሌም ጉዳይ የፍልስጤምና የእስራኤል የረጅም ግዜ የልብ ትርታ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። ፍልስጤማውያን ከእስራኤል የተቀሙትን መሬታቸውን ተነጥቀው ያሉ ቢሆንም ወደፊት ለሚመሰርቷት ሀገር ግን ዋና ከተማቸው እየሩሳሌም እንደምትሆን እምነት አላቸው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ የWhite House መኮንኖች የትራምፕ ውሳኔ “የነባሪው ሁኔታ እና የታሪክ እውነታን ያዘለ ነው።” እንጂ ፖለቲካዊ ዓረፍተ ሐሳብ አይደለም። የእየሩሳሌምን ፓለቲካዊን ሆነ አካላዊ የድንበር ሁኔታም አይለውጥም ብለዋል።

ፍልስጤማውያን

ፕሬዚደንት መሕሙድ አባስ በበኩላቸው…
«ውሳኔው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በእስራኤል-ፍልስጤም የሰላም ሂደት ላይ ስፖንሰር በመሆን የቆየችው አሜሪካ “የሸምጋይነት ሚናዋን ከተወች (ወደ እስራኤል ማመዘን ከጀመረች)» ቡሃላ ሀገሪቱን (በመድሏዊነቷ) የሚመጥን ውሳኔ ነው።
ይህ አስከፊ እና ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ ሁሉንም ዓይነት የሰላም ጥረቶች ገደል ይከታል። «እየሩሳሌምም የፍልስጤማውያን የዘላለም ዋና ከተማ ናት» ብለው አፅንኦት ሰጥተዋል።”

ሀማስ

የፍልስጤሙ የሀማስ ዋና ኢስማዒል ሀኒዬህ…
“የኛ ፍልስጤማውያን ህዝቦች በየትም የዓለም ቦታ ሁነው ይህንን ሴራ በዝምታ አያልፉትም! መሬታቸውን እና ቅዱስ ቦታዎቻቸውን በማስጠበቅ በኩል ያላቸው ማአማራጭም ግልፅ ነው!”

እስራኤል

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሆ የፕሬዚደንት ትራምፕ መግለጫ “ታሪካዊ አንድምታ” ያለው ሲሉ አሞካሽተውታል።
ውሳኔውንም “ጀግና እና ፍትሀዊ” ብለውታል። ሚኒስትሩ አክሎም «ውሳኔው ለሰላም አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ነው። ምክንያቱም እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጎ ያልያዘ ምንም አይነት ሰላም ሊኖር አይችልምና» ብለዋል። «ከተማዋ ለ70 ዓመታት የእስራኤል ዋና ከተማ ሆና ቆይታለች» በማለት አከለ።

የእስራኤል የትምህርት ሚኒስቴር የሆኑት ናፍታሌም ቤኔት “አሜሪካ በእየሩሳሌም አጥር ላይ ለአይሁዳውያን ህዝቦች መሠረት ተጨማሪ ግንቦችን እየገነባች ነው።” ብለው ካቆለጳጰሱት ቡሃላ ሎሎች ሀገራትም ይህንን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሙስሊሙ ዓለም
.
#ቱርክ
የቱርኩ መሪ ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን “የእየሩሳሌምን ነባራዊ ሁኔታ ማጠበቅ እጅግ አስፈላጊ እና የሙስሊሙን ዓለም ወደ አንድ ሀይል የሚያመጣ ክስተት ነው።”
.
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር የሆኑት መቭሉት ቻቩሶግለ ውሳኔውን “ሀላፊነት የጎደለው” ብለውታል።
.
በትዊተር ገፃቸውም “ውሳኔው የዓለም አቀፉን ህግ እና የተባበሩት መንግስታትን የመፍትሄ ሀሳቦች የተፃረረ ነው” ብለዋል።

#ሳዑዲዐረቢያ
የሳውዲ ዜና ጣቢያዎች እንደገለፁት ንጉስ ሰልማን ለትራምፕ በስልክ “በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት የጋራ ሀሳብ ላይ ሳይደረስ የሚታወጅ አዋጅ የሰላም ድርድሩን የሚጎዳ እና በቀጠናው ላይ ውጥረትን ይፈጥራል” ብለዋል።

#ግብፅ
አል ሲሲ “ጉዳዩን አዳዲስ ውሳኔዎችን በመወሰን ማወሳሰብ በመሀከለኛው ምስራቅ ላይ የሰላም ዕድል በሮችን ይዘጋል።”አለ።

#የዓረብ ሊግ
በቀጠናው ላይ ያልታሰበ አደጋን የሚያመጣ አደገኛ ውሳኔ ነው። ሲል ጉዳዩ ለወደፊት የአሜሪካን “ታማኝ ሸምጋይነት” ሚና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።

#ኢራን
የኢራን ከፍተኛው መሪ አያቶላህ አል ኮሂሚኒ በበኩላቸው
“እየሩሳሌምን የፅዮናውያን መናሀሪያ ከተማ ለማድረግ ማሰባቸው እጅግ ከመዛላቸው እና ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ የወሰኑት ውሳኔ ነው። እጆቻቸው የታሰሩ ሲሆኑ ያሰቡትን ማሳካት አይችሉም።” የሚል አስደንጋጭ ንግግር ተናግረዋል።

#ዮርዳኖስ
የጆርዳኑ መሪ ንጉስ አብዱላህ “ፍልስጤማውያንን በተመለከተ ሰፊ መዋቅር መዋቀር እንዳለበት እና በገዛ ሀገራቸው ላይ የተወሰነውን ውሳኔ ማንኛውንም አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት ሁሉም ሀይሎች እንዲቀናጁ ጥሪ አስተላልፏል።

#ቱኒዚያ
የቱኒዚያ የሠራተኞች ማህበር
ውሳኔው “የጦርነት አዋጅ” ነው ሲል… ሰፊ ተቃውሞንም ጠርቷል።

#ኳታር
የኳታሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሼይኽ ሙሐመድ ኢብን አብዱራሕማን “ውሳኔው ሁኔታውን የሚያባብስ እና ሰላምን ለሚሹ ሁሉ የተላለፈ የሞት ፍርድ ነው።” ብለዋል።

#ፓኪስታን
“የከተማዋን ታሪካዊ እና ህጋዊ ሁኔታ የሚቀለብሰው የአሜሪካ ውሳኔ ‘በመቃብር ጉዳይ ላይ መወሰን ነው’ ” ብላለች።

ጳጳስ #ፍራንሲስ
“ሰሞኑን በተፈጠሩት ነገሮች የተሰማኝን ጥልቅ ስሜት በዝምታ አላልፍም። የከተማይቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሁሌም የተባበሩት መንግስታት ባስቀመጠው የመፍትሄ ሀሳብ እንዲጓዝ በፅኑ አደራ እላለው።”

የተ.መ.ድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉትሬስ
“የፕሬዚደንት ትራምፕ ንግግር የእስራኤል እና የፍልስጤምን ጭላንጭል ሰላም ያጨናግፋል” ብለዋል። «እንደዚ አይነት ውሳኔዎች የሁለቱንም ወገን ያማከለ መሆን አለበት» በማለት ጨምረዋል።

#የአውሮፓህብረት
ትርጉም ወዳለው የሁለቱ ሀገራት የሰላም ሂደት መደረግ አለበት የሚል ጥሪ አስተላልፏል። “እየሩሳሌም የሁለቱም ሀገር ዋና ከተማ ለመሆኗ እና ሁለቱንም የሚያስማማ በሽምግልና አስታራቂ መንገድ መገኘት አለበት።” ብሏል።

#ፈረንሳይ
የፈንሳዩ ፕሬዚደንት አማኑኤል ማክሮን የትራምፕን ውሳኔ “ፀፃች ውሳኔ” ብሎታል። ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ጭቆናውን ለማስወገድ ጥሪ አስተላልፏል።

ቻይና እና ሩስያ 

እርምጃው የቀጠናውን ፍጥጫ የሚያባብስ እንደሆነ ገልፀዋል።

#እንግሊዝ
የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ “የእንግሊዝ መንግስት ‘በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን የማይረዳውን’ የአሜሪካንን ውሳኔ ይቃወማል።” ብለዋል። በንግግራቸውም ላይ “የእኛ የእንግለዝ ኤምባሲ በእስራኤል ቴል አቪቭ ይገኛል። ለማንቀሳቀስ ምንም አይነት እቅድ የለንም።

ምንጭ

ኢኽላስ.net

Filed in: Amharic