>

ኦህዲድ በህግ ስም የተቀባበለችውን ጥይት አከሸፈ (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

አንዳንድ ወገኖች በህግ ስም ኦህዲድን ከጨወታ ውጪ ለማድረግ በጣም ተዘጋጅተው ነበር።
ታስቦ የነበረው ኦህዲድ ለማን ቢያቀርብ የፖርላማ አባል በለመሆኑ የህግ አሰራር በመደንቀር ኦህዲድ እና ኦሮሞን ከጨወታ ውጪ ለማድረግ ነበር።
ለማ መገርሳ ይህ ስለገባው የሚወደው ህዝቡን እና ሀገሩን በማስቀደም ስልጣኑን የሱን ያህል ብቃት ላለው ሰው አሳልፎ ሰጥቷል።
ድርጅቱም ይህንኑ ተቀብሎ አፅድቋል። ክብር ህዝብ እና ሀገርን ከስልጣኑ ላስቀደመው ለለማ መገርሳ ይሁን።

 ¤¤¤¤

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶ/ር ወርቅነህን በማሰናበት ዶ/ር አብይን የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን አመራር ምደባ ማስተካከያ አደረገ።
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት፣ ተሳትፎ ለማጠናከር እና በክልል እና ሀገር ደረጃ የተጀመሩ ማሻሻያዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ኦህዴድ እና የክልሉ ህዝብ የጀመረው ትግል አሁን ከደረሰበት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲባል የአመራር ምደባ ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
የአመራር ምደባ ማስተካከያውም በኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መፅደቁን ድርጅቱ አስታውቋል።
በዛሬው እለት የተመረጡት አመራሮችም የክልሉን እና የሀገሪቱን ህዝቦች ጥቅም የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ታምኖባቸዋል ብሏል ድርጅቱ።
በመሆኑም የኦህዴድ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ የክልሉ እና መላው የሀገሪቱ ህዝብ ከኦህዴድ ውሳኔ ጎን በመሰለፍ በሀገር ደረጃ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመዘገብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከድርጅቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።
Filed in: Amharic