>

ባልደራስ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ገለጸ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ባልደራስ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


*… በእለቱ የእስክንድር ነጋን ተተኪም ይመረጣል

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በመጪው ነሐሴ 22፤ 2014 በሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ፤ የፓርቲውን ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ለመተካት ምርጫ እንደሚያደርግ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገለጹ። ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሄድ  የደረሰኝ መረጃ የለም ብሏል።

በሌላ በኩል የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ በባልደራስ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት እና የፓርቲውን የወደፊት አካሄድ በተመለከተ፤  ነገ ውይይት እንደሚያደርግ የፓርቲው ምንጮች አስታውቀዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ እስክንድር ከፓርቲው ጋር ግንኙነታቸውን ያቆሙት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው። ዛሬ ሐሙስ በፓርቲው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተላለፈው መልዕክትም፤ ሰሜን አሜሪካ በሚገኘው የባልደራስ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ በኩል እንጂ፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤት የወጣ እንዳልሆነም ጠቁመዋል።

“እስክንድር ከሐምሌ 16 ጀምሮ ቢሮ አይገባም ነበር። ስልክም አያነሳም። ግንኙነት ያለውም ከሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ጋር ነው እንጂ ከእኛ ጋር ግንኙነቱን ያቆመው ሐምሌ 16 ነው። ስለደህነነቱ የምናውቀውም ከሰሜን አሜሪካ በምናገኘው መረጃ ነው” ሲሉ የባልደራስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ ስለ ፓርቲው ፕሬዝዳንት የሚያውቁትን ተናግረዋል።

በባልደራስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተሰራጨው መልዕክት “የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ያስተላለፈው አይደለም” ያሉት እኚሁ አመራር፤ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ “ዛሬ በወጣው መግለጫ ላይ፤ በእስክንድር ጉዳይ ላይ እና አካሄዳችን እንዴት ነው የሚሆነው በሚለው ላይ ውይይይት ያደርጋል” ብለዋል። የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አምሃ ዳኘው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ነገ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7586/

Filed in: Amharic