>

አመሰግናለሁ ባህር ዳር!  (ቴዲ አፍሮ)

ከአራት አመታት በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው የሙዚቃ ድግሴ እጅግ ባመረ መልኩ ተጠናቋል ። የባህርዳር ህዝብ ወደ ከተማዋ ስገባ ካደረገልኝ አቀባበል ጀምሮ በነበረኝ ቆይታ ባሳዩኝ ፍቅርና ክብር እንዲሁም በተደረገልኝ መስተንግዶ ልቤ ተነክቷል- እወዳችዋለሁ ! የዝግጅቱ ዕለት ስቴዲየም ተገኝታችሁ የታደማችሁ በሙሉ በተለይም ደግሞ ከሩቅ አካባቢዎች ከአራቱም ማዕዘን መጥታችሁ ዝግጅቱን ለተካፈላችሁ ሁሉ ምስጋናዬና ፍቅሬ ከልብ ነው ።
የሙዚቃ ስራዎቼን ማቅረብ ከጀመርኩ ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማይገባኝን ሁሉ እንዳደረገልኝ በድጋሚ በመመስከር ሁሌም በፍፁም ታማኝነት እናንተን እንደማገለግል ሳረጋግጥ በታላቅ ኩራት ነው ።
እግዜር ያክብርልኝ !
አመሰግናለሁ ባህር ዳር !
አመሰግናለሁ ኢትዮጵያ !

Filed in: Amharic