ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ 1876 ዓ.ም ለኢጣሊያ ንጉሥ ከፃፉት ደብዳቤ።
ጳውሎስ ኞኞ
“….ሐረር…ከአያት ከቅድመ አያቶቼ ጀምሮ የሸዋ ግዛት ነው።…”
ምኒልክ ግንቦት 27 ቀን 1877 ዓ.ም ለኢጣሊያ ንጉሥ ከፃፉት ሌላ ደብዳቤ።
ግብጾች ሐረርጌን የያዙት በ 1867 ነው። ኢትዮጵያ በመሳፍንት አገዛዝ ተከፋፍላ ሁሉም የዕለት ጥቅሙን ያሳድድ በነበረበት ጊዜ ክፍት በር ያገኘው በራኡፍ ፓሻ የሚመራ 1200 ወታደሮች ያለበት የግብጽ ጦር በቀላሉ ሐረር ገባ። በዚያን ጊዘ በሐረር ከተማ 5000 ቤቶችና 2000 ጐጆዎች ነበሩባት። የሐዝቡም ብዛት 35 000 ነበር። ሐረር ከተማ ዙሪያዋን በግንብ ተከባ ወደ ከተማዋ የሚገባውም ከከተማዋ የሚወጣው በአምስት በሮች ብቻ ነው። እነዚህም በሮች የተለያየ ስም ሲኖራቸው ታላቁ መግቢያ አስበዲን በር ይባላል። ይህ መድፍ ተጠምዶ የተቀመጠበት በር የጨርጨር ሰዎች መግቢያ ነው። 2 ኛው ሱቅጣጥ በር ይባላል። 3 ኛው በር አርጐባ በር ይባላል። የፈዶሶች ያርጐቦች መግቢያ ነው። 4 ኛው አሱም በር ይባላል። አሱም በር እንደ አስበዲን በር ሁሉ መድፍ የተጠመደበት ሲሆን የኢሶች መግቢያ ነው። 5 ኛው በር የረር በር ይባላል። የየረሮች መግቢያ ነው። እነዚህ በሮች ሁልጊዜ በሚገባና በጥንቃቄ ይጠበቃሉ። ማታ ሲሆን በሮቹ ይቆለፉና የቁልፎቹ መፍቻዎች ለአሚሩ ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ ነግሮ በሮቹ እስኪከፈቱ ድረስ የሚገባም ሆነ የሚወጣ የለም።
ኢጣሊያኖች ሐረርጌን ከመቃዲሾ ጋር እንግሊዞችም ከበርበራ ጋር ደባልቀው ለመያዝ አሳብ ነበራቸው። እንግሊዞች አንግሎ ኢጆፕቲያን በተባለው ከግብጽ ጋር በነበራቸው ስምምነት መሠረት የግብፅ ጦር ከሐረርጌ ወጥቶ ሐረርጌን ለእንግሊዞች ለማስረከብ ተስማምተዋል። ይህን ስምምነት የሰማው የኢጣሊያን መንግሥት ደግሞ ሐረርጌን ከእንግሊዝ ቀድሞ በኃይልም ሆነ በፍቅር ለመያዝ አስቦ በሐረርጌ ያለውን
የግብጾች ጦር የሚሰልሉ ሰላዮች በየጊዜው ወደ ሐረርጌ ይልክ ԿՈԸ::
እንግሊዞች ከግብጾች ጋር በነበራቸው ስምምነት መሠረት ግብጾች ከሐረጌ እንዲወጡ አደረጉ። ምናልባት የኢጣሊያ መንግሥት ገፍቶ የመጣ እንደሆነ በማለትም ከግብጾች ቀጥሎ ሥልጣን ለያዘው ለሐረርጌው አሚር አብዱላሂ እንግሊዞች የሰለጠኑ ወታደሮች 400 ያህል ጠመንጃና ጥቂት መድፎችን ሰጥተው ጀልዴሳና ሐረር ላይ ምሽጉን እንዲያጠናክር አደረጉት።
አሚር አብዱላሂ ሥልጣኑን በሚገባ ከያዘ ብኋላ የግብፅን ገንዘቦች አሽራፊ እና መሀለቅ የተባሉትን አስገብቶ በሐረርጌ ገበያዎች ላይ እንዲውሉ አደረገ። የእነዚህን ገንዘቦች መግባት ያየው የሐረርጌ ኦሮሞና የሱማሌ ብሔረሰቦች ገንዘቦቹን አንቀበልም በማለት በአሚሩ ላይ ጥላቻ አሳድረው ገበያ ጠፋ። በገበያው መጥፋት ምክንያት የአሚር ወታደሮች ችግር ላይ ወደቁ። አብዱላሂ በዚህ ብቻ ሳይሆን በሚያወጣው አዋጅ ሁሉ በሕዝቡ ዘንድ እየተጠላ ሔደ።
በሐረርጌ የውጭ ሸቀጥ አስመጭና ያገር ውስጥ ንግድ ላኪ የነበረው ኢጣሊያዊው ጋይታኖ ሰኮኒ በስለላ ተግባር ይጠረጠር ስለነበር የሐረሩ ኢማም አብዱላሂ ጋይታኖን ጠርቶ “…በእስልምና ሃይማኖት እመን። የማይታመንም ከሆነ አገሬን ለቀህ ውጣ።…” አለው። ጋይታኖም በእስልምና ሃይማኖት አላምንም ብሎ ከሐረር ገብቶ ሚላን ሳለው ለአፍሪካ የንግድ ማኅበር የደረሰበትን በደል አመለከተ። ማኅበሩ ለስም የተቋቋመ እንጂ ዋንኛ ሥራው የኢጣልያን መንግሥት ሰላዮች ማስተባበርና መላክ ስለነበር ስምንት የታወቁ የኢጣሊያ ሰላዮችን በኢጣሊያ ንጉሥ ስም ስጦታ አስይዞ ወደ ሐረር ወደ አሚር አብዱላሂ ላከ።
እነዚህ የኢጣሊያ መልክተኞች ሚያዝያ 1 ቀን 1887 ዓ.ም የሐረርጌ ግዛት ከሆነው ጀልዴሳ ደረሱ። ከዚያም ሆነው “የተከበሩ ታላላቅ ስጦታዎችን ይዘን መጥተናልና እንዲቀበሉን ፈቃድ እንጠይቃለን” ብለው ለአሚር አብዱላሂ ላኩ። አብዱላሂም ክርስቲያኖቹ ኢጣሊያኖች ወደ ግዛቱ በመግባታቸው ተናዶ እንዲገድሏቸው ወታደሮች ላከ።
የተላኩትም ወታደሮች ሰባቱን ኢጣሊኖች አርደው ገደሉዋቸው። አንደኛው ግን በፈረስ አምልጦ ዘይላ ገባ። ኢጣሊያኖቹን የገደሉት ወታደሮች የመጣውን ስጦታ ይዘው ለአሚር አብዱላሂ እቀረቡ። አብዱላሂ ከኢጣሊያ ንጉሥ መጥቶለት የነበረውን ስጦታ ተቀብሎ ኢጣሊያኖቹን የገደሉትን ወታደሮች አስራቸው። አብዱላሂ ይህን ማድረጉ ኢጣሊያኖቹ የተገደሉት በስህተት ስለሆነ ወንጀለኝኖቹን አስሬአለሁ ለማለት ያህል ነበር። ይህ ከሆነ በኋላ ኢጣሊያኖች ሐረርጌን በጦር ኃይል ለመይዝ ጥሩ ሰበብ አገኙ። “በሐረርጌ የተገደሉብን ወገኖቻችንን ደም እንበቀላለን” የሚል መግለጫ ማውጣታቸውንና ሐረርን ለመያዝ ማሰባቸውን የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሰሙ። ወዲያውም ለአሚር አብዱላሂ ደብዳቤ ጻፉለት።
“….ቀድሞም ቢሆን ሐረርጌ ከኢትዮጵያ ውጭ ተገዝቶ አያውቅም። ከኢትዮጵያ አውራጃዎች አንዱ መሆኑን አንተም በታሪክ ስምተኽው ይሆናል።….ለአራት መቶ ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ ግብሩን ለአያቶቼ ሲገብር ኖርዋል። አሁንም ነገሩን በሰላምና በወዳጅነት ለመጨረስ ገብርና እንደ አባቶቻን ወዳጅ እንሁን……” የሚል ደብዳቤ ለአሚር አብዱላሂ ላኩለት። አሚር አብዱላሂ ደብዳቤውን ከተቀበሉ በኋላ “…በውኑ በዚህ ዓለም ላይ ከቱርክ የሚበልጥ መንግሥት አለን?….” ብሎ ለመኳንንቱ ተናገረ።
ምኒልክም ለመጀመሪያው ደብዳቤያቸው መልስ ያለመምጣቱን እንዳዩ ዳግመኛ “ብትገብር ይሻልሃል” የሚል ደብዳቤ ላኩለት። የምኒልክ ሁለተኛ ደብዳቤ ሲደርሰው አሚር አብዱላሂ ሳቀ። ለምኒልክ ደብዳቤ ሲመልስ “……በእስልምና
ብሎ እስላሞች የሚያሸርጡትን ሽርጥ እስላሞች በራሳቸው ላይ ሃይማኖት ገብተህ የሰለምክ እንደሆነ ጌትነትህን እቀበላለሁ” የሚጠመጥሙትን ጥምጥምና የጸሎት ጊዜ መስገጃ ምንጣፍ ላከላቸው። ይህን መልስ ያገኙት ምኒልክ “ ….ወደ ሐረር እለውጠዋለሁ። ጠብቀኝ።” የሚል ደብዳቤ ልከውለት ይዘጋጁ እመጣለሁ። በዚያ ያለውን መስጊድም ወደ ቤተክርስቲያን ጀመር። ወዲያውም በአስቸኳይ ተዘጋጅተው በአጤ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ኅዳር 4 ቀን 1879 ዓ.ም ከእንጦጦ ከተማ ተነሳ።
የምኒልክ ከእጦጦ መነሳት የሰማው አሚር አብዱላሂ በሐረርጌ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ከሐረርጌ እንዲወጡ አዋጅ አስነገረ። በሃይማኖት ሳቢያ ይረዳሉ ብሎ ኤውሮፖውያንንም ጠርጥሮ ስለነበር ካገር አልወጣም ያለ ማንኛውም ክርስቲያን የሆነ ፈረንጅ ሁሉ ከቤቱ እንዳይወጣ አዘዘ። ጠባቂም በየበራቸው ላይ አደረገ። በዚያን ጊዜ በሐረር የነበረው እንግሊዛዊው ፔቴን ብጻፈው ማስታወሻ “…በከተማዋ ውስጥ እንደ እስረኞች ነን። ደብዳቤ የመላክና የመቀበልም ነፃነት የለንም። ከሐረር ክግንቡ ውጭ እንኳ እንዳንወጣ ክልክል ነን።….” ብሏል።
የገና በዓል ደርሶ ነበርና ንጉሥ ምኒልክ ጨለንቆ ላይ ሠፍረው የገናን በዓል ለማክበር ወሰኑ። በዚያም ሠፈር አድርገው ሳለ ምኒልክ መኳንንቶቻቸውን ሰብስበው “….ይህ አሚር አብዱላሂ እኛ ክርስቶስ ተወለደ ስንል እሱ አልተወለደም የሚልበት ቀን ነውና የልደት ዕለት ጦርነት መግጠሙ አይቀርም” ብለው ተናገሩ። ከዚህም በኋላ “……ግባ እኔ ላንተው ነው እንጂ የመጣሁት አገር ለማጥፋት አልመጣሁም። ተገባህ ተተገዛህ አገር አልነሳህም። ኋላ ይቆጭሃል” ብለው ላኩበት። አሚር አብዱላሂ ግን የፈሩት መስሎት የተላኩትንም መልእክተኞች አሠራቸው።
ኮንቲ ሮሲኒ ሲጽፉ “….ገብር የሚለው የምኒልክ ደብዳቤ ለአሚር አብዱላሂ እንደ ደረሰው የሕዝቡን አስተያየት ለማውቅ ሕዝቡንና ወታደሮቹን አሰብስቦ የምኒልክን ጥያቄ ስማቸው። ሕዝቡም በሃይማኖታችን ላልገባና በእስልምና ሃይማኖት ለማያምን አንገብርም። እንዋጋለን። ቢያሸንፉን ሐረርን ይውሰዱ። ያንጊዜም የሚፈልጉትን ግብር እንገብርላቸዋለን ብለው መለሱለት።….” ይላሉ።
የሐረርጌ ሽማግሌዎች ግን አሚር አብዱላሂ ዘንድ ሂደው ጦርነቱ እንዲቀርና እንዲገብር መከሩት። አብዱላሂ “….ስለምኒልክ ሠራዊት እንድትነግሩኝ አልፈልግም። እንድትነግሩኝ የምፈልገው መጽሐፋችን ለካፊር እጃችሁን ስጡ ይላልን….” ብሎ አማካሪዎቹን አሠራቸው። ካፊር ማለት በእስልምና የማያምን ነው። ከዚያም በኋላ የጀሃድ ጦርነት አወጀ። ሊያገብሩት ሄደው የነበሩትን የደጃች ወልደገብርኤልን ሠራዊት በጥቂት መሣሪያ በማባረሩ የምኒልክ ሠራዊትም እንደዚያው በቀላሉ ይሸሻል ብሎ አሰበ። ከዚህ በኋላ ሠራዊቱን አስከትሎ የምኒልክን ጉዞ ለማስቀረት ወደ ጨለንቆ ተጓዘ።
ቀኑ የክርስቶስ የልደት በዓል ስለነበር የምኒልክ ሠራዊት እየበላ እየጠጣ ይጫውታል። ንጉሥ ምኒልክ ከድንኳናቸው ደጃፍ ተቀምጠው አሸጋጋሪውን ኮረብታ በመነጥር ሲመለከቱ የአሚር አብዱላሂ ሠራዊት ሲመጣ አዩ። ምኒልክ ሠራዊቱ እንዲሰበሰብ አድርገው “ሂደህ በለው” ብለው አዘዙ።
ከቀኑ 5 ሰዓት የአሚር አብዱላሂ መድፎች በሸዋ ሠራዊት ላይ ይተኮሱ ጀመር። የሸዋ ሠራዊትም በአስደናቂ ፍጥነት የአብዱላሂን ሠራዊት ወርሮ መድፎቹን ማረከ። በተማረኩት የአብዱላሂ መድፎችም የአብዱላሂ ሠራዊት የምታበት ጀመር። ጦርነቱ ብልጭ ብሎ ጠፋ። የአሚር አብዱላሂ ሠራዊት ሩብ ሰዓት ያህል ከተዋጋ በኋላ ሸሸ። አብዱላሂም በፈረስ ሆኖ ወደ ሐረር ሸሽቶ አመለጠ። ከአሚር
አብዱላሂ ሠራዊትም አንድ ሺህ ያህል ወታደሮች ተገደሉ። ታህሣስ 29 ቀን 1879 ዓ.ም የሐረርጌው የአብዱላሂ ጦር ድል ሆነ። ይህን የአብዱላሂን ጦር ድል መሆኑ የሰሙት እቴጌ ጣይቱ አዲስ በመሠረቱት አዲስ አበባ ሆነው “የሚጓዘው ሰንጋ የሚነዳው ሽህር ለልደት ባይደርስ እሱ ላም አርዶ ዋለ የሸዋው ንጉሥ” ብለው ተቀኙ። አንዳንድ ያገራችን ታሪክ ፀሐፊዎች “እስላም አርዶ ዋለ” ብለው ቅኔውን በመተርጐም ጽፈዋል። እንዲያ ከሆነ ቅኔነቱ ይቀራል።
ምኒልክ ድል ካደረጉ በኋላ የኢጣሊያ መንግሥት ሐረርጌን ለመያዝ እጅግ በጣም የተነሳሳ ጉጉት ስለነበረው እዚያው ጨለንቆ እንደሆኑ ለኢጣሊያው ንጉሥ ለኡምቤርቶ “….ኢጣሊያኖችን የገደለው አሚር አብዱላሂ በፈረስ አመለጠኝ። ግን እግዚአብሔር ይመስገን ሰዎቹን ፈጀሁበት። ሰንደቅ ዓላማዬንም በአገሬ ላይ አቆምኩ። ወታደሮቼንም አገባሁ። ኢጣሊያኖቹን ለመርዳት ስል። ተደርጎ የነበረው አደጋ በብዙ ሬሣዎች ተበቀልኩ። ከዚህ ደብዳቤ በኋላ ሁኔታውን በሰፊው የሚያስረዳ መልእክት እሰዳለሁ።…” የሚል ታህሣሥ 30 ቀን ማለት በጦርነቱ ማግስት የተፃፈ ደብዳቤ ላኩ። ምኒልክ ይህን ደብዳቤ የፃፉት ሐረርጌ የኢትዮጵያ ግዛት መሆኑን ለኤሮፓ ነገሥታት ለማሳወቅና ኤሮፓውያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ባላቸው አሳብ መሠረት ወደ ሐረርጌ ጦር ቢልኩ ውጊያው ከምኒልክ ጋር መሆኑን ለማሳወቅ ጭምር ነበር።
ምኒልክ አብዱላሂን ለመያዝ ወደ ሐረር ከተማ ገሰገሱ። ጥር 1 ቀን አማሬሳ ሲደርሱ አብዱላሂ የሸዋ ጦር እንደደረሰበት ስላወቀ “ልግባና ልገዛ። አገርዎን አያጥፉት” ብሎ ላከ። ምኒልክም “እሺ ግባ ምሬሃለሁ” ብለው ላኩበት። አብዱላሂ ግን ፈርቶ ለሊቱን ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ወደ ጅጅጋ ሸሸ። የአብዱላሂን መጥፋት ያወቁት ሐረርጌዎች ማለት የአሚር አብዱላሂ አጎት አሊ አቡበከር የሱፍ በርከሌ ቃዲ አብደላና ሌሎች ሽማግሌዎች ሆነው ወደ ምኒልክ ዘንድ መጥተው “….አሚር አብዱላሂ ሌሊት ጠፋብን። ግብርዎን ይቀበሉን። ሕዝቡንም እያጥፉት ንጉሥ ሆይ….” ብለው አመለከቱ። ከመልክተኞቹም ጋር እስረኞች የነበሩትን ሁለት ግሪካውያንና ሌሎችንም ፈትተው ወደ ምኒልክ ላኩ። ንጉሥ ምኒልክም መልክተኞቹን ተቀብለው “….ከዚህ በፊትም ብያለሁ። እኔ የእስልምናን ሃይማኖት ለማጥፋት አልመጣሁም። ሁሉም ሰው እንደየ እምነቱ ያድራል። እናንተም ለሰላምና ለእርቅ ስለመጣችሁ በሰላም ወደ ሐረር እስክመጣ ይህንኑ ለሰዉ ነግራችሁ ከዚያው ቆዩኝ….” ብለው መልእክተኞቹን መለሱ። ከመልክተኞቹም ጋር በጅሮንድ አጥናፌ ከተማውን ለመረከብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው እንዲሔዱ አደረጉ። የሻቃ ተክሌን ባላምባራስ ዳምጠውን የሻቃ አድነውን የሻቃ ገበየሁን የከተማውን በሮች እንዲጠብቁ አዘዙ። እነኚህም ታዛዦች እንደታዘዙ ሐረር ከተማ በሰላም ገብተው ፈረስ መጋላ በሚባለው አደባባይና በአምስቱም በር ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሰቀሉ። ሰንደቅ ዓላማቅን መስቀል ብቻ ሳይሆን የሐረርን ከተማ ሕዝብ እንዳይዘረፍም በየቤቱ በራፍ ዘብ አቁመው ያስጠብቁ ጀመር።
በዛሬው በጂቡቲ ውስጥ አቦክ ከተማ የነበረው ታውሪን እ.ኤ.አ ፈብሩዋሪ 3 ቀን 1887 ዓ.ም ወደአገሩ በፃፈው ደብዳቤ “….ከተማዋ የተያዘችው አበሾች ድል ሲያደርጉ እንደሚይዙት ዓይነት አይደለም።….ያለምንም ደም መፋሰስና ዝርፊያ ድል አድራጊው የሸዋ ጦር ከከተማዋ ገባ።……” ብሏል። ንጉሥ ሚኒልክ አንድ ወር ያህል በሐረር ከቆዩ በኋላ ባላንባራስ መኰንን ደጃዝማች ብለው ጥር 18 ቀን 1879 ዓ.ም የሐረጌ የበላይ ገዢና የወታደር ሹም ብለው ሾሙዋቸው። 3000 ወታደሮችም ሰጡዋቸው። ለሕዝቡ ግን እንደ ባህሉን እንደሃይማኖቱ እንዲያተዳድሩ የአሚር አብዱላሂ አጐት አሊ አቡበከርን ሾሙ። የካቲት 1 ቀን ወደ ሸዋ ለመመለስ ከሐረር ተነሱ። ከሐረርጌ ጦርነትም 3000 ጠመንጃ 600 000 በጥይትና አራት መድፎች ማርከው ይዘው መጡ።
ንጉሥ ምኒልክ የካቲት 28 ቀን እንጦጦ ከተማቸው ሲገቡ ከዚያ በፊት ያልታየ አቀባበልና ሰልፍ ታየ። የዚያን ጊዜ ምኒልክን ሰልፍ ድንቅ ያደረገው በሐረር የነበሩ የአሚር አብዱላሂ ግብፃውያን ሙዚቀኞች ስለተማረኩ ከሰልፉ ፊት ቀድመው ሙዚቃ (ማርሽ) በማሰማት ይጓዙ ስለነበር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ከግብፅ የመጡ የኤሮፓ ውሾችንና በያይነቱ ቀለዩ ያላቸውን የርግብ ለማዳዎችን ሌላም አውሬ ሁሉ ይዘው ገቡ:: የዚያን ጊዜ ዘፋኞችም “የምኒልክ ነገር ይመስለኛል ተረት፤
አሞራው በቀፎ ውሻው በሰንሰለት” እያሉ ዘፈኑ።
@ዘ- ብሔረ ኢትዮጵያ
