>
5:13 pm - Monday April 19, 0252

የመለስ ፋዉንዴሽን ለኦሮሞዉ፣ለአማራዉ፣ለወላይታዉምኑ ነዉ?(በፈቃዱ ሞረዳ)

ወይዘሮዋ የኤፈርትን ሥልጣን (ሥልጣን ከተባለ) በራሳቸዉ ጊዜ ( በኩርፊያ) ለመልቀቅ ፈለጉ ወይስ ተባረሩ? መልቀቃቸዉ ወይም መባረራቸዉ ባልከፋ፤‹‹ ሕወሓት ኤፈርትን በዝብዞታል፡፡ እስከዛሬ ኦዲት ተደርጎ አያዉቅም፡፡ ስለዚህ ከሕወሓት ሥር ወጥቶ በትግራይ ሕዝብ መተዳደር
አለበት …የመለስ ፋዉንዴሽንም የሕወሓት ባለሥልጣናት መጠቀሚያ ስለሆነ በፌዴራል መንግሥት ሥር መተዳደር ይኖርበታል…›› የሚል አቋም ይዘዉ ሙግት ባልጀመሩ፡፡
ኤፈርትን ከሕወሓት እጅ አዉጥቶ ለትግራይ ሕዝብ መስጠትም ባልከፋ፡፡ ግን መጀመሪያ የትግራይን ሕዝብ ራሱ ከሕወሓት እጅ  ማዉጣት አይሻልም? ከፈረሱ ጋሪዉ ዓይነት እንዳይሆን፡፡
ደግሞስ የመለስ ፋዉንዴሽን ለፌደራል መንግሥት ምን ይሠራለታል? የመለስ ፋዉንዴሽን ለኦሮሞዉ፣ ለአማራዉ፣ለወላይታዉ ፣ ለሶማሉ፣ ለቤንሻንጉሉ፣ ለአፋሩ፣ለጉራጌዉ፣…ምኑ ነዉ? ሟቹ ‹‹ እንትና ለእንትና ምኑ ነዉ? ›› ያሉትን ለማስታወስ ያህል ነዉ፡፡
ያኔ የሟቹን ካልቾ የቀመሱትና በሥልጣን ተዘቅዝቀዉ የነበሩት አሁን የበቀል ተራ ደርሷቸዉ ልመጫቸዉን በወይዘሮዋ ላይ እየሰነዘሩ  ከሆነ ግፉን አቡነ ኣረጋዊ ይቁጠሩት፡፡
ለማንኛዉም የሴትዮዋ ደጋፊዎች ሰሞኑን እዚያም፣እዚህም በንዴት ቀንድ ቢያበቅሉ ምን ቸገረን?
‹‹ እሳትና ጭድ…ያርጋቸሁ›› ማለት የክፉ ሰዉ ምኞት መሆኑ ተሰማንና ‹‹ ክፉ›› ላለመባል ብለን ተዉነዉ፡፡ ግን ‹‹Fire and Fury in  TPLF of…›› ማለት እንችላለን፡፡
ይልቅ ቀልዱን ይቅርና ኩርፊያቸዉ ሳይበርድ ወይዘሮዋን ኢሳት እንዲያነጋግራቸዉ የሚያግባባቸዉ ዘመድ የለም? እኔም በአጋጣሚዉ  በሴትዮዋ የአሜሪካ ጓደኞች አግባቢነት/ደላላነት በትግራይ የወርቅ ምርት ፕሮጀክት ላይ ኢንቬስት ስለአደረጉት የእኔ ሰፈር ነጮች  እጠይቃቸዉ ይሆናል፡፡ ‹‹ እዉዪ! ›› አለ የማነ ስምኦን? የድሮ ጓደኛዬ…
Filed in: Amharic