>
5:30 pm - Sunday November 2, 0290

የትግራይ ዩንቨርስቲዎች ከሌሎች ክልል ለሄዱ ተማሪዎች አስፈሪ ሆነዋል (የሺዋስ ኣበረ ጫኔ)

<ውጣ አንት አህያ አማራ!>
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የትግሬ ተማሪዎች መፈክር!!

<በር ዘግታችሁ አታስፈጁን !!! ፤ ከቤተሠቦቻችን ቀላቅሉን!!! > ተማሪዎቹ 
……
ወንድሜ ጋር ስንደዋወል ነበር ያደርነው። ጓደኛው (የደጋ ዳሞት ልጅ) በኮብል ስቶን ተፈነካክቶ ዛሬ ጧት ሞቶ ተገኘ። ሁለት የአማራ ተማሪዎች በሽጉጥ ሲገደሉም አይቷል። ይህም የሚያሳየው የአካባቢው ማህበረሰብ የጥቃቱ ተሳታፊ መሆኑን ነው። ሱቆች ተዘጋግተዋል። አልጋ ቤቶች ተማሪ ወጥቶ እንዳያድርባቸው ከ400 ብር በላይ ሆነዋል። የተሳካላቸው ቤተክርስትያን አድረዋል። የኔ ወንድም ኮሪደር ላይ ቆሞ አደረ። ዶርምማ በፌሮ እየተገነጠለ ነው። ጥቃቱ በተለይ ኦሮሞና አማራ ብሄሮች ላይ ያነጣጠረ ነው። አጥቂዎች ትግራዮች ናቸው።
ከደህንነት ክትትል እስከ ፖሊሶች ዛቻ በትግራይ ዩንቨርስቲዎች ውጥረት መንገሱን ተማሪዎች ይናገራሉ። በትግራይ ክልል ዩንቨርስቲ ውስጥ ብዙ ፀጉረ ልውጥ የሆኑ ሰዎች ኮፍየ ያለው ሹራብ እያደረጉ ማታ ማታ መታየት ጀምረዋል። ሕዝቡ ስለታፈነ በጭቆና ስር ስላለ ምንም መናገር አይችልም ። ተማሪዎች ራሳቸውን ለመከላከል በቡድን ነው የሚንቀሳቀሱት ፣ በቡድን መንቀሳቀሳቸው ጸጉረ ልውጥ የሆኑ ደህንነቶችን የላኩ ሃይሎች አልተመቻቸውም በቡድን ራት በልተው የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ወይም የኣማራ ተማሪዎችን እራት በልተው ወደ ግቢያቸው ሲመለሱ ለምንድነው በቡድን የምትንቀሳቀሱት በሚል ፖሊሶች አስቁመው ዛቻ ዝተውባቸዋል። ግቢውን ለመተበቅ የተመደቡ ፖሊሶች ሳይቀሩ በተማሪዎቹ ላይ እየዛቱ ነው። በቡድን የሚታዩ ተማሪዎችን ለማሰር አቅደዋል። ተማሪዎች ግራ ተጋብተዋል።ተማሪው በቡደን በቡድን በመሆን ትምህርቱን እናቋርጥ ወይስ ምን እናድርግ በሚል ውይይት ጀምሯል። የትግራይ ዩንቨርስቲዎች ከሌሎች ክልል ለሄዱ ተማሪዎች አስፈሪ ሆነዋል።

* በር ዘግታችሁ አታስፈጁን !!! ፤ ከቤተሠቦቻችን ቀላቅሉን!!! >> በአዲግራት የሚፈጸመው እኩይ ተግባር አሳዛኝና አስደንጋጭ አሳፋሪም ነው። ይህ የሕወሓት አገዛዝ የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ የሆነውና የትግራይ ሕዝብን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በመለየት ተግባር ተልእኮ ላይ ያተኮረው እርጉም ደባ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል። የዘረኝነት ምንጭ የሆነው ሕወሓት የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች በትግራይ እልል እንዳይማሩ ከፈለገ በሰላም እንደገቡ በሰላም ይሸኛቸው ፣ ለሞቱት ወገኖቻችን ነብስ ይማር። አሁኑ ሰአትም የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ግቢውን ለቀው ለመውጣት ቢሞክሩም አይቻልም ተብለው መውጫ በር ላይ በመከላከያ እየተጠበቁ ነው፡፡ >>

ግቢውን ለመጠበቅ ከተመደቡ የፖሊስ አባላት ጀምሮ እስከ ደህንነት አባላት ድረስ እየዛቱ ነው። ሕዝቡ ስለታፈነ በጭቆና ስር ስላለ ምንም መናገር አይችልም የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አካላት ዝም ጭጭ ብለዋል። የብአዴን ተወካዩ ስልኩን ዘግቶ ጠፍቷል።  ገና ዛሬ ጧት 4:00 ጀምሮ ፌደራል ፖሊስ ገብቷል። እሱም ቢሆን እየወጡ ያሉትን የኦሮሞን የአማራ ተማሪዎችን ለማገት ነው።

Filed in: Amharic