>

''የሚባለው ነገር ፍጹም ውሸት ነው።" (ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ)

“…. የግንቦት 7 አባል ለመሆን ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ በቂ ነው …..” 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ

ትናንት በአምስተርዳም በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ስብስባ ላይ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተሰነዘሩት ጥያቄዎች መካከል አንዱ ” አርበኞች ግንቦት 7 ከአመራሩ ውስጥ የአማራ ተወላጆች እንዳይካተቱ አድርጓል ይባላል። ይህ ለምን ሆነ?” የሚለው ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለጥያቄው የሰጡት ምላሽ እንደሚከተለው ነው: – “ሲጀመር አርበኞች ግንቦት 7 ኀብረ ብሔራዊና መሰረቱን በዜግነት እንጂ በብሔር ላይ ያዋቀረ ድርጅት አይደለም። አንድ ሰው የድርጅቱ አባልም ሆነ አመራር ለመሆን ብሔሩ ከየትም ይሁን ከየት፣ኢትዮጵያዊ መሆኑ ብቻ በቂ ነው …..”

“….ይህ እንዳለ ሆኖ ፣ይህ መሰረታዊው ነገር እንዳለ ሆኖ፣ በብሔር ተዋጽዖ እናስላ ቢባል እ ….. ለምሳሌ የአማራ ሕዝብ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ 30 በመቶውን ይሆናል ቢባል ፣ በአንድ ኀብረ -ብሔራዊ ድርጅት ውስጥ ካሉት አመራሮች 30 በመቶዎቹ አማራዎች መሆን አለባቸው። ሆኖም የተሰባሰብነው በኢትዮጵያዊነት አምነን እንጅ በብሔር ተመራርጠን ባይሆንም፣ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ 13 ሥራ አስፈፃሚዎች መካከል 8 ቱ አማራዎች ናቸው። ይህ ማለት ከአመራሩ የሚበልጡት፣ ማለትም ከግማሽ በላይ ወደ 60 በመቶ የሚሆኑት አማራዎች ናቸው ማለት ነው። ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ በአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውስጥ አማራዎች የሉም የሚለውን ሥርና ጫፍ የሌለውን አሉባልታ እነማን እንደሚያሰራጩት፣ ከምን ተነስተው እንደሚያሰራጬትና ለምን ዓላማ እንደሚያሰራጩት አይገባኝም። የሚገርመኝ ግን ውሸት መወራቱ ሳይሆን ከዚህ ከማህበራዊ ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ በብዙዎቻችን ዘንድ የአንድን ወሬ ውሸትነትና እውነትነት የማረጋገጥ ባህል ጭራሽ መጥፋቱና አንዱ ከሜዳ ተነስቶ የሆነ ነገር ሲል ያንኑ ተቀብሎ ማስተጋባቱ ልማድ እየሆነ መምጣቱ ነው። እና የሚባለው ነገር ፍጹም ውሸት ነው።”

 ደረጀ ሃ/ወልድ

Filed in: Amharic