>

"በመጨረሻ ሰዓት የምን መልቀቂያ ነው ? አብረን እንሞታታለን !!" (ዮናስ ሃጎስ)

ትናንት EBC የምሽት ዜናዎቹ ላይ አቶ አባዱላ ገመደ የስራ መልቀቂያ ተሰጣቸው እየተባለ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው የሃሰት ወሬ ነው ሲል ነበር ።

ከዚህ “ዜና” (ዜና ከተባለ) የሚከተሉትን ልብ ትላለህ ፦

አንደኛ የአቶ አባዱላ መልቀቂያ ማስገባት ስርዓቱን ምን ያህል እንዳሸበረውና ብርድ ብርድ እንዳለው ያሳበቀ “ዜና” ነው ! ሰውዬው ስርዓቱን ለመልቀቅ መጠየቃቸው ራሱ አስገራሚ ሆኖ ሳለ ተከልክለው በግድ እንዲቀጥሉ ማድረግ ደግሞ ለአንድ 26 ዓመታት ሃገሪቱን ለገዛ “መንግስት” የውርደት ውርደት ነው !! ሰውዬው ከአሁን በኋላ ከስርዓቱ ጋር ቢቀጥሉም ባይቀጥሉም በህዝብ ዘንድ የተፈጠረውን ስሜት አንዳችም አይለውጠውም ። አንድ ጓደኛዬ ስርዓቱ የአባዱላን መልቀቂያ የከለከለበት ዋንኛ ምክንያት ሌሎች ለመልቀቅ በቋፍ ያሉ ባለስልጣናት እንዳሉ በቅጡ ስለተረዳ ተሞክሮው ወደ ሌሎች ባለስልጣናት እንዳይዛመት ፈርቶ ነው ፤ ለአባዱላ የተከለከለ መልቀቂያ ለእኔ ሊሰጠኝ አይችልም ብለው አርፈው እንዲቀመጡ ለማድረግ ነው ብሎ ያምናል ። “በመጨረሻ ሰዓት የምን መልቀቂያ ነው ? አብረን እንሞታታለን !!” ማለታቸው ነው እያለ ይስቃል ።

ሁለተኛ ስርዓቱ ከአጀንዳ ሰጭነት ወደ FB አጀንዳ ተቀባይነት ማሽቆልቆሉን ትረዳለህ ። ለነገሩ ከአንድ ቴዲ አፍሮ ጋር ይዋጣልን የሚል ወራዳ ስርዓት ይሄንን ቢያደርግ ብዙ አይገርምም !! “ወያኔ ጠብ አይንቅም” ያለው ማን ነበር ? ስዩም ተሾመ ነው መሠለኝ ? እውነቱን ነው ።

አቶ አባዱላ የአቶ ታምራት ላይኔ እና የአቶ ስዬ አብራሃ አይነት ካርድ እንደማይመዘዝባቸው ምንም መተማመኛ እንደሌላቸው ከትናንቱ የ EBC ዜና ሊረዱ ይገባል ።

አቶ አባዱላ ንስሃ ገብተው “ጌታን ተቀበሉ” ሲባል ሰምቼ ነበር ፤ ንስሃቸውን ፓስተራቸው ብቻ ሳይሆን እኛም ሰምተነው ቢሆን ኖሮ ዛሬ እኛም ለመልቀቂያቸው እንታገልላቸው ነበር ። እስከዚያው ግን ስራቸው ያውጣቸው ብለናል ። ሁለንተናቸው ከትጥቅ ትግል ጀምሮ እራሳቸው ባገለገሉት እና እዚህ ባደረሱት ድርጅታቸው እጅ ነው ። In short , he is expendable for TPLF !

ቀልበህ ቀልበህ ያደለብከው ኮርማ…..

እናንተ ጨርሱት ።

Filed in: Amharic