>

ተጠቅላይ ሚንስትር ስልጣኔን እለቃለሁ ካሉ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰጡ አዝናኝ አስተያየቶችን በጥቂቱ...

*እኛ ከሞተሩ እንጂ ከካምቢዮ ጉዳይ የለንም::

*የስራ ልምድ ይፅፉላቸው ይሆን እንዴ?
*ስራ አጥ በበዛበት ሀገር ስራ መልቀቅ አይከብድም?
*ሀይለማርያም ሸሸ ወይስ አፈገፈገ?
*ሙጋቤ፣ዙማ አሁን ሀይልሽ…ምነው ግን የደቡብ ሰው ላይ አመቱ በረታ?
*ወይ ወርቅ በሰፌድ አበጥሮን ሄደ:
*ስልጣን ፈልገው ነው የለቀቁት የሚሉ ጭምጭምታዎች አሉ:
*ጠቅላዮቹም እባካችሁ አፍጥኑት::
*መንግስት ምህረት አደረገላቸው::
*እኔ ደግሞ ከረባታቸውን ሳይ እንኳን ለቫላንታይን ቀን አደረሳችሁ የሚሉ መስሎኝ ነበረ፡፡
*ምን አይነት ቀዳማዊ እመቤት ትመጣ ይሆን?
*አንድ ሰው እንኳን ተው አትሂድብን የሚል ይጥፋ?
*ኢህአዴግ አስሬ ሲንግል መልቀቁን ትቶ ምናለ ሙሉ አልበሙን አንዴ ቢለቅልን፡፡
*መጀመርያ ህዝቡን ወርቅ ታፍሳላችሁ ብለው ሰፌድ ያስገዙበትን ገንዘብ ይመልሱ፡፡
*ጃኮብ ዙማ ለቀቀ ሀይለማርያም ተለቀቀ፡
*የዕረፍት ጊዜዎትን ማዕከላዊ ሙዚየምን በመጎብኘት ያሳልፉ፡፡
*ወርቅ በሰፌድ ያስበጠርከን ጀግና መሪያችን እናመሰግናለን፡፡
*በከፍታ ዘመን ከፍ ያለ ውሳኔ፡፡
*የኢትዮጵያ ህዝብ “ሀይለማርያም ከስልጣን ይውረድ” የሚል ጥያቄ አልጠየቀም።የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ህዝብ ነው። ያልያዝከውን ልቀቅ አይልህም፡፡
*ለቀጣዩ መሪ ሰለሜ ሰለሜን አለማምደው ይሂዱ፡፡
*በፍፁም አይሆንም ለፅዳት የተገዛሎት መጥረጊያ እንኳን ሳያልቅ?
*ለፖሊሶች ትዕግስት ስላስተማሩልን እናመሰግናለን፡፡
*እንቅልፋም ፓርላማ ላይ ከማውራት ተገላገሉ፡፡
*ጥያቄውን ተቀብለናል ግን ‘ጠቅላይ’ ነበሩ እንዴ?
*በሉ ሲቪ ይዘው ስራ ይፈልጉ፡፡
*ከአሁኑ ናፈቁኝ በተለይ “የተከበራችሁ” የምትለዋ ቃል፡፡
*ያልነበረው ሰውዬ ልሄድ ነው አለ፡፡

Filed in: Amharic