>

ጠላት ፍለጋና ፋይዳው፦ (ዳንኤል ሺበሺ)

ኀወሓት-ኢህአዴግ እንደ ሸረሪት ማዘናጋትን፤ እንደ በረዶ ማደንዘዝን፤ እንደ ሌባ መዋሸትን፤ እንደ ተኩላ ማድባትንም ያውቅበታል፡፡ አንዴ እሥረኞችን ልንፈታላችሁ ነው ይለናል፣ ሌላ ጊዜ ግብር ቅነሣና ዕዳ ሲረዛ ላደርግላችሁ ነው ይላል፡፡ በጥልቅ ተሃዲሶ ላይ ነኝ ሲልም የሰማሁት መሰለኝ፡፡ ከሰማይ ቤታች የማንደራድረው ጉዳይ የለም ይልና አምነህ ስትገባ በመቃብሬ! ላይ ይለናል፡፡ በአስምባ በረሃ ጭጭ እምሽክ ያደርግሃል፡፡ ለንግግር በመሀል አአ የከተመውን በቅጽፈት ወደ ቃሊቲ-ቂሊንጦ ያጓግዝልሃል፡፡ ሲሸንጠው ለወጣቶቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ተመድቦላቸዋልና ኑ! ውሰዱ ይላል፡፡ ሐቁ ግን ጉም እንደመዝገን ነው፡፡

ይቀጥሉና ሙሰኞችን አሰርኩላችሁ ይለናል፤ ሐቁ ግን እንደ ብ/ጄ አባዱላ፣ አቶ በረከት ስምዖንና እንደ አዲሱ ለገሰ ገባ-ወጣ ድራማቸውን ይተውናል፡፡  አሸባሪዎችን ያዝኩላችሁ፤ ፀረ፣ፀረ፣ፀረ ገለመለ ኃይሎችን፣ አደገኞችን እንዲህና እንዲያ አደረኩ/ተደረጉ ይለናል፡፡ በተጠና መልኩ ጠላት ፍለጋ ግራ ቀኝ እያማተሩ፤ አማራ ጠላትህ ነው፣ ሻዕቢያ ደመኛችን ወዘተ ይለናል፤ ፡፡ ምክንያቱም ለእነርሱ ያለ ጠላት መኖር በራሱ ጠላት ስለሆነ፡፡ ጠላቶችን ማብዛት የእንጀራ ገመዳቸውን ማስረዘም ስለሆነ፡፡
ጠላት እንዲኖር ለምን ይፈልጋሉ ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁታውቃላችሁ?
ጠላቶቻችሁን እየተዋጋንላችሁ፤ ባላጋራችሁን እየመከትንላችሁ እያሉ ደንቁረው ለማደናቆር፤ በአገዛዛቸው ተደላድለው ለመቀጠልና አቅጣጫ ለማስቀየር ጥሩ ስልት ስለሆነ፡፡ እኔን ተክቶ ወይም እኔን ወክሎ ደመኛ ጠላቴን ዱቄት የሚያደርግ ጉልበተኛ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው? የሚል አስተሳሰብን በደካማው ላይ በማስረጽ የጠላቴን ጠላት ጡንቻ ማፈርጠም የተሻለ አማራጭ መሆኑን በግላጭ ለማሳመን ቀላል ወጪ ስለምጠይቅ፡፡
አጠቃላይ ዓላማው ለሕዝቡ ጠላቶችህ (Adversary) ናቸው በተባሉ ላይ እንዲያተኩር በማድረግ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳይነሱ ማፈን ነው፡፡ ውለን አድረን ስለ እያንዳንዷ ሐቅ ስንፈትሽ ግን አንድ ኢምንት (Atom) የለም፤ አሊያም የዘገየ ፍትህ ይሆንብናል!! ሰላም፡፡
Filed in: Amharic