>

ሲራጅ ፈርጌሳ የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ተጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የተቃረበ ይመስላል (ኤርሚያስ ለገሰ)

 

#ምክንያት አንድ: ለትግራይ ነፃ አውጪ ከደመቀ መኮንን ሲራጅ ፈርጌሳ በሁለት እጥፍ አድርባይ ነው።

#ምክንያት ሁለት: ሲራጅ ፈርጌሳ ከደመቀ መኮንን በላይ ለትግራይ ነፃ አውጪ ጄኔራሎችና የጦር አዛዦች የቅርብ ቅርብ ታዛዥ ነው። ሳሞራ የኑስ የሲራጅን ብሔረሰብ እየጠቀሰ በማንነቱ ላይ ሲሳለቅበት እንኳን አንገቱን ደፍቶ የሚኖር ሰው ነው።

#ምክንያት ሶስት: የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር እሳት በጐረሱ እና የቆሰለ አውሬ በሆኑ ካድሬዎቹና አባላቱ ” አማራ ወይም ኦሮሞ አንግሶ አንገታችንን አስደፋ!” ብለው ፊቱን ከሚያዞሩበትና ጉድጓድ ከሚቆፍሩበት ሲራጅን ቢሾም ያዋጣዋል።

#ምክንያት አራት: ደመቀ መኮንንን መምረጥ በተዘዋዋሪ ጓድ በረከት ስምኦንን መሾም ስለሚሆን የደብረፂዬን እና አርከበ ቡድን ፍቃደኛ አይሆንም። (ብአዴን ለበረከት የፌስ ቡክ ማስተባበያ ባወጣት አንዲት አንቀፅ ውስጥ ሰባት ጊዜ ” ጓድ” እና ” ጓዳችን” መጠቀሙን ልብ ይሏል።)

#ምክንያት አምስት: ሲራጅ ፈርጌሳ የፈለገ ቢፍጨረጨርና የመስዋእት በግ ቢሆን እንኳን በደቡብ ክልል ውስጥ ማህበራዊ መሰረቱን ከ2 በመቶ በላይ ማሳደግ አይችልም። የተፈጠረበት የስልጤ ብሔረሰብም ከህውሃት/ ኢህአዴግ ጋር ሙሉ ለሙሉ ከተቆራረጠ 4 አመት ስለሞላው ሲራጅ ፈርጌሳ በራሱ ብሔረሰብ የተጠላ ሰው ሆኗል። ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሐድያ…ወዘተ የሆኑ ካድሬዎች እና አባላት ወርቅ ቢያነጠፍላቸው እንኳን መቀመጫህን ላስ ማለታቸው አይቀርም። በሌላ በኩል የሲራጅ ፈርጌሳ መጠላትና ህዳጣን መሆን ለህውሃት ትልቅ እድል እና ደስታ የሚፈጥር ነው።

#ምክንያት ስድስት: ደኢህዴን የስልጣን ዘመኔን መጨረስ አለብኝ የሚል መከራከሪያ በኢህአዴግ ምክርቤት ሊያቀርብ ይችላል። ደመቀ መኮንን የሜቴክ የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆን ታሳቢ የተደረገው የመከላከያ ሚኒስትር ሊሆን ነው ተብሎ ሾልኮ የወጣውን መረጃ የሲራጅን ጉዞ ያመቻችለታል።

#ምክንያት ሰባት: ሲራጅ ፈርጌሳ የፓርላማ አባል ነው። ዶክተር አቢይ የፓርላማ አባል መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም ” የስልጣን አተያይ ችግር እና ተራ ሕዝበኝነት” በሚል በቀጣይ ቀናት በኢህአዴግ ምክርቤት ግምገማ ቁምስቅሉን አሳይተው ህውሃትን እና በረከትን ይቅርታ በመጠየቅ ከውድድር ሊወጣ ይችላል።

በተያያዘ ኢትዮሪፈረንስ:-

ደኢህዴን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን እና አቶ ደሴ ዳልኬን በሊቀ-መንበርነት እና ምክትል ለሊቀ-መንበርነት በመምረጥ ስብሰባውን አጠናቋል!!

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በፌዴራል መንግስቱ የተጣለባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሃላፊነት እንዲሁም ኢህአዴግንና ደኢህዴንን በሊቀ-መንበርነት በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ኮሚቴው ምስጋናውን አቅርቧል። የሚቀጥለው አገራዊ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ላሉት ሁለት አመታት ድርጅቱን በሊቀ-መንበርነት እና ምክትል በሊቀ-መንበርነት እንዲያገለግሉ አቶ ሲራጅ ፈጌሳን እና አቶ ደሴ ዳልኬን በመምረጥ ስብሰባውን አጠናቋል።

የደኢህዴን ጽሕፈት ቤት

Filed in: Amharic