>

እምየ ምኒልክ ዘመኑን የቀደመ መሪ ነበር (ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር)

በአምላኩ ሰማነህ

ጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር ለዘነበ ወላ እንዲ አለው; “……እምየ ምኒልክ እኔን ከትግሬ አምጥቶ አንተን ካርባምንጭ ጎትቶ አንድ የሚያደርገንን አማርኛ አስተምሮ ተግባብተን ባንድነት ምርጥ ጓደኛሞች እንድንሆን አደረገን፡ አየህ ምኒልክ የኔንም ትግሬነት ያንተንም ቦንጋነት አላጠፋብንም አንድ የምንሆንበትን የፍቅር ገመድ አስታጠቀን እንጂ፡፡” (ማስታወሻ ገጽ) …መላክ የሆነ ንጉስ ሠይጣን የሆነም መሪ የለም፡ ስህተት ግን አንዱ ላይ ይጎላል አንዱ ላይ ያንሣል፡፡ ለዚህች ሀገር እንደ ምኒልክ አብዝቶ የለፋ… ያሠለጠናት ሞቶ እንኳን የመራት የለም፡፡እሡ ዘመኑን የቀደመ መሪ ነበር፡፡Man OF THE CENTURY ብየዋለሁ የጥቁር ህዝብን ነፃነት የለኮሱ አልፈውም የነጮች የበላይነት እንደሌለ ለ አለም ማሳየት የቻሉ ድንቅ መሪ ናቸው።

“ስልኩም ተናገረ ባቡሩም በረረ
ሚኒሊክ አምላክ ነው ልቤ ጠረጠረ”
አንድነት ኃይል ነው!!!

Filed in: Amharic