>

የአፋር ፍርድ ቤት የአቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጉዳይ የመዳኘት ሥልጣን እንደሌለው ቢገልፅም መዝገቡን እንዳይዘጋ ተከለከለ...!

የአፋር ፍርድ ቤት የአቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጉዳይ የመዳኘት ሥልጣን እንደሌለው ቢገልፅም መዝገቡን  እንዳይዘጋ ተከለከለ…!

ያሬድ የኔሰው

በግፍ እስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከአዲስ አበባ በግዞት ወደ አፋር፤ አዋሽ ሰባት ከተወሰዱ በኋላ ባለፈው የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም.  በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።  ፍርድ ቤቱም በፌዴራል ፖሊስ የተከፈተባቸውን የሽብር የምርመራ ዶሴ የመዳኘት ሥልጣን እንደሌለው ገልጿል። ይሁን እንጂ መዝገቡን ዘግቶ ከማሰናበት ይልቅ የ11 ቀናት ቀጠሮ በመስጠት ለነገ የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የካቲት 23 በየዓመቱ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ መሥሪያ ቤቶች ተዘግተው የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት ዕለት ሲሆን ችሎቱ ቢሰየም እንኳን ዶሴውን የመዳኘት ሥልጣኑ ሳይኖረው ዳኞች ምን እንደሚያዳምጡና ምን እንደሚበይኑ አያውቁም። 

አቶ ስንታየሁ “ችሎቱ ጉዳየን የመዳኘት ሥልጣን ከሌለው ለምን መዝገቡን ዘግቶ አያሰናብተኝም? በሌለው ሥልጣን እኔን እስር ቤት አስቀምጦ ለምን ቀጠሮ ይሰጣል?” በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ችሎቱም “ሥልጣናችን ባይሆንም ቀጠሮ እንድንሰጥ ታዝዘናል። መዝገቡን መዝጋት አንችልም” ሲል መልሷል። አዛዡ ማን እንደንዳይዘጋ ተከለከለ!”

በግፍ እስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከአዲስ አበባ በግዞት ወደ አፋር፤ አዋሽ ሰባት ከተወሰዱ በኋላ ባለፈው የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም.  በአፋር መስተዳድር አንድ የወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።  ፍርድ ቤቱም በፌዴራል ፖሊስ የተከፈተባቸውን የሽብር የምርመራ ዶሴ የመዳኘት ሥልጣን እንደሌለው ገልጿል። ይሁን እንጂ መዝገቡን ዘግቶ ከማሰናበት ይልቅ የ11 ቀናት ቀጠሮ በመስጠት ለነገ የካቲት 23 ቀን 2015ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የካቲት 23 በየዓመቱ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ መሥሪያ ቤቶች ተዘግተው የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት ዕለት ሲሆን ችሎቱ ቢሰየም እንኳን ዶሴውን የመዳኘት ሥልጣኑ ሳይኖረው ዳኞች ምን እንደሚያዳምጡና ምን እንደሚበይኑ አያውቁም። 

አቶ ስንታየሁ “ችሎቱ ጉዳየን የመዳኘት ሥልጣን ከሌለው ለምን መዝገቡን ዘግቶ አያሰናብተኝም? በሌለው ሥልጣን እኔን እስር ቤት አስቀምጦ ለምን ቀጠሮ ይሰጣል?” በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ችሎቱም “ሥልጣናችን ባይሆንም ቀጠሮ እንድንሰጥ ታዝዘናል። መዝገቡን መዝጋት አንችልም” ሲል መልሷል። አዛዡ ማን እንደሆነ በግልፅ ባይጠቅስም የኦሮሙማ ባለሥልጣናት እንደሆኑ ይገመታል። 

የፍርድ ቤቱን ምላሽ ከሰሙ በኋላ በሕገ ወጡ ቀጠሮ ችሎት እንደማይቀርቡ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ተናግረዋል። 

መርማሪ ፖሊስ በሀሰተኛ የምርመራ ዶሴው ላይ ያቀረበባቸው ውንጀላ፥ “ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ፣ የስርጭት ፈቃድ በሌላቸው መገናኛ በዙሃን አማካኝነት ሕዝብን በመንግሥት ላይ ማነሳሳት” የሚል ነው። የፖለቲካ እስረኛው በአዲስ አበባ ጎፋ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በጸሎት ላይ እያሉ ታግተው መታሰራቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተደረገውን መንግሥታዊ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ሙከራ ተከትሎ ከ2500 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ከአዲስ አበባ ወደ አዋሽ ሰባት የተጋዙ ሲሆን፤ ሁሉም ሲፈቱ አቶ ስንታየሁ ብቻ በእስር ቀጥለዋል።

አቶ ስንታየሁ በየሦስት ወሩ የሚደረግ የህክምና ቀጠሮ እንዳላቸው ጠቅሰው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ቢጠይቁም ችሎቱ ከልክሏል።

በአሁኑ ሰዓት አቶ ስንታየሁ ቸኮል አዋሽ 7 ሜሪድያን ሆቴል ጀርባ ይገኛሉ።

Filed in: Amharic