አሁን አዲስ አበባ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አንዷዓለም አየለ ከወህኒ ቤት ተጠርተው “ጥፋተኛ ነን” ብለው ይቅርታ እንዲጠይቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ ባለመቀበላቸው ተመልሰው ወደ እስር ቤት ገብተዋል። እኔም መጀመሪያ ላይ እነ እስክንድር እንደሚፈቱ የሚያበስረው የራድዮ ፋናው ዜና ላይ “በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ” የሚለው ቃል ቀድሞውኑ አልተመቸኝም ነበር። እስክንድርም ሆነ አንዷዓለም ላለፉት 7 ዓመታት በስቃይ ሲያሳልፉ በተደጋጋሚ ይቅርታ ጠይቀው ይፈቱ ዘንድ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። እነርሱ ግን ለመቀበል ፈቃደኛ ስላልሆኑ ነው እስካሁን እስር ቤት ውስጥ የቆዩት። እርግጠኛ ነኝ ህወሃትም ይህ ጠፍቷት አይደለም “ይፈታሉ” ስትል ባደባባይ ያወጀችው። ምናልባት ዛሬ እንኳን ተሸንፈው ሊፈርሙ ይችላሉ በሚል ስሜት እንጅ!! … እነ እስክንድርን ሳትፈታ በመላው ኢትዮጵያ ያጎረቻቸውን እስረኞች ሁሉ ብትፈታ ደግሞ የሚቀበላት የለምና ሳትወድ በግዷ መልቀቋ አይቀርም ብዬ አምናለሁ። ለማንኛውም መጨረሻውን በቅርቡ የምናየው ይሆናል!!