>
3:08 am - Wednesday February 1, 2023

በፈጣሪ ፊት የግፉ ዋንጫ ሞልታ ልትፈስ እንደሆነ ተገንዘቡ

በላይ አ

በምንም በሉ በምን ፡ ይዋል ይደር ፡ ቀናቶች ትንሽ ይለፉ ግን ትግራይ ከፈጣሪ ትልቅ ቅጣት ይጠብቃታል ።

ራሄል ባሏን አጥታ ባለችበት ወቅት ፀንሳ ስለነበረ * የባሌን ማስረሻ አገኘሁ * ብላ ስትጽናና ሳለች ሁለት መንታ ልጆቿን ከምትረግጠው ጭቃ ጋር አብራ እንድታቦካቸው ግብፃውያን ስላስገደዷትና ይህንንም ስላደረገችው እሪ ! ብላ ወደ አምላኳ እንባዋን አነባች ፡ ወደሰማይም ይህንን እምባ ረጨችው – እርሱም አልተመለሰም ።
አምላክም ህዝቡን ፡ የእስራኤልን ህዝብ በዚህ ምክንያት አሰበ። ሙሴንም ልኮ ከዛ አወጣቸው ።
በኢትዮጵያችን መቼም ያልነበረ ግፍ በዝቷል ፡ በየቀኑ የምንሰማው ጉድ እግዚኦ ! ያሰኛል። የደም ጅረት ሀገሪቱን ከላይ እስከታች አጥለቅልቋታል።የሙት ልጆች በዝተዋል።እናቶች ሳይፈልጉ እየመከኑ ነው።
በየእስር ቤቱ የሚሰራው ግፍ ከልክ አልፏል።ሆነ ተብለው ህዝቦች በበሽታ ይመረዛሉ። የአገዳደል ጥበቡ እየረቀቀ እየመጣ ነው። ሆን ተብሎ ቅጥ ያጣ ድህነት ማህበረሰቡን እንደወረርሺኝ እንዲያጠፋው ታላቅ ስራ እየተሰራ እንዳለ በግልፅ ይታያል።በሰሜን ያገራችን ክፍል ላይ አንድን ብሄር ለማጥፋት የሚሰራው የረቀቀ ስራ ጉድ ያሰኛል ።
ሀይማኖትን ገዳማትንና አብያተክርቲያናትን ሙልጭ አድርጎ ከሀገሪቱ ለማጥፋት በታቀደው ዘመቻ ጳጳሳትና የበታቾቻቸው ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ስንሰማ የነዚህ ሰዎች አላማ ምን ያህል እሩቅ ሂያጅ እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ሙስና ለአንድ ማህበረሰብ ነቀርሳ መሆኑን ስለተገነዘቡ በኃይለኛ መርፌያቸው ሀገሪቷን የሙስና መርዝ inject አደረጓት ።ሳያውቁት ሳይሆን ሆነ ብለው በሀገሪቱ ስርዓት እንዲጠፋ አደረጉ።ልማትን አመካኝተው ህዝቡን ምንቅርቅር አደረጉት።በአዲስ አበባ ብቻ ፕላንድ የሆነ ከተማ ለመመስረት በሚል ምክንያት ስንቱ ለዓስርተ ዓመታት የኖረበትን ለቆ የበረንዳ አዳሪ እንደሆነ አስተውሉ ። ስንቶችስ ህፃናት በግሬደር ስር እንዳለቁ ልብ በሉ ።
ከትግራይ በስተቀር ሆነ ተብሎ ስርዓተ ትምህርቱ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል እንዲወድቅ ታላቅ ስራ ተሰርቷል ።
እርስ በእርስ ሊያጨራርሱን ስንት ተንኮል ሸረቡ ። ይህንንም እውን ለማድረግ ስንቱ ከነህይወቱ ገደል ተላከ ፡ ስንቱ ቤት ተዘግቶበት ከነልጁና ሚስቱ በእሳት ጋየ ፡ ስንቱስ በቆንጨራ አንገቱን አጣት ፡ ስንቱስ ለዘመናት ከኖረበት ቀዬው ያፈራውን ንብረት ጥሎ በሮ እንዲጠፋ ሆነ ?ምን ያልደረሰ አለ ? ዘርዝረን መጨረስ እንችል ይሆን ?

ይህ ሁላ መዓት በጠቅላላው ሀገር ሲፈላ ሲግም ትግራይ ተኮፍሳ ሌላውን እየታዘበች ነው። * ግንባታው በትግራይ ተጋግሏል * … ተብሎ ሲወራ ከዛ አካባቢ የሚመጣው ወሬ ትግራይ አሁንም በችግር መቀመቅ ውስጥ እንዳለች ነው የሚገልፀው።
ሀገር እንዲህ በችግር ሲቧካ ለምን ትግራውያን አያገባንም ብለው ዝም አሉ ? ትግራይ እኮ የሀገራችን የእምነት መሰረት ነበረች … ያ ህዝብ እኮ የኦርቶዶክስ እምነቱን ከማንኛውም የሀገሪቱ ህዝብ በላይ አጥብቆ የያዘ ፡ ለእምነቱ ሟች ለፍትህ መዛባትና ለበደል መንሰራፋት አንገቱን የሚሰጥ ህዝብ ነበር ። ታዲያ እኒህ ጉዶች ምን ቢግቱት ነው ዝም ያለው ብሎ ህዝባችን ሲጠይቅ የትግራውያኑ መልስ በጣም የሚያስገርም ፡ በጣም የሚያናድድ ፡ ንዴትን አሳይሎ በሳቅ የሚገድል ነው ።
አዎ ! … …ትግራይ አሁንም ከሌላው ህዝብ ብሄር በበለጠ በታላቅ ጭቆና ላይ ነች ያለችው ። ለዚህም ነው ህዝቡና ሌላው ወንድሙ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ሲቆላ ትግራውያን ዝም ያሉት ። ምንተ ዓመት ያስቃል ። የምንተ ዓመት የቤት ስራ የተባለው ምንተ ዓመት ሊያስቁን አስበው ይሆን እላለሁ አንዳንዴ ።

የነዚህ የወንበዴዎች መፍለቂያና መወለጃ ትግራይ መሆኗ ሳያንስ የህዝቡ ዝምታ የመስማማት ያህል ነው የሚታየው ።
ሌላው ቢቀር ባህርዳር ከነማ ክለብ ላይ ያንን አይነት ጥቃት በተደጋጋሚ በምድረ ትግራይ ሲደርስ ህዝቡ አጥቂዎቹ (የገዛ ህዝቡ) ላይ እርምጃ ቢወስድ ፡ ቢያወግዛቸው ፡ በተለያየ ዘዴ ቢቃወማቸው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ክብርን ባገኙ ነበር። ግን አልሆነም።
በውጪ ያለው ተማረ የሚባለው የትግራይ ወለድ ምሁር ፡ በተለይ ይህንን ነቀርሳ የሆነ ቡድን ከመመስረት ጀምሮ የተዋደቁለት የሰሩትን ታላቅ ስህተት ለመፋቅ ምን እያደረጉ ነው ብንል መልሱ ምንም ነው የሚሆነው ። በኢሳት አንድ ሁለቴ ኢንተርቪው መጠየቁና ስለዚህ ጉደኛ ድርጅት ማውራቱ ብቻ በቂ አይደለም ። ጥፋታቸውን ለመፋቅ ከዛ የበለጠ ብዙ ስራ ይጠበቅባቸው ነበር ። ይዋጉ ማለቴ አይደለም ።

ትግራይ ላይ ግፍ መሽጓል ፡ ትግራይ በዝምታዋና ከዚህ ግፍ ጋራ በመተባበሯ ከፈጣሪ እግዜአብሄር ታላቅ ቅጣትን እንደምትቀበል አትጠራጠሩ። ለትግራይ አልቅሱላት ። ፈጣሪ እግዜአብሄር ፊት የግፉ ዋንጫ ሞልታ ልትፈስ እንደሆነ ተገንዘቡ ።

Filed in: Amharic