ብርጋድየሩ ምን እያሉን ነው?

ዲስ ተስፋ

ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት የትህነጉ ደብረጽዮን ‘’ከዐማራ ይልቅ ሱዳን ይቀርበናል’’ በማለት በትግሪኛ የተናገረው ንግ ግር በማህበራዊ ሚዲያው በሰፊው ሲዘዋወርና ሲጋራ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ደብረጽዮን በየትኛውም ን ግግሩ ነፍጠኛ የሚለውንና ለዐማራ የሰጡትን መጠሪያ ኮድ ሳይጠቀም የቀረበት ጊዜ ዉስን ነው። ለደብረጽዮንና ለድርጅቱ ትህነግ ዐማራ የትግራይ ጠላት ነው፤ ለትግራይ እድገት መጓተትና ሰለም መደፍረስ ተጠያቂ ነው። በሰውየው ስነ ልቦናም ሆነ አእምሮ ውስጥ የሞላው የዐማራ ጥላቻና የማይቀዘቅዝ በቀልና ደም የማፍሰስ ጥማት ነው። ደብረጽዮን ድርጅቱ ትህነግ በዐማራ ላይ ለሚከተለው የማይቀለበስ ፖሊሲና አቅጣጫ መግለጫ ሞዴል ብቻ ሳይሆን በዐማራ ላይ ለተፈጸመው ስርዓት ትኮር የዘር ማጥፋት ቀንደኛ አስፈጻሚዎች አንዱና ዋነኛው ነው።

ጌታቸው ረዳ በብኩሉ ምንም እንኳ ስለ ዐማራ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በየጊዜው የተለያዩ ቢሆኑም ከዐማራ ኤሊት ጋር ገና ያልተወራረደ ሂሳብ አለን የሚለው ንግግሩ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ከዚህ ይልቅ በፖሊሲውና በማኒፌስቶው ዐማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ሌሎችን ብሄር ብሄረሰቦችንም ቋንቋቸውንና ታሪካቸውን ሲቀማ የኖረ ጨቋኝ ነው የሚል የሃሰት ትርክት በመፍጠር ለዐማራ ህዝብ እልቂት ምክንያት የሆነውን ትህነግን በማእከላዊ ኮሚቴና በስራ አስፈጻሚነት ይመራ ስለነበረ የስርዓቱ አገልጋይ ነውና በዐማራ የዘር ጭፍጨፋ ዋና ተጠያቂ ነው።

ለማንሳት የፈለግሁት ዋና ጉዳይ የጌታቸውን ወይም የደብረጽዮንን ወንጀለኝነት መተንተን አይደለም። የዐማራ ህዝብ መከራ መነሻውና መድረሻው ለብልጽግናም ሆነ ለሌሎች ድርጀቶች ጸረ ዐማራ ስርዓት ተካዩ ትህነግ መሆኑንና የዐማራ ህዝብም ይህንን ከተረዳ መቆየቱን ለመጠቆም ነው። ዐማራ ባለበት አካባቢ ሁሉ ትህነግና ኦነግ የትግል ፍልስፍናቸውም ሆነ ግባቸው ዐማራን ማዳከም፣ ዐማራን ማጥፋትና ማፈናቀል መሆኑን ህጻን አዋቂው ጠንቅ ቆ ያውቃል። እያንዳንዱ ዐማራ የሚያከብረውና መሪየ የሚለው የትኛውም አካል ከትህነግ ወይም ከኦነግ ጋር ወይም ከሌሎች ዐማራን አምርረው ከሚጠሉ ብድኖች ጋር ግንኙነት መመስረቱን በሰማ ቅጽበት እንደ ’’………… የነካ እንጨት ‘’ እንደሚያየውና ወይም ደግሞ መስጊድ እንደ ገባች ውሻ ከሰጠው እውቅናም ይሁን ክብር እነደሚያባርረው ሳይታለም የተፈታ ነው።

የዐማራ የህልውና ትግል ፍትሃዊ ፣ ቅዱስና ሰብአዊነትን መልህቁ ያደረገ ለህግ የበላይነት ለእኩልነትና በነጻነት የመኖር መርሆዎችን የተከተለ የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙትን ግን ያለምንም ማመቻመች ወደ ህግ ለማቅረብ ያንን ጸረ ዐማራ ስርዓት የገነቡትን ድርጅቶችና ቡድኖች በጠላትነት የፈረጀ ማሸነፍንና ህልውናን ማረጋገጥን ያነገበ ጽኑና መራራ ትግ ነው።

በዚህ ሂደት ጠላቶቻችንን አጋር ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ ቡድን እንዳለ ብርጋድየር ጀነራል ተፈራ ማሞ በአደባባይ ሲነግሩን ያሳዩን ነገር የዐማራ የህልውና ትግል ምን ያህን ውስጡን ማጥራት እንደሚገባውና ከፍተኛ ስራ እንደሚጠብቀውም ጭምር ነው። ትህነግን አጋር ብሎ ለመጥራት ያላፈረና ያልቀፈፈው ግለሰብ ልዩ የሆነውን የዐማራ የህልውና ትግንል በጦር አዛዥነት ለመምራት በምን መንገድ ኢዚያ ደረሰ ብለን መጠየቅና የትግሉን ንጽህና መጠበቅ የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነን ። ብ/ጀ ተፈራ “ሸማቂው ኮማንዶ “ በተሰኘውና በህዳር 2013 ዓ/ም በታተመው መጽሃፋቸው ገጽ 44 ላይ ስለትውልድ ሃረጋቸው እንዲህ ይሉናል። ‘’በአባቴ በወንዶቹ ወገን ቅድመ አያቴ የሆነው ተክሉ ጓንጉል የትግራይ ዘር እንዳለበት አባቴ እየደጋገመ የትግሬ ዘር አለብኝ ይልኝ ነበር። መነሻ አካባቢውም እንድርታ አውራጃ ልዩ ስሙ መሃል እንድርታ እንደነበር ይነግረኝ ነበር ።በሆነ አጋጣሚ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ወደ አካባቢያችን ከምጡ ክርስቲያን ወገኞቻችንና የዘር ሐረጎቻችን ናቸው እያለ ያወጋኝ ነበር።

ጉዳዩ ብርጋድየር ጀነራሉ ከትግራይ ጋር የደም ንክኪ መኖሩ አይደለም። ቀደም ሲልም አፍቃሪ ትህነግ መሆናቸውና የዐማራ ጨቋኝ ነው ትርክት ሰለባ መሆናቸው በግልጽ መታየቱ ነው። በእርግጥ ትንሽ ስጋ እንደ መሪፌ ትዎጋ የሚለውን አባባል ማስታወስም ተገቢ ነው። ምክንያቱም የትህነግ የትግል ፍልስፍና ትግሬ መሆን ስለሆነ ፤ፖለቲካዊ ትግሬነት። ብርጋድየር ጀነራሉ እነደብረጽዮን የዐማራን ፍላጎት ያከብራሉ የዐማራን ህዝብ ይወዳሉ ብለው ሲናገሩ ትናንትና በ አንድ ውይይታችን አንድ ወንድም እንደተናገረው ሞንጆሪኖ ራሷ ወይም ደብረጽዮን ራሱ ይህንን ንግግር ቢሰሙ ኧረ እ ኛ ያልከውን አናምንበትም ን ግ ግርህን አስተካክል ዐማራን እንጠላለን ታሪካዊ ጠላታችንን እንዴት አጋር ትላለህ ብለው ይቆጡታል ሲል ፈገግ አስብሎናል።

ማጠቃለያ : የዘፈን ዳርዳርታው እስክስታ ነው እንዲሉ ዘር ጨፍጫፊዎችን ነጻ ለማድረግ በአጋርነት ስም ሊሰራ የታሰበውን ፖለቲካዊ ሻጥር መበጣጠስና ህሊና ቢስ የሆኑ ግለሰቦች የሚተፉትን መርዝ ማርከስ ያለብን የትግል ምእራፍ ላይ ነን። ትህነግንና የመሳሰሉ በዐማራ ደም የተጨማለቁ የፖለቲካ ቡድኖችን ወደ ፍርድ ማምጣት እንጂ አጋር የማድረግ አላማ ያለው የዐማራ ትግል የለም። ከዘር ጨፍጫፊው ቡድን ጋር አጋር የሆነ ድርጅት ወይም ቡድን በየትኛው የታሪክ ምእራፍ የለም። ከአውድ ዉጭ የፖለቲካ ቲዮሪ በመጥቀስ ዐማራ ከዘር አጥፊዎቹ ጋር ድርድር ማድረግ ወይም አጋር መመስረት አለበት የሚል ትንታኔ ለመስጠት የምትሞክሩ ያለ አዋቂ አዋቂዎች ራሳችሁን ባታስገምቱ መልካም ነው። ዐማራ የፖለቲካ ምርጫ ላይ ሳይሆን የህልውና ትግል ላይ ነው። ህልውናውን አረጋግጦ ግን በእ ኩልነትና የህግ የበለይነት የሚያምን የፖለቲካ ማህበረሰብ ይፈጥራል። በእውነትና በፍትህ የታጀበ አጋርነት ከየትኛውም በሃገሪቱ የሚኖር ማህበረሰብ ጋር ይመሰርታል።እሴቶቹንና ማንነቱን ለማስከበር የሚታገለው ዐማራ የጀመረውን ጽናትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በማንነቱ የማያፍር ብቻ ሳይሆን የኮራና በራሱ የሚተማመን ትውልድ የመፍጠር ሂደቱን ማንም አያስቆመውም። ምስጢሩንና የትግል ስትራቴጂውን ለመሰለል የገቡ ውስጣዊ አርበኞችንም በአንክሮ ሊከታተላቸው ይገባል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.