>

መተማን ለሱዳን የሸጠው ደመቀ መኮንን ነው (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን ሊፈጥረው የሚችለውን 

በመገንዘብ ለቀጣይ ትግል መዘጋጀት ይኖርበታል

–   መተማን ለሱዳን የሸጠው ደመቀ መኮንን ነው 
ሰሞኑን ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን በተናጠል ባካሄዱት ስብሰባ ሊቀመናብርቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን ብአዴንን የወከለው ደመቀ መኮንን ሆኗል። ደመቀ ማን ነው? ቀጣዩን ሀጢያቱን ብቻ እንመልከተው
የሕወሐት አመራሮች ትልቁ ችግራቸው ለሱዳን እየተሰጠ ያለው መሬት የአማራ እንጂ የኛ አይደለም ብለው ማመናቸው ነው።
ወዳጆቼ የኛ መከራ ብዙ ነው ህዝባችን ብቻ ሳይሆን መሬታችንም አብሮ መሰደድ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል ሌት እህቶቻችን ወደአረብ ሐገራት መሬታችን ደግሞ ወደሱዳን መሰደዳቸውን ተያይዘውታል። የመሰደድ አባዜ ይዞን ሉሲ እንኳን ተሰዳ ነው የተጎበኘችው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ቅርስ ቱሪስት ፍለጋ የተሰደደው
ሠው ከሀገሩ ከወጣ ቀን ሲሞላ ለመመለስ የትራንስፖርት ገንዘብ ብቻ ነው የሚመለስው መሬት ከተሰደደ ድንበር ከተሰደደ ግን ለመመለስ የበርካታ ወጣቶችን ደም ይፈልጋል።
ህወሀቶች ከሰሜን ከአማራ ክልል ጀምሮ ምእራብ ኦሮሚያ እና ምእራብ ጋምቤላን ከኢትዮጵያ ካርታ ላይ ለመነጠል ንግግር የጀመሩት ዛሬ አይደለም ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ሱዳን እራሷ ለሁለት በመገንጠሏ በጋምቤላ ትይዩ የምትገኘው ደቡብ ሱዳን በጋምቤላ መሬት ላይ ያነሳችው ጥያቄ ስለሌለ ለጊዜውም ቢሆን የጋምቤላው መሬት ጉዳይ ጋብ ያለ ይመስላል የምእራብ ኦሮሚያና የአማራ መሬትን ግን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ከቀናት በዃላ የሕወሐት መሪዎች ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ይፈራረማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው ይህ በሀገርና በህዝብ ላይ የሚፈፀም ትልቅ ወንጀል ነው እነዚሁ የሕወሐት መሪዎች ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልል እየተቆረሰ ለሱዳን የሚሰጥ መሬት የአማራና የኦሮሞ እንጂ የኛ አይደለም የሚል እጅግ አስነዋሪ አመለካከት ተጠናውቷቸዋል።
የኢትዮ ሱዳን ድንበር ንትርክ መቼ ተጀመረ
በዳግማዊ አፄ ምንሊክ ዘመን በወቅቱ የሱዳን ቅኝ ገዢ የነበረችው የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነው ጉዌን የተባለ ግለሰብ ያለማንም ፈቃድ የሱዳንን ካርታ አዘጋጅቶ ለእንግሊዝ መንግሥት ያቀረበ ሲሆን የእንግሊዝ ነገሥታቶች በካርታው ዙሪያ ከኢትዮጵያው ንጉሥ አጤ ምንሊክ ጋር ሳይስማሙ በመቅረታቸው የእንግሊዝ ፍላጎት ሳይሳካ ቀረ ሆኖም ጊዜ እና ዘመን ሲጠብቁ የኖሩት የሱዳን መሪዎች ፀሎታቸው ሰምሮ ኮትኩተው ያሳደጉት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ የቆመ ሕወሐት የተባለ መንግስት አገኙ ጫካ እያሉ እኔ የትግራይ ገዢ እንጂ የተቀረው የኢትዮጵያ መሬትን ጉዳይ እንደፈለጋችሁ በሚሉ ምክንያቶች ስምምነቶች ላይ የተፈራረሙ በመሆኑ ሕወሐት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ይህ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ቀን ሲጠብቁ ኖረው ዛሬ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሰዋል።
ለሱዳን የሚሰጠው መሬት ከጎንደር ተነስቶ ኦሮሚያን ቆርሶ የጋምቤላ ምድር ድረስ የሚደርስ ሲሆን ርዝመቱ እስከ1600 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ይህም ማለት ምን አልባት ከአዲስ አበባ ዳሕላክ ወደብ የሚደርስ መሬትን ያህል እኩሌታ ማለት ነው። ይህ ለሱዳን የሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት የሚከተሉትን ከተሞች የያዘ ነው። እነርሱም 1, መተማ 2, ኮኪት 3, አፍጥጥ 4, ገንደውሀ 5, መቃ 6, ደረቅ አባይ 7, ኩመር 8, አውላላ 9, ነጋዴ ባህር ናቸው።

ይህ የሚሰጠው መሬት ወደኢትዮጵያ ድንበር ከ47 እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሆኑም ታውቋል ሌላው አስደንጋጩ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አጤ ቴዎድሮስ የተማሩበት ማህበረ ሥላሴ የተሠኘው ገዳምም በድንበር ማካለሉ ስምምነት ምክንያት የሱዳን አካል የሚሆን ሲሆን አፄ ዮሐንስ ከሱዳን ማህዲስቶች ጋር ጦርነት ላይ በነበሩበት ወቅት የተሰዉበት ሞፈር ውሃ የተሰኘው ታሪካዊ ቦታም አብሮ ለሱዳን የሚሰጥ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ በድንበሩ ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን እንዲለውጡ ወይም አካባቢውን ለቀው ሊሰደዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።
ከላይ እንደገለፅኩት የሕወሐት መሪዎች ትልቁ ችግራቸው ለሱዳን ተላልፎ የሚሰጠው መሬት የአማራና የኦሮሞ እንጂ የኛ አይደለም የሚል የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ መግባታቸው ነው።
የህወሐት መሪዎች ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ጉዳይ የተፈራረሙት እኛ ሳንሆን የቀድሞ የኢትዮጵያ ገዢዎች ናቸው ይሉናል ማስረጃ ግን አያቀርቡም ማስረጃ አቅርቡልንና እንመናቹህ
ወዳጆቼ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ከሕወሐት መሪዎች ውጭ ድንበሩን ለሱዳን ለመስጠት የተስማማ የኢትዮጵያ ገዢ የለም ሌላው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የምሆንላቹህ ዝም ብለን ከተቀመጥን በቅርቡ መሬት ለሱዳን ይሰጣል ያኔ ማፈር የሚኖርበት ሕወሐት ሣይሆን እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን ነን።
ከእነዚህ ሁሉ የመሬት ሽያጭ ጀርባ ሁሉ የህወሃት ተላላኪ የነበረው አቶ ደመቀ መኮንን ነበረ፤ ይህ ግለሰብ ደመቀ መኮንን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር በማድረግ የኢትዮጵያን ፈተና እና የህወሃትን የበላይነት ለማስቀጠል ውስጥ ውስጡን እየተሰራ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ጉዳዩን ሊከታተለውና የደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን ሊፈጥረው የሚችለውን በመገንዘብ ለቀጣይ ትግል መዘጋጀት ይኖርበታል።

Filed in: Amharic