>

ደብረ ፂዮን እና ህወሀት (መኮንን ከበደ) 

ከዚህ ቀደም በዚሁ የፌስ ቡክ ገፄ ላይ ህወሀት ራሱን ለማትረፍ በሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል በእጁ ያለውን የመከላከያና ደህንነት መዋቅር እየተጠቀመ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንደሚችል የቻለውን ያህል መግደል እንደማያቆም የጎረበጡት ሹመኞቹንም በተለያየ ዘዴ ከስሩ እንደሚያሸሽ ግርድፍ ግምቴን አስቀምጬ ነበር ።

ኦህዴድና ብአዴን በህወሀት ላይ በፈጠሩት ተፅእኖ ፓርቲው ከገባበት አጣብቂኝ አልተላቀቀም ። ዋናው ስቃዩ የሚጀምረው ደግሞ ከዚ በኋላ ነው ።  የቀድሞዎቹ መለስና ፀጋዬ ብልጠት ከተንኮል ጋር አጣምረው ማእከላዊነቱን ጠብቀው  የያዙት ህወሀት አባይ ወልዱ ጋር ሲደርስ በሙስና በጠገቡና እርስ በርስ በሚራገጡ ወያኔዎች ህወሀትን ሰንገው ሲይዟት  ሀገራችንን ቀውስ ውስጥ እንድትከርም ተገዳለች ።

አንድ ቀን የረጋ ናፍጣ በሙቀት ፈሳሽ ነዳጅ አድርጎ ስላሳየን ሳይንቲስታችን ነው ። እያሉ ወያኔያውያን የሚመፃደቁበት በንግግር ችሎታውና ግብረገብነቱም በደካማነት የሚጠቀሰው የአሁኑ የህወሀት አለቃ ደብረፂዮን ህወሀትን ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚከታት ይታመናል ። ከስድብና ማሸማቀቅ መለስ ይህ ነው የሚባል የረባ ሀሳብ የሌለው ደብሬ ተናቅን የበላይነታችንን ልናጣ ነው የሚል ምጥ ውስጥ ላሉት የታያቸው ብቸኛ ሠዋቸው ነው ። ነገር ግን በቦርድ አባልነት የሚመራው ኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞችን በተለያዪ ወቅታዊ ጉዳዮች በፕላዝማ ቲቪ ለማወያየት በጠራቸው ስብሰባዎች ሁሉ ውይይቱ የሚበተነው በደብሬ ማስፈራሪያ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ነው ። የተለየ ሀሳብ እንደስድብ ይነዝረዋል ይላሉ ቴሌዎች ። ታዲያ ለዚህ ነው ቀውሱ /እብዱ./ የሚል የቴሌ ሠራተኞችን መጠሪያ ያተረፈው ።

ህወሀት ይበድም ይቀውስም ደብሬ እንዲያከርማት ትፈልጋለች ። ከጌታቸው አሰፋ ጋር ያለውን የከረመ ፍቅር ተጠቅሞ ብአዴን እና ኦህዴድ የፈጠሩትን ግንባር ከተቻለ ንዶ ማፍረስ ካልሆነ እራሱ ኢህአዴግን ማፍረስ ግድ ሆኗል ።

የመጀመሪያዎቹ ሙከራዎች አሁን የተጀመሩ ይመስላል ።  በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባላይ ህወሀት  ዛቻ፣ ፍረጃ፣ ማስፈራራትን የመሳሰሉ አርጩሜ በሁለቱ ፓርቲ አመራሮች ጀርባ ላይ ብታሳርፍም ጠብ ያለ ነገር አልተገኘም ። ትንቅንቁ አይሎባታል ። ወደ ግድያ እና አፈና ደብሬ ያደረገው ጉዞ በለማ ጠባቂ ፖሊሶች እክል ገጥሞታል ። አሁን ዙሩ እየከረረ ነው ። ሁሉንም ከሸገር ሳይወጡ ለማፈን ህወሀት ልቧ ተመኝቷል ። ነገር ግን ከጀርባ ሚልዮኖች እፍርቷን ለማየት እስከመጨረሻው ሊቀብሯት አሉ ።

ግን የህዝብ ብሶት የወለደው የተባለለት ኢህአዴግ ባለፉት 27 አመታት እዚች ሀገር ላይ ስንት ብሶት ስንት ምሬት አስወለደን ? ህወሀት ዘራፊ መሪዎችዋን ከህግና ከህዝብ ተጠያቂነት ለማዳን በቅርቡ ሌላ እልቂት ፈፅማ ህጋዊ ትለናለች። ግን ለውጡ አይቀሬ ነው ። ዝርፊያ  ንጥቂያ ግድያና ሀገራዊ ውንብድና ላይ የተሰማራው የደብሬ ህወሀት የማታ ማታ ራሱን የሚያይበት የታሪክ መስታወት የህዝብ ጩኸት እና ሽሽት ብቻ  ነው ።

Filed in: Amharic