>

የአማራ ሕዝብ ሆይ! ወያኔ፣ ሸአቢያ፣ ኦነግ፣ ኦሕዴድና ብአዴን ጉድ ሊሠሩህ ነው ንቃ! ንቃ! ንቃ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ወያኔ መጨረሻው የደረሰ ከመሰለው ሀገሪቱን ለተገንጣይ ቡድኖች አቀራምቶ ወደጎሬው (ትግራይ) በመግባት ከተጠያቂነት እራሱን ነጻ ማድረግ እንደሆነ ዓላማው በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል፡፡ በዚህም አስተሳሰቡ መሠረት ፍጻሜው የተቃረበ በመሰለው ቁጥር ተገንጣይ ቡድኖችን ሲያነጋግር፤ ነገሮች የተረጋጉ ሲመስለው ደግሞ ከነሱ ጋር የጀመረውን ንግግር እየተወ ሲመለስ እዚህ ደርሷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወያኔ ነገርዓለሙ አላምር ስላለው “ለማንኛውም አዘጋጅቸ ላስቀምጣቸው!” በሚል ከመጋረጃ ጀርባ ከተገንጣይ ቡድኖች ጋር ድርድር ውይይቱን ሲያጧጡፈው ሰንብቷል፡፡ ወያኔ ይፋ ባያወጣውም በሶሕዴፓ (የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) በኩል ከኦብነግ (የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር) ጋር መስማማቱ ሾልከው የወጡ ዜናዎች እያረጋገጡ ነው፡፡
ከኦነግ ጋር ደግሞ ከዚህ ቀደም አቶ አባዱላ የአፈ ጉባኤነት ሥልጣኑን በፈቃዱ መልቀቁን ባስታወቀ ማግስትና እነ አቶ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን ትወና መተወን እንደጀመሩ ይሄንን የራሱን ዓላማና ግብ ይዞ እየተተወነ የነበረውን የአቶ አባዱላንና የእነ አቶ ለማን ድራማዎች የእነ አቶ ጃዋር ቡድን ባልተለመደና ባልተጠበቀ መልኩ በዚያው ሰሞን እንደገና ተቀስቅሶ እየተደረገ የነበረውን የቄሮ ተብሎ የሚጠራውን ዐመፅ የተቀላቀለበት ተቃውሞን በመቃረን ለእነ አቶ አባዱላና ለእነ አቶ ለማ የሰጡትን ድጋፍና አጋርነት በማሳያነት በመጥቀስ እነ አቶ ለማ ተለውጠው እንኳን ከልባቸው ኢትዮጵያዊነትን ሊያቀነቅኑ ይቅርና ወያኔ በእነሱ በኩል ከእነ ጃዋርና ኦነግ ጋራ ከመጋረጃ ጀርባ መስማማቱን በዚያ ጽሑፍ ጠቁሜያቹህ ነበረ፡፡
ለዚህም ነው ኦሕዴድ ባለፈው “ለኦሮሞ ሕዝብ የሚታገሉ ሁሉ ከሀገር ውጭም ይሁን ከሀገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ወደ ሀገር ገብተው የፈለጉትን አስተሳሰባቸውን በነጻነት ማራመድ እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተግባራዊም ይገረጋል!” የሚል መግለጫ ሊያወጣ የቻለው፡፡ ኦዴግም ከኦሕዴድ ጋር ተስማምቶ እንደሚሠራ የገለጸውም ለዚህ ነው፡፡
በዚያ መሠረት ለኦነግ ሞቅ ያለ አቀባበል ለማድረግ ይመስላል በተለየ ሁኔታ መሰንበቻውን በመላ የኦሮሞ መኖሪያ ኦሮማራ እያሉ የሚጠሩትን የአማራንና የኦሮሞን ትብብርን በሚቃረን፣ በሚያሻክር፣ በሚያፈርስ መልኩ የሚከተሉት ጥላቻን የሚገልጹ እንቅስቃሴዎች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ የአማርኛ ጽሑፍ ያለባቸው የማስታወቂያ ጽሑፎች በቀይ ቀለም የኤክስ ምልክት ዘመቻ ሲደረግባቸው ሰንብቷል፡፡ “ለምን?” ተብሎ ሲጠየቅ ለዚህ የጥላቻ እርምጃ ሽፋን መስጠት የፈለጉ ወገኖች “አይ አማርኛ ስላለባቸው ሳይሆን ኤክስ የሚደረግባቸው ከኦሮምኛው አማርኛው ጎልቶ በመታየቱ ነው!” አሉ፡፡ አማርኛው ከኦሮምኛው ጎልቶ ያልታየበት ግን ኤክስ የተደረገ ማስታወቂያ ሲቀርብላቸው ደግሞ “አይ የኦሮምኛው የፊደል ስሕተት ስላለበት ነው!” በማለት የማይገናኙ ምክንያቶችን በመጥቀስ ሽፋን ለመስጠትና ለማዘናጋት ጥረት አደረጉ “እንደዚያ ከሆነ ምክንያቱ ለምን ታዲያ አማርኛ ጽሑፍ በሌለባቸው ነገር ግን የፊደል ስሕተት ባለባቸው የኦሮምኛ ማስታዎቂያዎች ላይ ኤክስ አልተደረገም?” ተብለው ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ አልነበራቸውም፡፡ ወደ ኋላ ደግሞ ጭራሽ ማስታወቂያዎቹን እየነቀሉ የመውሰድ እርምጃ እየተደረገ ነው፡፡
ይሄ ብቻ አይደለም ሌሎች የአማራንና የኦሮሞን የወንድማማችነት ግንኙነትን የሚያሻክሩ፣ ለአማራ ጥላቻን የሚያሳዩ ድርጊቶችም ተፈጽመዋል፡፡ ከደርግ ውድቀት ዋዜማና ማግስት በቁጥጥሩ ስር በነበረው የሀገሪቱ አካባቢ በሚኖሩ አማሮች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ጅምላ ጭፍጨፋ የፈጸመውንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ገና ወደፊትም እንደሚፈጅ ሲዝት የነበረውን ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ የጥፋት ኃይል የኦነግን አርማ በሰፊው የመያዝ የማውለብለብ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የኦነግ አርማ የማይታየው የማይውለበለበው ባንክ ቤት ብቻ ነው እየተባለ ነው፡፡  ኦነግ ኦሮሚያ በማለት የሚያሳየውንና እንደሚገነጥለው የሚያወራበትን ቅርጽ የያዘ ምሥል እንደመስቀል አንገቱ ላይ አስሮ የማይታይ ወጣት ከተገኘ ጥቂት ነው እየተባለ ነው፡፡ በቅርቡ ሕዝቡ ከእስር ለተፈቱት ለዶ/ር መረራ አምቦ በተደረገ የአቀባበል ዝግጅት በተስተናገዱበት መድረክ ላይ ይሄው ኦነግ ኦሮሚያ የሚለው ካርታ (ገጸ ምድር) ነበር የተሰቀለው፡፡ በተለያየ መድረክ ለተሸላሚዎች የሚበረከተው ሽልማት ይሄው የኦነግ ካርታ ሆኗል፡፡
እርግጥ ነው ከሕዝባዊው ዐመፅ ወዲህ አንዳንዴ በአንዳንድ ወጣቶች የኦነግ አርማ ሲውለበለብ መታየቱ እንግዳ ነገር አልነበረም፡፡ ይሁንና ግን የኦነግን አርማ በሰፊው መናኘቱን ጨምሮ ይሄ የሰሞኑ የተለያዩ ድርጊቶች ግን ክስተት በሚመስል መልኩ ከዚህ ቀደም በነበሩ ተቃውሞዎችና ዐመፆች ያልነበሩ ያልታዩ ነገሮች ናቸው በዘመቻ መልኩ እየተደረጉ ያሉት፡፡ ይሄ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም፡፡
በተለይ ደግሞ ሰሞኑን ከ5-9,6,2010ዓ.ም. እየተደረገ ባለው አድማ “የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይል (ፖሊስ) የአድማው አካል ሆኖ ወለቴ ላይ ከማዕከላዊ የጸጥታ ኃይል (ከፌዴራል ፖሊስ) ጋር አላሳልፍም በማለት ተፋጠጠ!” መባሉን ስንሰማ ነገሩ ታስቦበት በቅንጅት እየተሠራበት ያለ ጉዳይ ለመሆኑ የሚያሳይ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ “ኦሕዴድ የወያኔ አገልጋይ ነው፣ ትወና ነው እየተወነ ያለው ካልክ እንዴት ከሕዝቡ ተቃውሞ ጋር ተመሳጥሮ ተናቦ ይሠራል ትላለህ?” ትሉኝ ይሆናል፡፡ የሚያሳዝነኝ ነገርም ቢኖር ይሄው ቁማርና ያልታሰቡ ውጤቶች በሕዝቡ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ነው፡፡
ሕዝባዊው ዐመፁና ተቃውሞው አይሎ ተጽእኖ ማሳደር ከጀመረ በኋላ እነ ጃዋር/አነግ/ኦሕዴድ በሕዝቡ ትግል አቅም አግኝተው ወያኔን አንበርክከው ጥቅማቸውን ለማስከበር ከወያኔ ጋር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ስምምነታቸው ተግባራዊ የሚሆንበት መላ ከመመቻቸቱና ከመፈጸሙ በፊት እንደምታዩት በተደጋጋሚ ሕዝቡ በአንዳንድ ነገሮች በተበሳጩ ቄሮዎች እየተገፋፋ ከነጃዋር/ኦነግ እና ከኦሕዴድ/ወያኔ ፍላጎት ውጭ በራሱ ስሜት እየተነሣሣ ሲያምፅ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ማለቁ ነው የሚያሳዝነው ነገር፡፡
እነ ኦሕዴድ/ኦነግና የእነ ጃዋር ቡድንም ከወያኔ ጋር እንደመስማማታቸው ከነሱ ፍላጎት ፈቃድና ቅስቀሳ ውጭ ሕዝቡ በራሱ ተነሣሽነት ዐመፅና ተቃውሞ ማድረጉን ባይፈልጉትም ከሕዝቡ ላለመነጠል ሲሉ ሳይወዱ በግድ ከሕዝቡ ጎን ለመቆም ሲገደዱ ተስተውሏል፣ ወያኔም ስምምነቱ ተፈጽሞ ጥቅሙን ከማስጠበቁ በፊት ሁኔታው ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ ባላሰበውና አደጋ ላይ በሚጥለው መንገድ እንዳይሔድ ለማድረግ ሲል ለመግደልና ሕዝቡን ከዐመፁ እንዲመለስ ለማድረግ ሲገደድ በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡ ይሄው ነው እንግዲህ በቁማሩ መሀል ያለው ጉዳይ፡፡
አሁን ጥያቄው ከላይ የጠቀስኳቸው የጥላቻ ድርጊቶች ቄሮማራ የሚባለው የአጋርነት፣ የወዳጅነት፣ የትብብርና የወንድማማችነት ግንኙነት ባዶ ፕሮፖጋንዳ (ልፈፋ) ካልሆነና በኦሮሞ ወጣቶችና ልኂቃን በኩል በትክክል መሬት ላይ ያለ እየሠራም የሚገኝ ግንኙነት ከሆነ ምነው ታዲያ ኦሮሞ ወገኖቻችን ይሄ እያደረጋቹህት ያለው ሁሉ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት አጋራቹህን ወንድማቹህን አማራውን ሊያስቀይም፣ ሊያስከፋ፣ ግንኙነታችንን ሊያሻክር፣ ሊያበላሽ እንደሚችል መገንዘብ ተሳናችሁ???
ነው ወይስ የአማራን አጋርነት የምትፈልጉት የነበረው ወያኔ “ከአማራ ጋር አንድ ሆናቹህ ከምትነሡብኝ በቃ እሽ ያላቹህኝን ሁሉ አደርጋለሁ!” ብሎ እንዲያደርግላቹህ የምትፈልጉትን እስኪያደርግላቹህ ድረስ አጋርነቱን ጫና ለማሳደሪያና የራሳቹህን ጥቅም ለማስከበሪያነት ብቻ ነበር ማለት ነው የምትፈልጉት??? “የኦሮሞ ሕዝብን መብት ለማስከበር እንታገላለን!” የሚሉ እናንተም ስትደግፏቸው የታያቹህባቸው ሌሎች አማራጮች እያሏቹህ እንዴት የተበላሸ፣ የጠለሸ፣ የጎደፈ፣ በንጹሐን ደም የረከሰ ስምና ማንነት ያለውን አረመኔ የጥፋት ኃይል ኦነግን ልትደግፉ፣ ልትፈልጉ፣ ልትናፍቁ ቻላቹህ??? እነኝህ ድርጊቶቻቹህ ለአማራ ሕዝብ ምን ዓይነት መልእክት የሚያስተላልፉ ይመስላቹሀል??? ነገሩ አንዴ የተሳሳተ አቅጣጫ ከያዘ በኋላ መመለስ የሚቻል ይመስላቹሀል ወይ???
አዎ እውነት ነው! የኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ በዚህ ድርጊት ተባባሪ አይደለም፡፡ በመቶኛ እናስላው ከተባለ ይሄ ስሕተት እየፈጸመ ያለው ሠላሳ በመቶም ላይሆን ይችላል፡፡ ይሁንና በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ወሳኙና ነገሮችን በፈለገው መንገድ እንዲሔድ ማድረግ የሚችለው መድረኩን የያዘው የልኂቃኑ ክፍል ነው እንጅ ሕዝብ ባለመሆኑ ሕዝቡ በዚህ ጉዳይ ላይ አለመካተቱ ለዚህ ወቅታዊ ችግር የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ ልኂቅ (ኤሊት) የሚባለው ክፍል ደግሞ ከወጣቱ እስከ ዐዋቂው ድረስ በኦነግ ርዕዮተዓለም ተጠምቆ በግልጽም ሆነ በስውር ምን ዓይነት የጥፋት ዓላማ እያራመደ እንዳለ በግልጽ  የምናየው ጉዳይ ነው፡፡
እንግዲህ ወያኔና ግብረአበሮቹ ይሄንን ያህል ከዶለቱና ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ከወያኔና ግብረአበሮቹ አስተሳሰብና ፍላጎት ውጭ የሆነው አማራ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን እያደረገ ነው? የሚለው የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ወያኔ ለአማራ የደገሰለት ብአዴን እጅና እግሩን እንዲያስርለት አድርጎ ለእርድ እንዲያቀርብለት ማድረግ እንደሆነ በግልጽ እያያቹህት ነው፡፡ ከአማራ ውጭ ያለው አፍቃሬ አንድነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በየብሔረሰቡ ወያኔ ባዘጋጀለት አጋር ድርጅቶቹ ቁጥጥር ስር ያለና እንወክልሀለን የሚሉትን የወያኔ አጋር ድርጅቶቻቸውን አስተሳሰብ የማይፈልግ ቢሆንም ወያኔንና አጋሮቹን “አልችላቸውምና ምንም ማድረግ አልችልም!” ብሎ በዝምታ ያለና ለሚፈልገው፣ ለሚናፍቀው፣ ለሚመኘው አንድነት በድፍረት ወጥቶ እየታገለ፣ ዋጋም እየከፈለ፣ እየተጋፈጠ ስላልሆነና መድረኩን ለጠባቦቹ ዘውገኞች ስለተወው ጠባብነትንና ዘውገኝነትን በወያኔ በተጠመቁ ዘውገኞቹ ተውጦ ታፍኖ የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አማራ ያለ አጋር ብቻውን ተጋልጦ ይገኛል፡፡ እንኳን ኢትዮጵያን እራሱን እንኳ ማዳን በማይችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡
አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ ከአማራ ውጭ ያለው አንድነትን አፍቃሪው ሕዝብ እራሱን አግልሎ በዝምታ መዋጡ መድረኩ ላይ በብቸኝነት ጎልቶ የሚሰማው ጫጫታ የዘውገኞቹና ጠባቦቹ ብቻ እንዲሆንና የሚከተላቸው ቁጥር እያሻቀበ እንዲሔድ በማድረግ ሁኔታው እየተባባሰ እንዲመጣ አሉታዊ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ነው፡፡ ይህ በዝምታ በታዛቢነት ያለው አፍቃሬ አንድነት ሕዝብ ባዶ የአንድነት ምኞትና ፍላጎት ምንም ሊለውጥ እንደማይችል ተረድቶ ወጥቶ ካልተጋፈጠና መክፈል ያለበትን ዋጋ ካልከፈለ በዚህ 27ዓመት ከባድ ጉዳት የደረሰበት የሀገርና የሕዝብ አንድነት እስከወዲያኛው መፈራረሱ አይቀሬ መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ ነበረበት፡፡ አያውቅም ማለት ደግሞ በጣም የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ካወቀ ታዲያ ለምን ነገሩን በዝምታና በታዛቢነት መመልከትን መረጠ???
ከአማራ ውጭ ያለው አፍቃሬ አንድነት ሕዝብ እንወክልሀለን በሚሉት በጣብ ዘውገኛ ቡድኖች በመሸበቡ በብቸኝነት ተጋፍጦ አደጋ የተጋረጠበት የአማራ ሕዝብ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ካላቸውን አደገኛና አረመኔያዊ የጥፋት ዓላማ አኳያ አደጋውን ተረድቶ በማንነቱ መደራጀትና ህልውናውን መታደግ አጥብቆ ቢፈልግም አምላክ ይይለትና ከፊሉ የአማራ ልኂቅ ክፍል ፍጹም ኃላፊነት በጎደለው ንዝላልነትና ግለኝነት ታንቆ፣ ዋጋ ላለመክፈል እራሱን አሸሽቶ፣ ለመደራጀት የፈቀደውም በሰርጎ ገብ የወያኔ ካድሬዎች (ወስዋሾች) ሴራ ተንበርክኮ አማራ የተጋፈጠውን ጊዜ የማይሰጥ አደጋ መገንዘብ መረዳት ተስኖት ከአማራ ሕዝብ ሥነልቡናና ማንነት ጋር የሚጣጣም፣ በመላ የአማራ ሕዝብ ተቀባይነትና ድጋፍ ያለው አንድ ጠንካራ የአማራ ሕዝብ ድርጅት መመሥረትና ሕዝቡን ቶሎ ማቀፍ ተስኖት ይሄው በግላጭ ሊያስበሉት ከደገሉ ጫፍ አቁመው ትተውታል፡፡
የሚበዛው የአማራ ልኂቅ ደግሞ መሬት ላይ አርፎ ሊሠራ ሳይችል ቀርቶ በሌሎቹ የተተፋውን የተጣለውን ሁሉን አቀፍ የአንድነት ትግልን ዛሬም አንቆ ይዞ በመንገታገት ተገንጣይነትን በይፋ የሚያቀነቅኑትን በፀረ ኢትዮጵያና በፀረ አማራ ስሜት እንደሰከሩና እንዳበዱ በግልጽ ከሚታዩ ጠባብ ዘውገኛ የጥፋት ኃይሎች ጋር “ተጣምረን፣ ኅብረት አንድነት ፈጥረን፣ ለአንዲት ኢትዮጵያ እንታገል?” እያለ በመንከርፈፍ እራሱን ሲያጃጅልና ሲያቄል የሚውል በዓይኑ የሚያየውን እውነት መገንዘብ የተሳነው የዘገምተኛ መንጋ ነው፡፡
የነኝህ ባለበት ከቆመ ዘመናትን ያሳለፈው፣ በዘውገኞቹና ጠባቦቹ ላይ መርሕ ላይ የተመሠረተ ቆራጥ አቋምን መያዝ ያልቻለውና ጭራሽም ለጠባቦቹ ድጋፍ ሆኖ የዘለቀው የዘገምተኞች አቋምና ሞገስ አልባ እንቅስቃሴም እያደር ለጠባብ ዘውገኛ ተገንጣይ ቡድኖች ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ሲመጣ ለአንድነት ኃይሉ ግን ጊዜው እየከፋበት እንዲመጣ አድርጓል፡፡ መርሕ አልባ የጅል ሥራቸው ይሄንን ውጤት እንዳስመዘገበ በዓይናቸው በብረቱ እያዩት አሁንም ፈጽሞ ሊነቁ አለመቻላቸው ነው አስደናቂው ነገር፡፡
ወያኔ የሚምረው መስሎት “እኔን አይንኩኝ እንጅ የአማራን ሕዝብ እንደፈለጋቸው ያድርጉት!” ብሎ ተስማምቶ በወገኑ ላይ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀሎች በየአቅጣጫው እየተፈጸመ እያየ ተመሳስሎ የሚኖረው ወይም የወያኔ አገልጋይ ሆኖ የሚኖረው የአማራ ልኂቅ ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡ ከነአካቴው ማንነቱን ቀይሮ ወይም አማራነቱን ክዶ የሚኖርም አለ፡፡
ይሄ ሁሉ ተደማምሮ የአማራን ህልውና ለከባድና አደገኛ ሁኔታ አጋልጦታል፡፡ የአማራ ልኂቃን ሆይ! ኧረ እባካቹህ እንጥፍጣፊ ጊዜ ነው የቀረን ሳንበላ ንቁ??? የፈለጋቹህትን ያህል ብትደክሙ፣ ሽህ ዓመት እንኳ መኖር ብትችሉ እንደ ኦነግ ያለን የጥፋት ኃይል ለምንና እንዴት አፍቃሬ ኢትዮጵያና አንድነት ማድረግ ፈጽሞ እንደማይቻል እኮ ሳይንሳዊ ትንታኔ በመስጠት ደጋግሜ አስረዳን እኮ አይደለም እንዴ??? እስኪ ከፊሎቹን ልጋብዛቹህና እነኝህን ጽሑፎች (ሀ.) ኦነግና ኦነጋውያን ወያኔና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች ተፈጥሯዊ የተጠያቂነት ቁመና አላቸውን? (ለ.) የኦሮሞ ፖለቲከኞች ድብቅ ኦነግነትና ኢፍትሐዊ ጥያቄዎቻቸው! (ሐ.) ለኦነግና ኦነጋውያን የወያኔን ዓላማ አንግቦ ወያኔን ለመውጋት የእንተባበር ጥሪ አይሠራም! (መ.)  ኦሮምኛ ከአማርኛ በተጨማሪ የሥራ ቋንቋ ሊሆን ይገባል ወይ? በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የቡድንና የግለሰብ መብት እንዴት ይጠበቃል?
የሚሉትን ጽሑፎች አንብቧቸው ሊንኮቻቸው (ይዞቻቸው) እነሆ፦
ወይ እነኝህ ጽሑፎች የያዟቸውን ሀቆች፣ አመክንዮዎች፣ ትንታኔዎች መሞገትና ያልታየ መንገድ ካለ ያንን ማሳየት አልቻላቹህ!!! ዝም ብላቹህ በደመነፍስ መጃጃላቹህ አሁን እያያቹህት እንዳላቹህት ኦነግ የኦሮሞ ወጣቶችን እያጠቃለለ እንዲወስድና የኦነግ አርማ በይፋ የሚውለበለብባት ሀገር እንዲያገኝ ነው አስቻላቹህት፣ የወያኔ ቅጥቅጦች የየብሔረሰቡ ጠባብ ዘውገኛ ቡድኖች ሕዝባዊ መሠረት እንዲያገኙ ነው እያስቻላቹሀቸው ያለው፡፡ ጭራሽ እንዲያውም ከዚህም አልፎ ለአማራ ሕዝብ እንሞታለን የሚሉትም ጭምር ቀንደኛ የኦነግ ደጋፊ እንዲሆኑለት ነው ያስቻላቹህት፡፡
በቀደምለት ሁለት የኦሮሞ ተወላጅ ሯጮች በዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ላይ ሩጫቸውን ሲፈጽሙ የኦነግን አርማ አውለብልበው እንደተከናነቡ የሚያሳይ ፎቶ (ምስለ አካል) ለጥፌ “እጅግ ያሳዝናል እዚህ ደረጃ ተደርሷል!” በማለት ነገሩ አግባብ እንዳልሆነ የምታመለክት አጭር ሐሳብ አስፍሬ ነበረ፡፡ የኦነግ ደጋፊ የኦሮሞ ተወላጆች ግስላ ሆነው መብታቸው እንደሆነ ስድብና ዘለፋ የተቀላቀለበት አስተያየት አሰፈሩ፡፡ የነዚህን የኦነግ ደጋፊ የኦሮሞ ተወላጆች ጽንፈኛ አስተያየት በመደገፍም ቤተ አማራ ነን ባዮቹ መብታቸው እንደሆነ እየገለጹ የድጋፍ አስተያየታቸውን በመስጠት ሽንጣቸውን ገትረው ተከራከሩ፡፡ እኔም የመንግሥታቱ ድርጅትን ጨምሮ የየትኛውም ሀገር ሕግ ቢሆን የዘር ማጥፋትን ያህል አደገኛ ወንጀል የፈጸመን የጥፋት ኃይል መደገፍ ወንጀል ነው ይላል እንጅ መብት ነው የሚል አንድም ሕግ እንደሌለ ገለጽኩ፡፡ በኋላ ላይ ሳጣራ ቤተ አማራ ነን ባዩ ቡድን በአቋም ደረጃ ሳይቀር የያዘው አስተሳሰብ እንደሆነ ሰማሁ፡፡
ይታያቹህ! “በአማራ ላይ በግፍ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ተፈጽሟል፣ አማራ ከምድረገጽ ሊጠፋ ነው ህልውናውን ለመታደግ ተደራጅቻለሁ!” የሚል ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት የጅምላ ፍጅት ለፈጸመውና እስከቅርብ ጊዜ ድረስ መደበኛ ባልሆኑ መድረኮች ላይ ወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ በአማራ ሕዝብ ላይ እንደሚፈጽም ለሚዝት የአረመኔዎች የጥፋት ኃይል ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍ እንዲሰጠው መሥራት መደገፍ ማለት ምን ማለት ነው??? ኦነግ በኦሮሞ ሕዝብ ተደግፎ ጉልበትና አቅም አግኝቶ እንደሚዝተው የአማራን ሕዝብ እንዲፈጅ ነው ወይ ፍላጎታቸውና ምኞታቸው??? ይሄ ምን ያሳያል? ቤተ አማራ የሚባለው ቡድን ፀረ አማራ እንጅ ለአማራ ህልውና የሚታገል አለመሆኑን ቁልጭ አድርጎ አያሳይም ወይ??? እኔ ይሄ ቡድን የወያኔ ካድሬ (ወስዋሽ) የተጠራቀመበት ቡድን ብቻ ይመስለኝ ነበረ፡፡ ለካ የኦነግ ካድሬዎችም የሞሉበት ፀረ አማራ ፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ቡድንም ኖሯል ለካ፡፡ አየ አማራ! አየ ወገኔ! ኦነግ እንኳ ነቅቶ፣ ብልጥ ሆኖ እንዲህ ይቀልድብን??? ኧረ እባካቹህ እንንቃ??? መቸ ነው ነቅተንና እውነታውን ተገንዝበን ሆ! ብለን ለማንነታችን፣ ለህልውናችንና ለሀገራችን የምንነሣው??? የግድ እንደ ሕዝበ እስራኤል ከርስታችን ተነቅለን በዓለም መበተንና በባዕዳን ሀገራት በአሰቃቂ መከራ ውስጥ ማለፍ አለብን ወይ??? አይሁዶችስ የጠንካራ መንግሥታትን ድጋፍ አግኝተው እንደገና በሀገራቸው ለመሰብሰብና ሀገራቸውን ለማቆም ቻሉ፡፡ አንተ ግን ይሄንን ዕድል ማግኘትና ከጠፋህበት እንደገና መነሣት የምትችል ይመስልሀል ወይ??? ኧረ ተው! ኧረ ተው! ወገኔ ተበላህ ንቃ!!! ከዚህ በላይ ምን ብታይ ነው የምትነቃው???
አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ በቅርቡ “ወያኔ አለቀለት! ከዚህ በኋላ መንግሥት አይደለም….!” የሚል ቃለምልልስ ከሰጠ በኋላ እንደገና ደሞ በሳምንት ልዩነት ለ2ኛ ጊዜ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ አስቀድሞ ከተናገረው በሚቃረን መልኩ ምን እንዳለ አልሰማቹህም? “ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተስማምተን መሥራት እንፈልጋለን! ከዚያ በፊት ግን አሁን ሀገሪቱን እያወከ ያለው ችግር መፈታት ይኖርበታል!” ማለቱን አልሰማቹህም? ምን ማለቱስ እንደሆነ አልገባቹህም???
ወያኔ ባድሜንና ሌላም የሚፈልገው ነገር ካለ በመስጠት ለመታረቅ በቅርቡ ሸአቢያን በወተወተ ጊዜ ሸአቢያ ወያኔን ኦነግ ኦብነግና ሌሎች ተገንጣይ ቡድኖችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ጫና ማሳደሩንና ይሄ ከሆነ እንደሚስማማ ከወያኔ ጋር መስማማቱን እኮነው የሚያሳየው እነእንከፎ!!! ግ7 ከደምሕት ጋር የአማራን ትግር በመቃረን እንዲቆም የተደረገው እኮ ለዚህ ነው፡፡
ኦሕዴድ ኦነግን ጨምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ እንታገላለን ለሚሉ ሁሉ በነጻነት የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር መወሰኑን ማወጁን፣ ሶሕዴፓም ከኦብነግ ጋር መስማማቱን ያዙና ሸአቢያ ከወያኔ ጋር በእነ ኦነግና ኦብነግ ሀገር ውስጥ መግባትና መሥራት መስማማቱን መዶለቱን አይደለም ወይ የሚያሳየው እነ እንከፎ???
ወያኔ “በእነ አሜሪካ ተገድጀ ተቃዋሚዎችን ሀገር ውስጥ በማስገባት ከነሱ ጋር ተስማምቸ ለመሥራት መስማማቴ ካልቀረልኝ ሸአቢያን መልሸ ወዳጀ ለማድረግ በሚያስችለኝ መንገድ ላስኪደው!” ብሎ ነው ይሄንን የሸአቢያን የመደራደሪያ ነጥብ የተቀበለው፡፡ ከዚያስ ምን ይፈጠራል? ከዚያማ መከረኛውን የነዚህ ሁሉ ኢላማ የሆነው የአማራን ሕዝብ ቀቅለው ሲበሉት በዓይንህ በብረቱ ታያለሃ! ይሄ ምን ጥያቄ አለሁ??? ኧረ እባክህ? እባክህ? እባክህ? ወገኔ ሆይ ንቃ!!! ከመቀደምህ በፊት ፈጥነህ ቅደም!!! ቆርጠህ ጨክነህ ከመጋፈጥ ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለህምና ፈጥነህ በመደራጀት ተነሣ!!! በአንድነት ቁም!!!!!!!……
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic