>
5:14 pm - Wednesday April 30, 5383

የበረኸኞቹ መልእክት ...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የበረኸኞቹ መልእክት …!!!

ዘመድኩን በቀለ

የመጀመሪያው የምጥ ዓመት 2012 ዓ.ም ባየነው በተመለከትነው መልኩ አልፏል ። እግዚአብሔር ከተናገረው አንዳችም የቀረ የጎደለም የለም ። ስለብዙሃን ፀሎት ሲል በተለይ በአክሱምና በጎንደር በተደረገው ጸሎት ሲል ከመከራዎቹ ጥቂቶቹ አልፈዋል የክሱማዊያን እንባ የጎንደሮች እንባና ምዕላ እግዚአብሔር ተመልክቷል ስለዚህም ሲል ህዝቦቹን ከመቅሰፍት ከበሽታ ከወረርሽኝ አድኗል ።
     ይኸ የዛሬው መልእክት የአሁኗን ኢትዮጵያ ብቻ እንጂ የጎረቤት ሀገርና ሌላውን ዓለም አይመለከትም የነሱን ደሞ በሌላ ጊዜ እግዚአብሔር ባለ ሰአት እንመለስበታለን ዛሬ ግን ስለ ኢትዮጵያ የተነገረውን ሽክም እንናገራለን ።
     ያለፈው ዘመነ ዮሐንስ የሰማእትነት ፣የመከራ ፣የጭንቀት ዘመን ነበረ ዘመነ ማቲዎስ ምን እንደሚመስል እናየዋለን በዚህ በያዝነው ዓመት  በዘመነ ማቲዎስ በሀገረ ኢትዮጵያ እንዲህ ይሆናል
-ረሀብ 
-በሽታና
-ወረርሽኝ 
-የእርስበርስ ጦርነት ዋነኞቹ ናቸው ።
በመጀመሪያ ረሀብ ቀደም ባሉ አመታት ያዝ ለቀቅ ያደርግ የነበረውና በአንዳንድ አካባቢ ብቻ ተወስኖ ይታይ ይነገር  ይሰማ  የነበረው የረሀብ ዜና አውን ዘንድሮ በመላው ሀገሪቱ ይንሰራፋል አምና በአንበጣ መንጋ ምክንያት ይወድም የነበረው የህል ምርት ገሚሱን በአበው ፀሎት በአክሱማዊያንና በጎንደሮች ምህላ ለመዳን በመቻሉ የእህል እጥረት ቢኖርም ዋጋው ቢወደድም እንደምንም ዘመነ ዮሐንስ ታልፏል ። የሚበላው አቶ በየቤቱ በከባድ መከራና ሰቀቀን ለሊቱ የማይነጋለት ቀኑ የማይመሽለት ህይወቱ በከባድ ማዕበል ውስጥ የሚያሳልፈው ህዝብ ግን ሳይቆጠር ማለት ነው ።
አደባባይ ያልወጣ #የከተማ #ረሀብ ከጀመረ ቆየ የኮረና ወረርሽኝ የተባለው መቅሰፍትም የእርሻ ግብአቶችን በሚፈለገው መጠን ባለማቅረቡ በመንገዶች መዘጋት ምክንያት የአምናው ምርት ተቀንሷል እናም ዘንድሮ 2013 ዓ.ም ዘመነ ማቲዎስ ከበድ ያለ የረሀብ ጊዜ ማስተናገድ የግድ ነው ። ጎርፍ ፣ የአህዛብ ሰይፍ አምራቹን ገበሬ በሰቀቀን ውስጥ ከቷል ጦም ያደረው መሬት እህል ሳይዘራበት ያለፈው መሬት ቀላል አይደለም ይሁነኝ ተብለው የተሰሩ የአምራች ሀይሉ የገበሬዎች መፈናቀል ምክንያት ገበሬው በጊዜው ዘር ባለመዝራቱ እርሻም ባለማረሱ ምርት የለም ። በመከራ የተዘሩትንም ቢሆን አንበጣና ጎርፍ ተረባርበው የተዘራውን እህል ያወድሙታል በጌዲኦ በደቡብ የተዘራውን እህል በሜንጫ ጨፍጭፈውታል በጎተራ የገባውን እሳት ለኩሰውበታል በአውድማ የተከመረውን በእሳት አንድደውታል የእህል ግፍ የእህል ጡር ሁሉንም እኩል ዋጋውን ይሰጠዋል እናም በዘንድሮው ዓመት ረሀብ ተጠባቂ ነው ። የማይነቅዙ እህልና ጨው አዘጋጁ ለመትረፊያ የተዘጋጁ ለገዳማት ላኩ ጾም ፣ፀሎት ፣ ንስሐ ስጋ ደሙን አዘውትሩ መፍትሄው ይኸ ብቻ ነው ።
   ሁለተኛው የእርስበርስ ጦርነት አስቀድሞ እንደተናገረ በተለይ በትግራይና በአማራ በኩል የማይቀር ደም አፋሳሽ ጦርነት ይደረጋል አይቀሬ ነው ራያ የደም መሬት ነው ። ….. ብሔር ወጣት የሚያልቅበት ነው ስሙ አልጠቅስም እነሱ ተናግረዋል እኔ የዚህ ዘር አይደለሁም ብለው እስኪምሉ ድረስ  ብዙዎች ያልቁበታል በሆነ ምድር ወንድ ልጅ ብርቅ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል እሩቅ አይደለም ። ምክንያቱም ከባእዳን ጋር ወግኖ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ሀገሩ ኢትዮጵያን ወንድሙን ……. የድንግል ማርያም አስራት ሀገር ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ሰንደቃላማችንን ወዘተ በድፍረት ለማጥፋት እንዲሁ እንቅልፍ አቶ እየሰራ ያለ የነበረ ስለሆነ ምድር እስክታልፍ ድረስ ዳግም መሪ መሆን አይችልም ስልጣንም እንደ ሰማይ ይርቀዋል እጅግ ጥቂት የዘረኝነት መንፈስ የሌለባቸው የተመረጡ ከዋክብት  ……ለትንሳኤው እንደተዘጋጁ ይታወቅ ። ነጻ የወጣ ህዝም ወደፊት የሚዘመርለት ይሆናል የዛሬው መቃጠል ፣የዛሬው መታረድ ክብር ሆኖ ከክብሯን ጋር ይደመራል ይህ ማለት ግን አማራ በውስጡ የተፈለፈሉ ክፋትና አጥያትን እስከ አጥንታቸው ድረስ እንደ ቂቤ የጠጧት እልፍ አእላፍ እንዳሉና የፍርዱን ተካፋይ እንደሚሆኑ ሳይረሳ ነው ። በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሰንደቃላማ በተዋህዶ የሚያምኑ በንስሐ የተጠበቁ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለትንሳኤው የተመረጡ ናቸው ።
   የዋቄፈና የገዳ አራማጆች ግን ከመጪው የኢትዮጵያ ትንሳኤ እድል ፈንታ አይኖራቸውም ሰው ማረድ ሰው መግደል ሰው መስቀል ሰው ማሳደድ ንብረትና ሀብት ማፈናቀል ውርደትን ያመጣል ብድር በመድር ይሆናል ።ተፈፅሞ ሁለቱ ወንድማማቾች ሀገራችን ሰድበው ለሰዳቢ ይሰጧታል ከነሱ ፀብ አስቀድሞ በእቡ ይሰራ የነበረና አሁንም ያለ ቡድን ከሁለቱ ውድቀት በኋላ ሀገራችን ያጠፋታል ከሀገር ቤት እስከ ውጭ የተዘረጋውና ለጥፋት የታዘዘው ፅንፈኛ የእስላማዊ አስተዳደር ይችን ሀገር ያወድማታል ጎንደር ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ወገራ ገቢያና ፎገራ (እርብ)  ከጎጃም ፈረኛ ይወጣል ወያኔን ይቀብራታል ወሎ ከሚሴ ደሴ ቦሩ ሜዳና ላሊበላ ሸዋ ምንጃርና ይፋት አዲስአበባ በአራቱም በር ቄሮ አልሸባብ እስላማዊ ሀይሎች የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊሶች በማሰማራት አዲስአበባን በደም ጎርፍ ሊያጥብልህ ነው ።
የምኒልክ ሀውልት አደጋ ይገጥመዋል መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዎርጊስም እንዲሁ የምኒልክ አደባባይ በደም ይጨቀያል ታቦታቱ ከአሁኑ በስውር ከከተሞች በመውጣት ላይ ናቸው ወደ ተዘጋጀላቸው  ስፍራ የሄዱ ታቦታት አሉ ደገኛ አባቶች ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዎርጊስ ቤተክርስቲያን እየተሳለሙ እያለቀሱና እያነቡ በመሰናበት ወደ ገዳማት በመሄድ ላይ ናቸው ።
   ከዚህ በፊት እብድ ፣አረጋዊ በሽተኛ መስለው በየአብያተክርስቲያን በራፍ ላይ ወድቀው ይታዩ የነበሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ከተማዋን ለቀው መውጣት ከጀመሩ ቆዩ ዞር ዞር ብላችሁ ተመልከቷቸው የሉም የቀሩት በቅርቡ ይወጣሉ ። እነሱ(አህዛብ) ልክ እንደ ኦሮሚያ በቅድሚያ የሚያወድሙትን መዝግበው ይዘዋል ሁሉም ድንገት ይሆናል  ለሊት በድንገት ያደርጉታል የተቀረው አካባቢ ቀደም ብለው የጀመሩትን አጠናክረው ቀጥለው በአራቱም ማእዘን ዳር እስከዳር ያዳርሱታል ምስራቃዊና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክንፍ በአክራሪ ጽንፈኛ እስላሞች ማእከላዊ ደቡባዊና ምእራባውያን የኢትዮጵያ ክፍል እንደ ሰደድ እሳት የሚዛመቱ የእርስበርስ ጦርነቶች ህዝብ ይተላለቃል ይኸ ሁሉ መከራ የሚሆንብን እና የሚመጣብን ግን በራሳችን አጥያትና በአመጻችን ምክንያት ነው አህዛብ በአራቱም አቅጣጫዎች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ።
    አስቀድመው የሶርያና የየመን ስደተኞች የኔ ቢጤ መስለው የገቡት ስራቸውን ይጀምራሉ ዝርዝሩ በጣም ሰፊ ነው ልክ እንደ ኦሮሚያ ጭፍጨፋ ወንዱን ሁሉ አብዛኛውን ጨርሰው ሴቱን ከክብር ያወርዱታል ።
   ሦስተኛው መልእክት
የተፈጥሮ አደጋዎች ወንዞች ከልካቸውና ከመጠናቸው በላይ ይሞሉ ዘንድ ታዘዋል ይህ መልእክት የተላለፈው ነሐሴ ላይ ነው ይህ አደጋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለሙ ሁሉ ጭንቀት ነው ።ጎሮቤት ሀገራት የቅርብና የሩቆቹ አይቀርላቸውም ጎርፍ በመላው አለም ጀምሯል ከባባድ አውሎንፋስ ከመዝገባቸው ይወጣሉ ይህ አመፀኛውን ትውልድ የሚመካበትን ሁላ ድብልቅልቁን ያወጣዋል በእሳት የሚቀጡ ሀገራት አሉ በድርቅ ፣በረሀብ በቸነፈርም የሚቀጡ ሀገራት አሉ አመፀኛዋ ምድር በፈጣሪዋ በእግዚአብሔር እጅ በሚገባት መጠን በሚገባት ልክ ትቆጣለች ዘልዛላው ዓለም መግቢያው መውጫውም ይጠፋዋል  #የበጉ #የኢየሱስ #ክርስቶስ #ደም #ምልክት #ያለባቸው #ስጋ #ደሙ የተቀበሉ ግን በእሳት ውስጥ ይመላለሱ ። በማእበሉ ላይ ይዋኛሉ ክፉ አያገኛቸውም #በሰማእትነት የተጠሩም በደስታ ሁሉንም በክብር ይቀበሉታል በኢትዮጵያ የሚፈጠረውን ክፍተት ተጠቅሞ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከአህዛብ ወገን የሆነ ሊነግስ ይችላል ከአንድ ዓመት እስከ አንድ አመት ተኩል የሚሆን ጊዜ ይራወጣል አክሱም ፂኦን ላይ ያለው ጥያቄ ይበረታል ነጋሲው ካቢኔ አዋቅሮ ጨርሷል ።ነገር ፍለጋ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች የፕሮቴስታንት ክፍል በእናት ቤተክርስቲያን በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የትቢትና የጭካኔ ተግባራትን ለመፈፀም  ይራወጣል በተለይ በሲዳማ ፣በከንባታ ፣በሀድያ ፣በወላይታና በጉራጌ ምድር ብዙ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች የተዋህዶ ልጆች ህይወት ንብረት እንደዋዛ ይረግፋል ስደት ወደ መሀል ሀገር ስደት ወደ ሰሜን ስደት ወደደቡብ ስደት ወደ ምስራቅ ይሆናል ።ብክነት ብኩን መሆን ብቻ ።
በሁለት ሀያላን በሰባት አረብ ሀገር የሚመራ ጦር  በኢትዮጵያ ምድር ይርመሰመሳሉ በጭዎቹ ሁለት አመታት በኢትዮጵያ የምጥ አመታት ናቸው አውሬው በተናጠል አማሮችን በጅምላ ሁሉንም የኦርቶዶክሳዊያን ደም ያፈሳል ሌሎች ኢትዮጵያን አይቀርላቸውም ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ ወየውላቸው አየሩም ንፋሱም ሞት ያዘንባል ጅራፍና ጠረጋው  ከመቅደሱም ይገባል የሚቃጠሉ ገዳማት አድባራት ይኖራሉ ዋልድባ ስደት ይጀምራል ። አባቶች ለሰማእትነት እራሳቸውን አዘጋጅተዋል  ብርና ገንዘብ ከወረቀት እኩል ይቆጠራል ዋጋም አይኖራቸውም ህግና ፍትህ በአፍጢማቸው ይደፋሉ መኖሪያ ቤቶች ከንቱ ይሆናሉ ገዳማትና ተራሮች የመሸሻ የመደበቂያ የመትረፊያ ስፍራዎች የሚሆኑበት ዘመን ይመጣል ገላጋይ የለም ሽማግሌ አስታራቂ የለም የተቀባው የተገፋው የታረደው ህዝብ ግን ያሸንፋል የኢትዮጵያ ትንሳኤ ያበስራል #የደሙ ምልክት ያለባቸው በሙሉ ይተርፋሉ አድኑኝ ድረሱልኝ የሚለው ጥሪ የሚመጣው ከዚህ ሁሉ ፍፃሜ በኋላ ነው የማይቀሩ ትእዛዞች ቢቀሩ እረጅም የመከራ ዘመን ለማሳጠር በየ በረሃው በየ ጥሻው በየ ገዳማቱ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ፀብ አጋንንት ግርማ ለሊቱን ታግሰው በጾም በስግደት በጸሎት የወደቁ የትየ ለሌ ናቸው መማለዳቸውን አያቋርጡም ህዝብ ግን አውንም በቀረችው ሽርፍራፊ ሰአት ንስሐ ይገባ ዘንድ ጥሪው አያቋርጥም  ክፉዎች ፍርድን አያስተውሉም እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሁሉንም ያስተውላሉ ። መፅሐፈ ምሳሌ 28፥5
   አሁን እግዚአብሔር ሊነግሥ ነው በምድርና በሞላዋ ላይ ሀይሉንም ሊገልጥ ነው እርሱ ሲነሳ ዓለም ትቀመጥ ዘንድ እሱ ሲናገር ዓለም ዝም ትል  ዘንድ የግድ ነው አሁን እግዚአብሔር ተነስቷል የጽዳት ዘመቻ ጀምሯል ረሀብ ፣በሽታ፣ የእርስበርስ ጦርነት ፣የተፈጥሮ ቁጣ የእግዚአብሔር የመግረፊያ ጅራፎች ናቸው ።መርከቢቱ ተሰርታ አልቃለች ነገር ግን አልተዘጋችም በሮቿ ክፍት ናቸው ለመዳን አሁንም እድሉ ሰፊ ነው እድሉ እንዳለ ነው ። አንተ ባለማእተብ ሆይ አትደንግጥ ፣አትፍራ ፣አትሸበር አዲስቷ ኢትዮጵያ ልትወልድ በምጥ ላይ ናት ። እናም ደስ ይበልህ አትዘን አታልቅስ አንተ ከሚተርፉት ወገን ለመሆን ግን እራስህን አዘጋጅ ከነዴማስ ፣ከነ ይሁዳ ተለይ ከሚያላግጡ ከሚያሾፉት ወገን አትሁን እራስህን ከከንቱዎች በአስቸዃይ በፍጥነት ለይ ከካራን ውጡ ከንአንም ግቡ የኢያሪኮ ግንቧ በቅርቡ ፈራሽ ነው ዓለም ሁሉ እያየ ግን ኢትዮጵያ ትነሳለች  አሜን ።
Filed in: Amharic