>

ኢትዮጵያ ያለ ጥርጥር የ1966ቱ ዋዜማ ዓይነት ጊዜ ላይ ነች (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ ንጉሱ እየመጣ ያለውን የህዝብ የለውጥ ፍላጎት ስላልተረዱ ህዝቡ በሚፈልገው መጠን ለውጥ ሊያካሄዱ አልቻሉም።ስለዚህ አቢዮት ተካሄደ።ንጉሱ እና ባለስልጣኖቻቸው ተዋረዱ።
የመከላከያው እዝ ስለተበጠሰ ከኮለኔል  በታች ያሉት የመከላከያ መኮንኖች ጄነሮሎቹን በየካምፑ አሰሩአቸው።
ብቻ በአጠቃላይ የህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ እንጂ የተደራጀ ኃይል ስላልነበረ ወታደሩ ስልጣን ያዘ።
አሁን የ1966ቱ ዋዜማ ዓይነት እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው።ኢህአዲግ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በቂ ጊዜ ነበረው።ግን እየተጠቀመበት አይደለም።በአሁኑ መከላከያው ያኔ ያደረገውን እንዲያደርግ አደረጃጀቱ የሚፈቅድለት አይመስለኝም።ስለዚህ ምን ሊከተል እንደሚችል ማወቅ ከባድ ነው።የሆነው ሆኖ ኢህአዲግ መንቀርፈፉን ትቶ ቢያንስ ኢህአዲግ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ እናምጣ እያሉ ያሉትን የራሱን ኃይሎች ቢሰማ እና ለውጡን ቢመራ ለሁላችንም ጥሩ ነው።ለውጥን ለመምራት ጊዜ እና ፍጥነት እጅግ በጣም ወሳኝ ነው።

በመጨረሻ ሸገር ለኢህአዲግ በለውለታዋ ናት።ሸገር ግን ሰልፉን ከተቀላቀለች ኢህአዲግ ነገሮችን ተረጋግቶ መቆጣጠር አይችልም።ስለዚህ በኔ እይታ ኢህአዲግ ማድረግ የነበረበት ጉባዔውን ማራዘም ሳይሆን የጉባኤ ጊዜ እንኳን ባይደርስ አስቸኳይ ጉበዔ አካህዶ አመራሩን በመቀየር ህዝቡ በሚፈለገው መጠን ለውጡን ማቀጣጠል ነበረበት።አሁን ግን ኢህአዲግ የደረሰውን ጉባዔ እያራዘመ አደገኛ risk እየወሰደ ነው።የምታዩት ሰልፍ  በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የተካሄደ  ሰልፍ ነው።

Filed in: Amharic