>
5:21 pm - Monday July 20, 2516

የደብረ ታቦር ሕዝብ ለባልደራስ ልዑክ ደማቅ አቀባበል አደረገ ...!!!

የደብረ ታቦር ሕዝብ ለባልደራስ ልዑክ ደማቅ አቀባበል አደረገ …!!!
 
“በቴዎድሮስ መንፈስ እንታገላለን፤ አንከዳችሁም
እስክንድር ነጋ

በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የባልደራስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ረቡዕ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጎንደር ከተማ ወደ ደብረ ታቦር አቅንቷል። ልዑኩ ጠዳ፣ ማክሰኝት፣ አዲስ ዘመንን አቆራርጦ ከመድፈኞቹ ከተማ ደብረ ታቦር ሲደርስ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። አቀባበሉ በተሽከርካሪዎች ታጅቦ ከከተማው ዳርቻ እስከ ቴዎድስ አደባባይ የዘለቀ ሲሆን የቡድኑ በአባላት አደባባዩ ስር ቆመው ሕዝባዊ ንግግር አድርገዋል። የኢትዮጵያ አንድነት መሀንዲሱ የአጼ ቴዎድርስ ፎቶ ግራፍ በክብር ተሰርቶም ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። የባልደራስ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ሽልማቱን ሲቀበሉ “ከጎናችን በቆመው በቴዎድሮስ መንፈስ እንታገላለን። እንደ ቴዎድሮስ ለአንድነታችን እንሠራለን። አንከዳችሁም” ብለዋለ።
“እስር ቤት ውስጥ ሆነን ስለጦርነቱ ሂደት በያንዳዱ ቅፅበት እናወራ ነበር። ጦርነቱን ሕወሓት ቢያሸንፍ ኖሮ ሀገር ያፈርስ ነበር። እየገፉ ሲመጡ ‘ከደብረ ታቦር አያልፉም’ ብዬ ነበር። እግዚአብሔር ይስጣችሁ ሳታሳፍሩኝ ቀራችሁ” ሲሉም አቶ እስክንድር ጨምረዋል።
የባልደራስ የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው “አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መምጣታችንን ሰምታችሁ እንደዚህ ሞቅ ባለ አቀባበል ስለተቀበላችሁን እናመሰግናለን። በርግጥ ወደ ደብረ ታቦር ስንመጣ እንግዶች አይደለንም። ቤታችን ነው። ይህ ሕዝብ ደግሞ ጀግናውን ማክበር ያውቅበታል። እኛ እንተን ልናከብር ስንመጣ እናንተ እኛን አክብራችኋል። ወያኔን ታግለን አሸንፈናል። ግን ትግላችን ገና አላለቀም። አዲስ አበባ ላይ ምዕመመናን ባንዴራ ለበሳችሁ ተብለው ተገድለዋል። ስለዚህ ትግሉ ገና ነው። ሞት እስኪቆም እንታገላለን” ብለዋል።
የልዑክ ቡድኑ አባል እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ አስቴር ስዩም (ቀለብ) “የአማራ ፋኖ፣ የአማራ ሚኒሻ፤ አጠቃላይ አማራ አንድ ሆኖ ኢትዮጵያን ማዳን አለበት። አደራ እላችኋለሁ።  እንደ አፄ ቴዎድሮስ አንድነታችሁን አስጠብቁ” በማለት መክረዋል።
በተመሳሳይ የሴቶች አደረጃጀት ሓላፊዋ ወ/ሪት አስካለ ደምሌ እና የድርጅቱ የገንዘብ አስተዳድር ሓላፊዋ ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሒም  ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል።
Filed in: Amharic