>

ይድረስ ህወሓት plan B የለውም ለምትሉ (ሃብታሙ አያሌው)

ይሄ በሐርመኒ ሆቴል አዲስ አበባ እየተደረገ ያለ ምክክር ነው። “የትግራይ እና የኤርትራ ወጣቶች የምክክር መድረክ ” ተሰኝቷል። 

ወያኔወች ምጥ ሲይዛቸው ከኤርትራ ጋር እንታረቅ እያሉ ነው በዛሬው እለት ሀርሞኒ ሆቴል ስብሰባ ላይ እንደነበሩ እና ወደ አስመራ ልኡካን እንደሚልኩ ተወስኗል።  ሻዕቢያን በማስወገድ እውን እንደርገዋለን የሚሉትን በምስራቅ አፍሪካ ታላቋን ትግራይ መስርቶ ሲንጋፖር የማድረግ ዘመቻ በነሱ አሰያየም ” የምስራቅ አፍሪካ አይሁድ” በአረብ ምድር ላይ እንደ ሰለጠነችው አይሁድ መሆኑ ነው። ጥረታቸው የማይሳካ ቅዠት ቢሆንም ቀጥሏል። የንቅናቄው መሪ ሐብቶም ገብረ ስላሴ ይባላል በፎቶው ላይ በመሐል ያለው ማለት ነው።

ጀኔራል ፃድቃን ወ/ተንሳይም የስብሰባው ተካፋይ እንደነበር ሲገለፅ አስመራ የማይሞከር ነገር ነው ትግሬወች እዚያ በፀበላችሁ ችግራችሁን አራግፋችሁ ከዚያ በሗላ አናግሩን ችግር ይዛችሁብን ለመምጣት አታስቡእንዳሏቸውም ታውቋል ።

ሻዕቢያ ለወያኔ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር ማሳየቱ ለህወሓት የግር እሳትና እንቅፋት የሆነው እንዴት ነው? በሚገባ መገንዘብ ያለብን ፍሬ ነገር አለ። የህወሓት ጉጅሌዎች ተነቃቅተናል። ሻዕቢያን አውግዙ ጫወታ፤ ሻዕቢያ ጠላት ነው ጫወታ ተበልቷል።
Filed in: Amharic