>
7:55 am - Wednesday July 6, 2022

"...አልሙዲ ቂመኛ ነው። ተከታትሎ እንዳይበቀለኝ ብቻ አድርግልኝ እኔ ፖለቲካ ውስጥ አልገባም..." ታምራት ላይኔ

አርአያ ተስፋማርያም
አቶ ታምራት ላይኔ 18 አመት ከተፈረደባቸው በኋላ ድጋሚ ተከሰሱ። የተከሰሱት በአቶ መለስ የተላከባቸውን የድርድር “ሃሳብ” አልቀበልም በማለታቸው ነበር። “በስዬ ላይ በሃሰት መስክርና እንፈታሃለን፣ ወደ ውጭ እንልካሃለን” ተባሉ። 5 ጊዜ ከመለስ የተላኩ ደህንነቶች እስር ቤት እየሄዱ ጠይቀዋል። አሻፈረኝ ስላሉ .. ከስዬ ጋር ድጋሚ ተከሰሱ። ፍ/ቤት ሲቀርቡ ይህንን ድራማ አጋለጡ። ፍ/ቤት ውለው ሲሄዱ የወህኒ ቤቱ አዛዥ በጥፊ እንደተመቱ ገለፁ። (የታምራት ጥፊ በሚል ርእስ ከዚህ ቀደም ስለተፃፈ አልመለስበትም)..አቶ ታምራትን ያወቅኳቸው ፍ/ቤት ሲሆን በጥንቃቄ ፅሁፍ ያቀብሉኝና በጋዜጣ ይወጣ ነበር።..በድጋሚ በተከሰሱበት የአንድ ወር እስራት ተቀጡ። 18 አመት ከ1 ወር ሆነ። ..በ2001 ዓ.ም መጨረሻ በረከትና አዲሱ ለገሰ ለመለስ ሀሳብ ያቀርባሉ። “ታምራት ይፈታ” ይላሉ። “ፖለቲካ ውስጥ እንደማይገባ ማረጋገጫ ይስጥ” ይላሉ መለስ። በረከትና አዲሱ ወህኒ ቤት ወርደው ታምራትን በማናገር መለስ ያሉትን ይናገራሉ። ታምራት ይስማሙና በተፈቱ እለት እዛው ወህኒ እንዳሉ በቲቪ ቀርበው ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ እንደማይገቡ ማረጋገጫ ይሰጣሉ።..ታምራት በተፈቱ በሳምንቱ በረከትን ደውለው ካገኙ በኋላ ከመለስ ጋር መገናኘትና ማውራት የሚፈልጉት ጉዳይ እንዳለ በመግለፅ ቀጠሮ እንዲያስዙላቸው ይጠይቃሉ። በረከትም የተባሉትን ያደርሳሉ። ቅዳሜ ምሽት ቤተ መንግስት ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ለታምራት ይነገራቸዋል። አዜብ መስፍን “ራሴ ነው እራት የማዘጋጀው” ይላሉ። በድግሱ ምሽት ታምራት በተላከላቸው መኪና ቤተ መንግስት ደርሰው ከመለስ ጋር ተቃቅፈው የእራት ግብዣው ይቀጥላል። ተፈራ፣ ህላዊ፣ በረከት፣ አዲሱ..ተገኝተዋል። እየተበላ.. እየተጠጣ እያለ ታምራት ላይኔ መለስን ማናገር እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። …ታምራት እንዲህ አሉ..
..በቤተመንግስት የእራት ግብዣ አቶ ታምራት ከተጠቀመጡበት ተነስተው መለስን በግል ለማናገር ተለዩና “መለስ ቂም የለኝም! ከአገር እሄዳለሁ። ስለፓርቲው ምንም አልልም። በማንኛውም ፓለቲካ ውስጥ አልገባም። አንድ ነገር ብቻ እለምንሃለሁ..አልሙዲ ቂመኛ ነው። ተከታትሎ እንዳይበቀለኝ ብቻ አድርግልኝ” ሲሉ ተማፀኑ። መለስ በታምራት ሀሳብ ተስማምተው የሼኹን ጉዳይ “በእኔ ተወው” አሉ። መለስ ጫማቸው ስር ተቀናቃኝ ያሉትን “ማስተኛት” ደስታ ይሰጣቸዋል። ..ታምራት ለሌሎቹም በፀሎት እንደሚያስቧቸው፣ የኢየሱስ አገልጋይ እንዲሆኑ ..ቡራኬ አሰምተው ግብዣው አለቀ። ..በዛ ሰሞን በግል ጋዜጦች የተጠየቁት ታምራት ፓለቲካ እርም ማለታቸውን፣ ከዚህ ይልቅ ስለኢየሱስና እርቅ እንደሚሰብኩ ተናገሩ። እርግጥ ነው በጣት ከሚቆጠሩት በቀር አብዛኞቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት “እግዚአብሔር የለም” ብለው ያምናሉ።..ታምራት ትንሽ ቆይተው አሜሪካ ዴንቨር መጡ። “ሼኹ እንዳይበቀለኝ” ያሉት 16 ሚሊዮን ዶላር በመንግስት ስም ተበድረው፣ በልጃቸው ስም ስዊዝ ባንክ በማስገባታቸው ነበር። አንድ ከፍተኛ የአቃቤ ህግ ሃላፊ በመንግስት ተወክለው ገንዘቡን ለማስመለስ ሄደው ነበር። ግን አልተሳካም። (ሃላፊው እዚህ ፌስቡክ አሉ..ዝርዝር መረጃ ማወቅ ከፈለጋችሁ በቅርብ ልመለስበት እችላለሁ.) አቶ ታምራት ያሳዘኑት ህዝብ ቢኖርም ይቅርታ ሳይጠይቁ እስካሁን አሉ። “እርቅና ስለኢየሱስ ብቻ እሰብካለሁ” ያሉት ታምራት ከዚህ ይልቅ በተቃራኒው መንገድ መታየታቸው ብዙዎችን አስገርሟል!..የመሰላቸውን ሀሳብ የመግለጽ መብት አላቸው! ቢሆንም ዘርና ጎጥ እየሳቡ “እከተለዋለሁ” ከሚሉት እምነት ጋር የሚጋጭና በተለይ የአምላክ ህግጋትን የሚጋፋ መርዝ መርጨት አስነዋሪ ነው ይላሉ ታዛቢዋች። በምስራቅ ኢትዮጵያ በእሳቸው ንግግር የተፈፀመውን ዘርና ብሄር የለየ ጥፋት ፍ/ቤት አልቀስው የተናገሩትን ..ዛሬ እረስተው ዳግም የጥፋት መርዘኛ ቃል መርጨት እጅግ አሳዛኝ ነው!
Filed in: Amharic