>
5:13 pm - Wednesday April 18, 0610

በወ/ሮ አዜብ መስፍን ላይ የተከፈተው ዘመቻና የአቶ ዓባይ ወልዱ ለምን ይነሳሉ ተቃውሞ ፓርቲውን እንዳናጋው እየተሰማ ነው:: (በወንድወሰን ተክሉ)

የህወሃት ሹም ሽር የድርጅቱን ውስጣዊ ስምምነትና አንድነት አደጋ ላይ  ጥሎታል

የገዢው ኢህአዴግ ፓርቲ አስካል የሆነው ህወሃት ከሁለት ወር ውስጣዊ ግምገማና ስብሰባ በሃላ ባለፈው ሳምንት ያደረገው የሹም ሽር እርምጃ በድርጅቱ ውስጥ እጅግ የሚፈለገውን ውስጣዊ ስምምነት፣ድርጅታዊ አንድነትን እና ጥንካሬን ይበልጥ እንደሰነጣጠቀው መሰማት ጀምራል።

ከስልጣን ከተነሱት የአቶ ዓባይ ወልዱ ደጋፊዎች በተለይም ታችኛው የካድሬ ክፍል በስራ አስፈጻሚው አካል የተወሰደውን እርምጃ ከመቃወማቸውም በላይ ግልጽ ማብራሪያ እንደጠየቁ ለትግራይ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እየገለጹ ነው።

ኢሳት በትናትና ዘገባው የአቶ ዓባይ ወልዱ ደጋፊዎች የአማራው ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሳይወርዱ አቶ ዓባይ የሚወርዱበት ምክንያት የለም የሚል አቃም በመያዛቸው ፓርቲው አቶ ገዱን ከስልጣን ለማውረድ መንቀሳቀሱን መዘገቡ ይታወቃል።

በህወሃት ካድሬ ዘንድ በታማምነታቸውና ከሙስና የጸዱ ሰው በመሆናቸው የሚታወቁት የአቶ ዓባይ ወልዱ መነሳት አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ያልተቻለበት ውሳኔ እንደሆነ በመግለጽ በፓርቲው ውስጥ ለተፈጠረው የከረረ ልዩነት ምክንያት ሆናል ሲሉ ምንጮች ይናገራሉ።

የሕወሃት ሹም ሽር መሰረቱ በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፈልና መባደን እንዲፈታ ታስቦ ቢሆንም ውሳኔው ግን ያስከተለው ለውጥ ድርጅቱን ወደ በለጠና ተካረረ መከፋፈል ደረጃ አብቅቶታል ሲሉ ምንጮቻችን ይናገራሉ።

በቀድሞዋ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የተነሳውን እራስን እና ስልጣንን የመከላከል ዘመቻን ለማክሸፍ ድርጅቱ በወ/ሮዋ ላይ መጠነ ሰፊ ስም የማጥፋትና የማጥላላት ዘመቻን በታችኛው ካድሬ ክፍል እያጣጣፈ መሆኑንም መረዳት ተችላል።

የወ/ሮ አዜብ መስፍንን የዘር ግንድ በመጥቀስ ሴቲዮዋ የአማራ ተወላጅ መሆናቸውና ብሎም የህወሃትን ምስጢራትን ለኢሳትና መሰል መገናኛ ብዙሃን የሚያቀብሉ ሰላይ ናቸው የሚለው የህወሃት ዘመቻ ድርጅቱ የገባበትን ስር የሰደደ ልዩነትና መሰነጣጠቅ የሚያሳይ ነው ያሉን ምንጮች የፕሮፖጋንዳው ዘመቻ የሴቲዮዋን ጠንካራ ዘመቻ እያደረጉ መሆንም ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

“የአቶ መለስን ያልተቀናነሳና ያልተሸራረፈ ተግባሪና አዋቂው እኔ ነኝ” በማለት አቃማቸው የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከግዙፉ የኤፈርት ሊ/ርነትና የስራ አስፈጻሚው አካልነት የተባረሩ ሳይሆን እስከ የመጋቢቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ታግደው ጉባኤው እንዲወስንባቸው የተወሰነ ቢሆንም ሴቲዮዋ የአጸፈ ዘመቻ በመክፈታቸው የተነሳ ያጋደቸው አካል ከወዲሁ ዋጋ የማሳጫ ዘመቻ ከፍቶባቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን ይናገራሉ።

Filed in: Amharic