>

የኩራት/ዝ  ቀን በኢትዮጵያ!!!  ፖለቲካ ሆይ ነፍስህን አይማረዉ!!! (በላቸው ሀይሌ)

የኩራት/ዝ  ቀን በኢትዮጵያ?! 
 ፖለቲካ ሆይ ነፍስህን አይማረዉ!!!
በላቸው ሀይሌ
~የብአዴን አመራሮችንና የመከላከያ ኢታማዦርሹምን በሴራና እርስበርስ የተጫረስንበት ኢትዮጵያ!
~ እምነትን ጠብቃ፣ ታሪክን አቆይታ፣ፊደል ቀርጻ ሀገር ያቆየች ኦርቶዶክስን ለመሰንጠቅ መንግስት የሚያሴርባት ኢትዮጵያ!
~23 ባንክ በጠራራ ፀሐይ በመሀል ከተሞች ዝርፊያ የተከናወነባት ኢትዮጵያ!
~ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅል መንጋ ያየንባት ኢትዮጵያ!
~ትም/ሚ/ር የዘቀጠ ውሳኔ ያሳለፈባት ኢትዮጵያ!
~ዘረኝነት የነገሰባት ኢትዮጵያ!
~ሰላማዊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በጠመንጃ የሚበትንና የፈላ ውሃ በሰው ላይ የሚደፋ ትውልድ ያየንባት ኢትዮጵያ!
~በአጣዬና በከሚሴ እንዲሁም በሲዳማ የበርካታ ዜጎች ህይወት የጠፋባት ኢትዮጵያ!
 ~ ሌላው ሞቶ፣ተፈናቅሎ፣ ተሰዶ እኛ (ኬኛ) ብቻ ሁሉን እናጋብሰው የሚል ስግብግብ ትውልድ የፈላባት  ኢትዮጵያ!
~የጋራ ነገሮቻችን እየጠፉ ዘረኝነት የነገሰባት ኢትዮጵያ!
~ፍ/ቤት የሚፈልጋቸው እነጌታቸው አሰፋን አሳልፌ አልሰጥም በማለት የፌደራል መንግስትን አቅም የሚፈታተን የክልል ስልጣን ያየባት ኢትዮጵያ!
~ መንግስት የአዋሳን የክልልነት ጥያቄ ጉሮሮውን ታንቆ ለመመለስ ቀን የቆረጠባት ኢትዮጵያ!
– ወጣቱ በስደት ባህር  ላይ ሠምጦ የሚቀርባት ኢትዮጵያ
– ወጣቱ በአደባባይ ድምፁን ሲያሠማ  በጥይት  የሚመታበት ሀገር ኢትዮጵያ ፡
–  ህዝብ መሪዉን /ገዥዉን መርጦ የማያዉቅባት ኢትዮጵያ
–  የሰው ልጅ በድንጋይ ተወግሮ የሚገደልባት ኢትዮጵያ!
~ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ያሰማ ወጣት በጠራራ ፀሀይ በጥይት የሚረሸኑባት  ኢትዮጵያ
~ “መጤ” እያሉ ወግረው  የገደሉት ሰው ሬሳው እንኳ ቦታ እንዳይዝባቸው በእሳት የሚያቃጥሉባት ኢትዮጵያ!
– በዘር በቀለምና በቋንቋ የምትተራመስ  ሀገር  ኢትዮጵያ
–  መንግስትና ተፎካካሪ ፖርቲወች ሆድና ጀርባ የሆኑባት ሀገር ኢትዮጵያ
–  ንፁህ የመጠጥ ዉሀ የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
–  መብራት በፈረቃ የሆነባት ሀገር ኢትዮጵያ
– የኔት ወርክ  ችግር  ቅንቅኑን ያራገፈባት  ሀገር ኢትዮጵያ
– በብድር እዳ  ተስፈኛ የሆነች ሀገር ኢትዮጵያ
– የወላጆች ማዋለጃ ጤና ጣቢያ ያልተሟላበት ሀገር ኢትዮጵያ
-,ህፃናት የሚራቡባት ሀገር ኢትዮጵያ
–  የትምህርት ጥራት የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
–  በበሬ ጫንቃ በእርሻ የምታመርት ሀገር ኢትዮጵያ
–  ቤተክርስቲያንና አባቶች የሚቃጠሉባት  ሀገር ኢትዮጵያ
– ጉቦ በገሀድ የሚፈፀምባት ሀገር ኢትዮጵያ
– አንድነቷ የሚያሰጋት ሀገር ኢትዮጵያ
– ዜጎች ወጥቶ በሠላም የመግባት ዋስትና የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ
– የኑሮ ዉድነት ጣራ የወጣባት ሀገር ኢትዮጵያ
–  የተረጋጋ መንግስት የሌለባት ሀገር ኢትዮጵያ
–  ሥራ አጥነት ከፍ የአለባት ሀገር ኢትዮጵያ
– ዜጎቿ ሠብስቦ መመገብ የማይችል መንግስት ያለባት  ሀገር ኢትዮጵያ
-ታክሲ በወረፋ  ፡ ዘይት  በቀበሌ የሚታደልባት  ሀገር ኢትዮጵያ
እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉትን ኩነቶች ያስተናገደ መንግስት ሊያከብር የሚገባው ብሔራዊ የሀፍረት ቀን እንጅ ብሔራዊ የኩራት ቀን አይደለም።
Filed in: Amharic