>

ለአየር ሀይሉ የጎጥ አሰራር ምቹ ባለመሆናቸው ብቻ የበቀል ጅራፍ የሚጮህባቸው መኮንኖች (ጌታቸው ሽፈራው)

መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መቶ አለቃ ገዛኸኝ ድረስ፣ መቶ አለቃ ዳንኤል፣ መቶ አለቃ ብሩክ እንዲሁም መቶ አለቃ አንተነህ  ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ ያልታወቀ ቦታ ታስረዋል።
በወቅቱ አየር ኃይል ውስጥ ያለውን ዘረኝነት ለመርማሪዎቹ በሚገባ ነግረዋቸዋል። እነ ሳሞራ በቪዲዮ ተቀርፆ እንዲላክ ባሉት መሰረት አምስቱም የአየር ኃይል መቶ አለቃዎች አየር ኃይል ውስጥ ስላለው ጎጠኝነት የተናገሩት የሰራዊቱ አባላት በስብሰባ እንዲያዩት ተደርጓል ተብሏል።
እነ ማስረሻ  በምርመራ ወቅት ስለ አየር ኃይሉ ውድቀት የተናገሩት ይጠቅማል ተብሎ የአየር ኃይል አባላት “ሂስና ግለ ሂስ” ማውጫ ሲውል አምስቱም መቶ አለቃዎች ይለቀቃሉ ተብሎ ነበር። ሆኖም  እያንዳንዳቸው 10 አመት ተፈረደባቸው። መቶ አለቃ ማስረሻ፣ መቶ አለቃ ዳንኤልና መቶ አለቃ አንተነህ በቃጠሎው እጃችሁ አለበት ተብለው ተጨማሪ  የሀሰት ክስ ተሰጣቸው። መቶ አለቃ ዳንኤል  በቆመበት በእስር ቤት ፖሊሶች በጥይት ተመትቶ ቆስሏል።
መቶ አለቃ ማስረሻ ዳርፉር ግዳጅ ላይ በነበረበት ወቅት አየር ላይ ሞተሯ ያቆመ ሄሊኮፍተርን፣ እንዲሁም መቶ አለቃ ገዛኸኝ ድረስ ሀገር ውስጥ ሁለቱም መተሩ የተበላሸ ጀትን በሰላም ያሳረፉ ብቁ አብራሪዎች ናቸው። ለዚህም መከላከያ ዶክመንተሪም ሰርቶላቸዋል። እነኚህ ጀግና አብራሪዎች ታስረው  ገና ሲነሳ ሄሊኮፍተሩን መሬት ላይ ካሉት ጋር እያጋጨ በአንዴ 3 ዘመናዊ ሄሊኮፍተር የሚያወድም አብራሪ በጎጡ ምክንያት “አብራሪ” እየተባለ ነው። አዛዦች የሚባሉትም መሰሎቹ ናቸው።
እነዚህ ጀግና አብራሪዎች ዛሬ በእስር ላይ ናቸው። በእርግጠኝነት ነገ ይፈታሉ!  በእርግጠኝነት በቀጣዩ ዘመን   ኢትዮጵያ ትፈልጋቸዋለች!
Filed in: Amharic