ለ 2018 ከፍተኛ ትምህርት ከተፈተኑት ውስጥ 8•4% ብቻ በማሳለፍ የኢትዮጲያን ወጣቶች ተስፋ እያጨለመ ያለው የፋሺስቱ አቢይ አህመድ ቀኝ እጅ አገልጋይ የሆነው ብርሃኑ ነጋ በውድቀት የተዘፈቀው ስርአተ ትምህርት
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
ዘንድሮ የ 12ኛን መልቀቂያን ፈተናን ከወሰዱት ከ585ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ 50% በላይ ነጥብ በማምጣት ለከፍተኛ ትምህርት የበቁት ተማሪዎች ቁጥር 48929 ብቻ ሲሆን ይህም በፐርሰንቴጅ ሲቀመጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእድጠቃላይ ፈተና ላይ ከተቀመጡት ተማሪዎች 8•4% ያህል ብቻ ሲሆኑ የወደቁት ደግሞ 91•6% ያህል ናቸው።
ከ 585ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ 50% በላይ ውጤት አምጥተው ማለፍ የቻሉት ተማሪዎች ቁጥር 48929 ሆነ ማለት ከ 490 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ አቅታቸው ወድቀዋል ማለት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ. ባለመቻል ስማቸው ተመዝግባል።
‘’እኔ በስልጣን ዘመኔ አንድም አዲስ ዩንቨርስቲ አልገነባም’’ በሚል መሪ መሀይማዊ የትምህርት ፖሊሲ የሚታወቀው ፋሺስቱ አቢይ አህመድ – የነጋ ቦንገርን ልጅ – ብርሃኑ ነጋን ወደ ትምህርት ምኒስቴርነት ስልጣን ካመጣ ጀምሮ በዚህ አምስት አመት ውስጥ የኢትዮጲያ ወጣቶችን ብሩህ ተስፋን በማጨለም ሪኮርድ የሰበረ አረመኔ ሰው ሆናል።
ፋሺስቱ የብልጽግና ስርአት በሚያራምደው የጦርነት ፖሊሲ ምክንያት ከ 7,5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ሙሉ በሙሉ የታገዱ ሲሆን የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ከ 95% በላይ ያለውን የማይማሩ ታዳጊዎችን በመያዝ ይመራሉ።
የጨለማው ብርሃኑ ነጋ ቦነገር አይነተኛ ተልእኮ ወጣቶችን ከትምህርት ደጃፍ በማባረር ለጦር አምራቹ አቢይ ግብአትነት የማዘጋጀትን ሀላፊነት ወስዶ በትጋት እየሰራ ያለ ሲሆን ለዚህም በየአመቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በማገድ ለውትድርና የሀይል አቅርቦት ስራን እየሰራ ይገኛል።
ይህ ትውልድ ገዳይነት ነው። ይህ አማራውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጲያን ወጣት ተስፋን ማጨለም ነው።
ይህን ፋሺስታዊን ስርአት ሁሉም በየፊናው አምርሮ ሊታገለው ይገባል።
የዘንድሮ የትምህርት ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆን የሚገባው በግፍ ስለተጣሉት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ህይወት ጉዳይ መሆን ሲገባው በጣት የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ውጤት እየገለጹ ከአዲስ አባባ እከሌ እና እከሌ የሰቀሉ እያሉ የሚጽፉ አዝጎችን ማየት እጅግ ያሳፍራል።
በትምህርት ጉዳይ አጀንዳ ልናደርጋቸው የሚገባን የፋሺስቱን ትምህርት ሚኒስቴር ብርሃኑ ነጋን ጭካኔን እና የነገ ተስፋቸውን የተነጠቁት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ህይወት ጉዳይ ነው እንጂ ሰቅለው ስላለፉት አንድ ፍሬ ተማሪዎች ጉዳይ መሆን አይገባውም።