ፖለቲካ ሆይ ነፍስህን አይማረዉ!!!
በላቸው ሀይሌ
~የብአዴን አመራሮችንና የመከላከያ ኢታማዦርሹምን በሴራና እርስበርስ የተጫረስንበት ኢትዮጵያ!
~ እምነትን ጠብቃ፣ ታሪክን አቆይታ፣ፊደል ቀርጻ ሀገር ያቆየች ኦርቶዶክስን ለመሰንጠቅ መንግስት የሚያሴርባት ኢትዮጵያ!
~23 ባንክ በጠራራ ፀሐይ በመሀል ከተሞች ዝርፊያ የተከናወነባት ኢትዮጵያ!
~ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅል መንጋ ያየንባት ኢትዮጵያ!
~ትም/ሚ/ር የዘቀጠ ውሳኔ ያሳለፈባት ኢትዮጵያ!
~ዘረኝነት የነገሰባት ኢትዮጵያ!
~ሰላማዊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በጠመንጃ የሚበትንና የፈላ ውሃ በሰው ላይ የሚደፋ ትውልድ ያየንባት ኢትዮጵያ!
~በአጣዬና በከሚሴ እንዲሁም በሲዳማ የበርካታ ዜጎች ህይወት የጠፋባት ኢትዮጵያ!
~ ሌላው ሞቶ፣ተፈናቅሎ፣ ተሰዶ እኛ (ኬኛ) ብቻ ሁሉን እናጋብሰው የሚል ስግብግብ ትውልድ የፈላባት ኢትዮጵያ!
~የጋራ ነገሮቻችን እየጠፉ ዘረኝነት የነገሰባት ኢትዮጵያ!
~ፍ/ቤት የሚፈልጋቸው እነጌታቸው አሰፋን አሳልፌ አልሰጥም በማለት የፌደራል መንግስትን አቅም የሚፈታተን የክልል ስልጣን ያየባት ኢትዮጵያ!
~ መንግስት የአዋሳን የክልልነት ጥያቄ ጉሮሮውን ታንቆ ለመመለስ ቀን የቆረጠባት ኢትዮጵያ!
– ወጣቱ በስደት ባህር ላይ ሠምጦ የሚቀርባት ኢትዮጵያ
– ወጣቱ በአደባባይ ድምፁን ሲያሠማ በጥይት የሚመታበት ሀገር ኢትዮጵያ ፡
– ህዝብ መሪዉን /ገዥዉን መርጦ የማያዉቅባት ኢትዮጵያ
– የሰው ልጅ በድንጋይ ተወግሮ የሚገደልባት ኢትዮጵያ!
~ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ያሰማ ወጣት በጠራራ ፀሀይ በጥይት የሚረሸኑባት ኢትዮጵያ
~ “መጤ” እያሉ ወግረው የገደሉት ሰው ሬሳው እንኳ ቦታ እንዳይዝባቸው በእሳት የሚያቃጥሉባት ኢትዮጵያ!
– በዘር በቀለምና በቋንቋ የምትተራመስ ሀገር ኢትዮጵያ
– መንግስትና ተፎካካሪ ፖርቲወች ሆድና ጀርባ የሆኑባት ሀገር ኢትዮጵያ
– ንፁህ የመጠጥ ዉሀ የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
– መብራት በፈረቃ የሆነባት ሀገር ኢትዮጵያ
– የኔት ወርክ ችግር ቅንቅኑን ያራገፈባት ሀገር ኢትዮጵያ
– በብድር እዳ ተስፈኛ የሆነች ሀገር ኢትዮጵያ
– የወላጆች ማዋለጃ ጤና ጣቢያ ያልተሟላበት ሀገር ኢትዮጵያ
-,ህፃናት የሚራቡባት ሀገር ኢትዮጵያ
– የትምህርት ጥራት የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
– በበሬ ጫንቃ በእርሻ የምታመርት ሀገር ኢትዮጵያ
– ቤተክርስቲያንና አባቶች የሚቃጠሉባት ሀገር ኢትዮጵያ
– ጉቦ በገሀድ የሚፈፀምባት ሀገር ኢትዮጵያ
– አንድነቷ የሚያሰጋት ሀገር ኢትዮጵያ
– ዜጎች ወጥቶ በሠላም የመግባት ዋስትና የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
– የኑሮ ዉድነት ጣራ የወጣባት ሀገር ኢትዮጵያ
– የተረጋጋ መንግስት የሌለባት ሀገር ኢትዮጵያ
– ሥራ አጥነት ከፍ የአለባት ሀገር ኢትዮጵያ
– ዜጎቿ ሠብስቦ መመገብ የማይችል መንግስት ያለባት ሀገር ኢትዮጵያ
-ታክሲ በወረፋ ፡ ዘይት በቀበሌ የሚታደልባት ሀገር ኢትዮጵያ
እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉትን ኩነቶች ያስተናገደ መንግስት ሊያከብር የሚገባው ብሔራዊ የሀፍረት ቀን እንጅ ብሔራዊ የኩራት ቀን አይደለም።