>

ትግል ያለ ድርጅት - ድርጅትም ያለብቁ ባለ ራእይ መሪ ፈጽሞ አይታሰብም!!

·አማራ ታሪኩን ያድሳል – ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ በ1985(1993)

የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እና ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ የትግል ጉዞ !!!

ትግል ያለ ድርጅት – ድርጅትም ያለብቁ ባለ ራእይ መሪ ፈጽሞ አይታሰብም!!!

 

ጋዜጠኛ   ወንድወሰን ተክሉ

 

ልክ በዛሬዋ እለት ጥቅምት 07- 1969 (European Calendar) ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ – ወደዚህች ምትክ የለሽ ብቸኛና ብርቅዬ አለም ተወለደ። ዛሬ በ55 እመት የጉልምስና እድሜ ላይ ሆኖ ፋሺስታዊውን ስርአት በአማርዊ ነፍጥ መታገል ከጀመረ ድፍን ሶስት አመት ከአምስት ወራት ሞላው። ታላቁ አርበኛ ነፍጥ መዞ ጫካ የገባው በወርሃ ሀምሌ 2022 ሲሆን ከዘጠኝ ወር በሸዋ፣ በአፋርና በጎጃም በረሃና ገጠሮች የውስጥ ለውስጥ የማንቃትና የማደራጀት ስራው በሃላ በግንቦት 20 ቀን 2023 የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን በመመስረት ጸረ ፋሺስታዊ የነፍጥ (ትጥቅ) ትግልን በይፋ መጀመሩን ያበሰረ ሰው ሆነ። ከታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ወደ ጫካ መግባት. በፊት የፋኖ አደረጃጀት ነበረ። በ2021 የህወሃት ወረራን ተከትሎ አማራው ልጆቹን እየመረቀ ነፍጥ አስታጥቆ እንዲታገሉ በማድረግ ሂደት የፋኖ አደረጃጀት በአራቱም ክፍለ ሀገር በሚያስብል መልኩ ተፈጥሮ ነበር።

ይህ የፋኖ አደረጃጀት – ከዛሬው የፋኖ እድደረጃጀት የሚለይበት ዋና ነጥብ በወቅቱ አደረጃጀቱ የህወሃትን ወረራ ለመቀለብስ ያለመ ከመሆኑ አካያ የዛሬውን የአማራን ሕዝብ ጠላት የብልጽግናን ስርአት አጋሩ አድርጎ ህወሃትን ጠላት በማድረግ የተደራጀ ስለነበረ ብልጽግናን በጠላትነት ፈርጆ አፈሙዙን በብልጽግና ላይ ያላነጣጠረ የፋኖ አደረጃጀት ነበረ የተደራጀው።

ሆኖም ይህንን ጸረ አማራ የሆነውን ብልጽግናን አጋር አድርጎ የተደራጀውን አማራዊውን የፋኖን አደረጃጀት ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ የቀየረው በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ የተመሰረተው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ነው።

π ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ እና የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል

በ 1984 (1992)በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ፣በወተር፣ መሰል የኢትዮጲያ ግዛቶች ውስጥ የተከፈተው ህወሃታዊው ጸረ አማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ታላቁን ሰው አባታችንን ፕ/ር አስራት ወልደየስን አስነስቶ – የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅትን (መአሕድ) እንዱወለድ አደረገ። እስክንድር ያኔ በአፍላ ወጣትነት እድሜው ይህንን ታላቅ ንቅናቄን በመቀበል ላለፉት ሶስት አስርተ አመታት የዘለቀን የፖለቲካን ትግል የጀመረበት ወቅትና ሁኔታ ሆነ።

በዚህ ሶስት አስርተ አመታት የዘለቀና ለትውልድ ተሻጋሪ የሆነን አማራ ታሪኩን ያድሳል መሪ የመታጋየው መፈክር አድርጎ ለነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና መጀመሪያ በሰላ ብእሩ ለጥቆም ዛሬ ላይ በነፍጥ የታገለና ዛሬም እየታገለ ያለ እንቁ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ይህ ለቆመለት ሕዝባዊ አላማ እስከመሰዋት ባደረሰ ታማኝነት ጸንቶ ለሶስት አስርተ አመታት በኢትዮጲያ ምድር ውስጥ ሆኖ ሚዛኑን ጠብቆና የጽናት ተምሳሌት ሆኖ ለመቀጠል እስክንድርን ሆኖ መወለድን ይጠይቃል። በዚህ ሶስት አስርተ አመታት ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ተነስተው አይተናል። ለምሳሌ በ27ቱ ህወሃት መራሽ የኢህአዴግ ዘመን በትንሹ ከ600 በላይ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ከሀገር ለቀው ተሰደዋል። እስክንድር ግን በዚሁ የወያኔ ዘመን ዘጠኝ ግዜ ያህል እየታሰረ ሲፈታ ፣ እየታሰረ ሲፈታ የቆየ ቢሆንም ለሰከንድ ያህል ሁሉ ወደሚመኛት አሜሪካን ሄጄ ልኑር ብሎ እራሱን ከትግሉ ሜዳ ለማራቅ ያላሰበ አስደናቂ ሰው ነው። ብዙዎች አንዴ፣ ወይም ቢበዛ ሁለቴና ሶስቴ ታስረው ሲፈቱ ሙሉ በሙሉ ከሀገር በሚሰደዱበትና ወይም ሙያቸውንና አቋማቸውን ለውጠው ከጋዜጠኝነት መድረክ በሚጠፉበት ሁኔታ እስክንድር ደግሞ ደጋግሞ እየታሰረ ሲፈታ ሽንፈትን፣ ሽሽትን እና ስድተን ፈጽሞ አላውቀውም በማለት – ከሁሉም ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች የበለጠና የተሻለ አማራጭ እያለው – እግሩን ከሀገሩ ሳይነቅል፣ አላማውን ፣ አቋሙን ቅንጣት ሳያዝንፍ – ለቆመለት አላማና እና ለተነሳለት ሕዝብ እንደታመነ ድፍን ሶስት አስርተ አመታት የዘለቀ ብቸኛ ሰው ነው።

ትናንት ከሰላሳ አመት በፊት የአማራ መጨፍጨፍ አስቆጥቶትና አስቆጭቶት በአፍላ ወጣትነት እድሜው – ህይወት ምቹ ከሆነባት ሀገረ አሜሪካን ለቆ ወደ ኢትዮጲያ በመግባት የትግራዩን ጉጅሌ ፊት ለፊት – ያለአንዳች ፍርሃት- በብእሩ መፋለም የጀመረው መስመሩን ሳይስትና ዝብፍ ሳይል ዛሬ ከሰላሳ አመት በሃላም ይዞት የተነሳውን አማራ ታሪኩን ያድሳልን መፈክር እንግቦ ለነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና ትናንት በብእሩ እንደታገለው ዛሬ ደግሞ በነፍጥ ታግሎ በማታገል ላይ ያለ ድንቅ የዘመናችን ክስተት የሆነ ታጋይ ነው።

π ሩሲያን ከፈለጋችሁ ድርጅት ስጡኝና አስረክባችሃለሁ – ፍላድሜር ኤልች ሌኒን በ1915

የትኛውም የሆነ ምድራዊ ጭቆና ምድራዊን አመጽ ይወልዳል። የሚወለደውም አመጽ የሚገለጸው በድርጅታዊ መዋቅር ስር ታቅፎ ሲሆን ያለድርጅታዊ መዋቅር የሚፈነዳ አመጽ- ሕዝባዊ አመጽ ያመጸበትን ስርአት መገርሰስ ቢችል እንካን ስርአቱን ገርስሶ አዲስ ስርአት መመስረት ስለማይቻለው ውጤታማ አመጽ አይሆንም።

ትግል ያለድርጅት፣ ድርጅት ደግሞ ደግሞ ያለብቃት ያለው ባለ ራእይ መሪ ፈጽሞ ውጤታማ አይሆኑም። በ1915 አካባቢ በራሺያ የዛር ንግሳዊ አገዛዝ ላይ ታላቅ አመጽ በተነሳበት ወቅት ሌኒን በስደት ይንከራተት ነበር። እናም የሩሲያ አቢዮተኞች በስዊዘርላንድና በእንግሊዝ በስደት ላለው ሌኒን ለምን መጥተህ አትታገልም የሚል ጥሪ ሲያቀርቡለት ሌኒን የመለሰላቸው ምላሽ ድርጅት ስጡኝና እኔ ደግሞ ሩሲያን እሰጣችሃለሁ አላቸው። እናም አቢዮተኞቹ ቦልሼቪኮች ድርጅታቸውን እንዲመራ ሰጡትና በሌኒን መሪነት ቦልሼቪኮቹ ጥቅምት 17 ቀን 1917 የዛሩን መንግስት ገርስሰው የዛሬዋን የሩሲያን ፌዴሬሽንንን ለመመስረት በቁ።

የአማራ ፋኖ አደረጃጀት ዛሬ የተፈጠረ ክስተት አይደለም። ሀገራችን በፋሺስቱ ጣሊያን በተወረረችበት ወቅት እንቢ ለመብቴ፣ እንቢ ለነጻነቴ ብሎ የአማራ ፋኖ ለነጻነቱ ተፋልማል። በሀገራችን በ2010 ላይ ለተከሰተው የህወሃት መራሹን ሀይል ከስልጣን የማስወገድ ሕዝባዊ ትግል ላይ የአማራ ፋኖ ወሳኝ ትግል አድርጋል። ሆኖም አማራው እራሱን በጎበዝ አለቃ እያደራጀ በፋኖ አደረጃጀት ስርአቱን የታገለ ቢሆንም ትግሉን ወሳኝ መሪ ባለው ድርጅት ስላላካሄደው የትግሉን ፍሬ ተቋዳሽ ሳይሆን ቀርታል።

በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ የተመሰረተው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ይህን ወሳኝ የሆነውን ክፍተት በመሙላት አማራው ለመጀመሪያ ግዜ በማእከላዊ መንግስት ላይ በተደራጀ የፋኖ አደረጃጀት ጦርነት ከፍቶ ፍልሚያ እያደረገ ያለበት ሁኔታ ላይ የደረሰ ህዝብ ሆናል። የማታገያ ፕሮግራም (ማንፌስቶ) ቀርጾ በድርጅት ተዋቅሮ ( አፋሕድ እና አፋብኃ) መታገል ደረጃ ላይ የደረሰው ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ከአቻ አጋሮቹ እነ አርበኛ መከታው ማሞ ጋር ሆኖ በሸዋና በአፋር በረሃ ሆኖ በፋሺስታዊው የብልጽግና ስርአት ላይ ይፋዊ ጦርነት በማወጅ ሲሆን ዛሬ በአራቱም ክፍለ ሀገር በስምንት ያህል እዝ እና በሁለት ወሳኝ ድርጅቶች – አፋሕድ እና አፋብኃ – የፋኖ አደረጃጀቶች ታግሎ አታጋይነት ህዝባችን ለህልውናውና ለሁለንተናዊ ነጻነቱ እየታገለ ይገኛል-

——– ይቀጥላል

Filed in: Amharic