በዋሺንግቶን ዲሲ በስሚዞኒያን የሂርሾርን ሙዚየም በታዋቂው የቻይና አርቲስት እና የሰባዊ መብት ተምሟጋች አይ ዌዌ ስም ተሰይሞ በአለም ዙሪያ ያሉ የህሊና እስረኞችን በልዩ የስነጥበብ ፈጠራ መልክ የሚያስተዋውቀውኤግዚቢሽን ከJune 2017 ጀምሮ ለጎብኝዎች ቀርቧል።የዚህ እድል ከደረሳቸው የሀገራችን የህሊና እስረኞች ውስጥ አንዱዓለም አራጌ እስክንድር ነጋ ርዕዮት ዓለሙ ውብሸት ታዬና ናትናኤል መኮንን ምስልና ታሪካቸው በኤግዚቢሽኑ ተካቷል።የኢግዚቢሽኑ የመዝጊያ ቀን ሰኞ January 1st 2017 ሲሆን በቨርጅኒያ ሜሪላንድና ዋሽንግተን የምትኖሩ ለፍትህና ለነጻነት የቆማችሁ ሁሉ ኤግዚቢሽኑ ከመዘጋቱ በፊት እሁድ December 31st በ2፡00 pm በቦታው በመገኘት በመቶ ሽህ በላይ የሚቆጠሩ የሀገራችንን የህሊና እስረኞችን ወክለዉ በዚህ እግዚቢሽን የተካተቱትን እስረኞች በመጎብኘት እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የግፍ እስራት የተሰቃዩና ዛሬ በመካከላችን የሚገኙ ጀግኖቻችንን እንድናመሰግናቸው በቦታው እንድትገኙ በአክብሮት እናሳስባለን ።
መግቢያ በነጻ ነው
ቀን፥ እሁድ ዲሰምበር 31, 2017
ሰአት፥ 2pm
ቦታ፥ Hirshhorn Museum, Independence Ave SW & 7th St SW, Washington, DC 20560
አባክዎት ይህንን መልክት ለሌሎች በማካፈል ይተባበሩ