>

'ኦሮምኛ የሚናገር የኛ፤  የማይናገር ጠላታችን " የሚለው ሰይጣናዊ እሳቤ ዛሬ ላይ በቃ! ሊባል ይገባል...! (አቻምየለህ ታምሩ)

‘ኦሮምኛ የሚናገር የኛ፤  የማይናገር ጠላታችን ” የሚለው ሰይጣናዊ እሳቤ ዛሬ ላይ በቃ! ሊባል ይገባል…!

አቻምየለህ ታምሩ


በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ እየተገበረ ያለው የተ.መ.ድ. የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ ወይስ የኦሮሙማን መመሪያ?

በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች በኦሮምኛ አንዲማሩ፣ የኦነግን ኦሮምያ የነጻነት አርማ እንዲያውለበልቡና ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢ የሚከሰውን መዝሙረ ኦሮምያን እንዲዘምሩ በማስገደድ ላይ ይገኛል። በተለያዩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ ይህንን የግዳጅ ጭነት የሚቃወሙ ተማሪዎችና ወላጆች ቢቃወሙም የኦሮሙማው አፓርታይድ አገዛዝ ግን ሕዝባዊ ተቃውሞውን ፍላጎቱን ለማስፈጸም ሕይወት እንደሚዘራ እንደ ወፎች ዜማ በመቁጠር በኦሮሙማው ቀጥሎበታል።

የአፓርታይድ አገዛዙ በሚከተለው የኦሮሙማ ርዕዮት ኢትዮጵያን የምታህል የኦነግን ኦሮምያ ለመገንባት ያለ እረፍት እየሰረ ስንደሆነ ሲነገር ብዙ ሰው በተለይም የአዲስ አበባ ሕዝብ ጆሮ ዳባ ብሎ ቢያልፈውም በሕዝቡ ይሁንታ ያለ እረፍት ሲሰለቅጥ የሚውለው አይጠግቤው ኦሮሙማ ግን የከተማ አስተዳደሩንና የሕዝብ መገልገያ የሆኑትን የአዲስ አበባ ምልክቶች ኦሮማይዝ ከማድረግ አልፎ የያንዳንዱን አዲስ አበቤ ቤት በማንኳኳት ላይ ይገኛል።

ዛሬም ያልገባው ቢኖር ኦሮሙማ ማለት ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶችን ኦሮሞ ማድረጊያ፣ የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍልቆ በኦሮሞ ባሕልና ቋንቋ መሰልቀጥና መዋጥ፣ የኦሮሞ የተባለውን ሃይማኖት ብቻ እንዲቀበሉ ማስገደድና ባጠቃላይ ሰማዩንም ምድሩንም ኦሮሞ የማድረጊያ ፕሮጀክት ነው። በኦሮሙማ ፕሮጀክት እሳቤ መሰረት የክርስትና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነ ኦሮሞ እንደ ኦሮሞ አይቆጠርም። የኦሮሙማ ፕሮጀክት አይዲዮሎጉ ፕሮፈሰር አሰፋ ጃለታ አንድ ኦሮሞ የክርስትናና የእስልምና እምነትን ከዋቄ ፈታ እምነት የሚመርጥ ከሆነ በፍቃዱ ኦሮሞነቱን እንደተወ ይቆጠራል ይላል።

በኦሮሙማ እሳቤ አንድ ሰው ኦሮሞ የሚሆነው ኦሮምኛ የሚናገር ብቻ ስያሆን የዋቄፈታ እምነት ተከታይ ሲሆን ጭምር ነው። የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አገዛዝ አሁን በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮምኛን ቋንቋ ጭኖ በቋንቋ በኩል የሚፈጸመውን ኦሮሙማ ከጨረሰ በኋላ ቀጣዩ እቅዳቸው የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን አዲስ አበቤ የዋቄ ፈታ እምነት እንዲቀበል ማስገደድ ነው። ኦሮሙማ ይኼው ነው። ከዚህ ውጭ ኦሮሙማ ሌላ ትርጉም የለውም! ይህንን የሚጠራጠር ቢኖር ኦሮሙማ የያንዳንዱን ቤት እያንኳኳ ስለሆነ ተራው እስኪደርሰው ድረስ እድሜ ይስጠው እንጂ በቅርቡ ከበሩ ስልፎ ቤቱ ሲንኳኳ ያየዋል።

የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ እየጫነው ያለውን የኦሮምኛ ቋንቋ በሚመለከት ሲናገር ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማሩ የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ እየተገበረ እንደሆነ ይናገራል። እውነት ነው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ልጆች አፋቸውን በፈቱበ ቋንቋ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቢማሩ ይሻላል የሚል ምክረ ሀሳብ አለው። የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ ግን ከኦሮሞ ቤተሰብ የተወለዱ ልጆችን ጨምሮ በኦሮምኛ እንዲማሩ እያስገደደ ያለው በአማርኛ አፋቸውን የፈቱ የአዲስ አበባ ልጆችን ነው።

በሌላ አነጋገር የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ አፋቸውን በአማርኛ በፈቱ ከኦሮሞ ቤተሰቦች በተገኙ የአዲስ አበባ ልጆች ላይ ጭምር በኦሮምኛ እንዲማሩ እያደረገ ያለው ማስገደድ ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማሩ የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ እየተገበረ ሳይሆን ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ቢማሩ ይሻላል የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ በመጣስ ጥርሱን እያረገፈ ነው።

ቤተሰቦቹ ከየትኛው ነገድ ቢሆኑ አዲስ አበባ የሚወለድ ልጅ የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ ነው። ከዚህ የተለየ ጥናት ካለ ለመታረም ዝግጁ ነው። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሰረት እነዚህ አፋቸውም በአማርኛ የሚፈቱ የአዲስ አበባ ልጆች የቤተሰቦቻቸው ቋንቋ ምንም ይሁን ምን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መማር ያለባቸው በአማርኛ ነው። የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ አዲስ አበባ ላይ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ ባፍጢሙ በመድፋት የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅትን ምክረ ሀሳብ በኦሮሙማ ቀይሮ በአማርኛ አፋቸውን የፈቱ ልጆችን አፋቸውን ባልፈቱበት ቋንቋ እንዲማሩ እያስገደደ ይገኛል።

 

የአንድ አገር መንግሥታት ኃላፊነት ሕጻናትን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ማድረግ ነው። የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ ግን «ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር አለባቸው» የሚለው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ «ሕጻናት [አፋቸውን ባልፈቱበት] በብሔራቸው ቋንቋ መማር አለባቸው» በሚል እየተገበረ “ብሔራቸው” ኦሮሞ ባልሆኑ የአዲስ አበባ ልጆችን ጭምር በኦሮምኛ እንዲማሩ እያስገደደ ይገኛል።

አንድ ከኦሮሞ ቤተሰብ የተወለደ አፉን በአማርኛ ቋንቋ የፈታ የአዲስ አበባ ልጅ ኦሮምኛ ማወቅ ከፈለገ ሊማር ይችላል። ይህንን ሊያደርግ የሚችለው በግሉ ነው። የመንግሥት ግዴታ አፉን በፈታችበት ቋንቋ እንዲማር ማድረግ እንጂ «በብሔሩ» ቋንቋ እንዲማር ማድረግ የመንግሥት ግዴታ አይደለም።

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ ኦሮምኛን እየጫኑ የሚገኙት የኦሮሙማ ጉግማንጉጎች አብዛኛዎቹ  ልጆቻቸውን አውሮፓና አሜሪካ ልጆች የወለዱ ዲታዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ልጆቻቸው አፋቸውን የፈቱት በየሚኖሩበት አገር ከተማ ባለው ቋንቋ ነው። ልጆቻቸውንም የሚያስተምሩት አፋቸውን በፈቱበት ቋንቋ ነው። ለኦሮሞ ሕዝብ ግን «ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር አለባቸው» የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክተ ሀሳብ እየጣሱ አፋቸውን ባልፈቱበት በብሔራቸው ቋንቋ ስላልተማሩ ጭቆና እየተደረገባቸው እንደሆነ አድርገው ይነግዱበታል።

በኦሮምኛ አፋቸውን የሚፈቱ ከኦሮሞ ነገድ ውጭ የሆኑ ልጆችም  መማር ያለባቸው አፋቸውን በፈቱበት በኦሮምኛ ነው። ሌላውም እንደዚያው መሆን ይኖርበታል። ይህ የተባበሩበት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት በወላጆችና በመንግሥታት ላይ የሚጥለው ኃላፊነት ነው።

በአማርኛ አፉን ፈትቶ “በብሔሩ” ቋንቋ በኦሮምኛ ያልተማርው ጭቆና ስለሚደረግብኝ ነው ብሎ የሚያስብ ቢኖር እሱ ኦነግ ያደነቆረውና በጥላቻ የተሞላ የእውቀት ጾመኛነት ነው። እያንዳንዱ ሰው ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ውጭ ባለ “በብሔሩም” ይሁን በሌላ የውጭ ቋንቋ መማር ቢፈልግ በራሱ ይማር አልያም ወላጆቹ ያስተምሩት እንጂ በሕዝብ ገንዘብ በመንግሥት ወጪ ሕጻናት አፋቸውን ባልፈቱበት ቋንቋ ሊማሩ አይችልም።

ባጭሩ የአዲስ አበባ ሕጻናትን አፋቸውን ባልፈቱበትና በብሔራቸው ቋንቋ እንዲማሩ ኦሮምኛን በግዳጅ እየጫነ የሚገኘው በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማሩ የሚለውን የተባበሩበት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ እየተገበረ ሳይሆን ሕጻናት አፋቸውን ባልፈቱበት ቋንቋ እንዲማሩ በማስገደድ የተ.መ.ድን ምክረ ሀሳብ ጥርሱን እያረገፈ ነው።

በመሆኑም የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አገዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ እየተገበረ ያለው ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አፋቸውን በፈቱበት በአማርኛ ይማሩ የሚለው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ምክረ ሀሳብ ሳይሆን ኦሮምኛ የሚናገር የኛ ነው፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ የሚለውን የኦሮሙማ መመሪያ ነው።

Filed in: Amharic