>

ወያኔ-(ህወሓት ) በወሎህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ(ተንኮል) በጥቂቱ (ከይርጋለም ታደሠ) 

1. ራያአዘቦ ከወሎ ገንጥሎ በጉልበት ወስዷል!!
2. አውሳ የወሎ አማሮች እና አፋሮች በጋራ የሚኖሩበት
ምድር ሆኖ ሳለ ወያኔ ግን አማራን አውሳ ላይ ሁለተኛ ዜጋ
እንዲሆን አድርጎታል!!
3. #የወሎ ክፍል የሆነውን #የአሰብ ወደብን በመሰሪነት
ለኤርትራ እንዲወስድ አድርጓል!!
4. በ1984 700,000 (ሰባት መቶ ሺህ) የወሎ ህዝብ
ከአሰብ እና ከቀይ ባሕር ከተሞች
እንዲፈናቀሉ ምክኒያት ሁኗል!!
5. 700,000 የወሎ ህዝብ ከአሰብ እና አካባቢው
ሲፈናቀሉ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ለዘመናት ያፈሩት ንብረት
ተወስዶባቸዋል፣ ብዙ ወጣቶችም በመንገድ ላይ እንዲረሽኑ
ተደርጓል!!
7. የአሰብ ተፈናቃዮች የጥርስ ወርቅ በሰደፍ እየተመታ የጣት
ወርቅ ደግሞ ጣት እየተቆረጠ እንዲወጣ በማድረግ
በአካላቸው ላይ ዘግናኝ ግፍ ተፈጽሟል!!
8. የዚህ ሁሉ ግፍ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግሥታት
(UNITED NATION) በ1985 መጀመሪያ ላይ እንዲጣራ
ቢያዝም መለስ ዜናዊ ግን በባንዳው እንድሪያስ እሸቴ
አማካኝነት “ወታደር እንጂ አማራ አልተበደለም” አስባለ!!
በመሠረቱ እንድሪያስ እሸቴ ለሰራው ታሪካዊ ቀይ ስህተት
ከ13 ዓመት በሗላ በ1997 ይቅርታ ጠይቋል። ምን ዋጋ
አለው!!
9. ደሴ የሚገኘውን የብዙ ታሪክ ባለቤት የሆነውን ወ/ሮ
ስህን ትምህርት ቤት ስሙን እንዲቀየር አድርጓል። በሕዝቡ
ጩከት እንደገና ስሙ ቢመለስም የትምህርት ቤቱ የአሁኑ
ሥራ እና ታሪኩ እንዳይገናኝ አድርጓል።
10. የንጉሥ ሚካኤል ቤተመንግሥት እንደ አፄ ዮሐንስ
ቤተመንግሥት ሙዚየም መሆን ሲገባው ሬዲዮ ፋና የሚባል
ገብቶበት ቤተመንግሥቱ ውስጥ የብልግና እና የማይጠቅም
ወሬ ቤት አድርጎታል!!
11. የደሴ ሕዝብ የጄኔራል ሁሴን አህመድን ታናሽ ወንድም
በምርጫው መርጦ ለፓርላማ ስለላከ ብቻ ጠላት ወያኔ
ከወደብ መጥቶ በደሴ በኩል ወደ መቀሌ የሚያልፈውን
መንገድ በመዝጋት ሌላ መንገድ በበረሃው ከፈተ። የዚህ
ዓላማው ደሴን በኢኮኖሚ መጉዳት ነው!!
12. አልተሳካም እንጂ የደሴን ሕዝብ በሃይማኖት ከፋፍሎ
ለማጨፋጨፍ አቅዷል፣ ተንቀሳቅሷል፣ ሰርቷል።
13. #ላሊበላን የሚያክል ታላቅ የታሪክ እና የሃይማኖት ሀገር
ጠላት ወያኔ የቱሪዝም ገቢዋን እየዘረፈ ግን ምንም አይነት
መሠረት ልማት እንዳይኖራት አድርጓል!!
14. በሰሜን ወሎ በተለይም በሰቆጣ እና በአካባቢው በውሃ
ብቻ መከላከል በሚቻለው በትራኮማ ምክንያት ROTARY
CLUB “አስደንጋጭ!” ያለው የአይነስውርነት እንዲከሰት
አድርጓል!!
15. በድፍን ወሎ ከባድ #ስራአጥነት በማስከሰት እና ተስፋ
እንዳይኖር በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴት ልጃገረድ
እህቶቻችን እና ወንድ ወንድሞቻችን #ለስደት፣ ለእንግልት፣
ለባርነት እና ለሞት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል!!
16. በደሴ ከተማ #በነጋዴው  ላይ ከፍተኛ ግብር
በመጣል ለድህነት፣ ለአይምሮ በሽታ እና ለስደት ዳርጓቸዋል!!
18. በወልዲያ፣ በሐይቅ፣ በኮምቦልቻ እና በደሴ ወጣቱ
ከፍተኛ የሆነ #የሱስ #ተጠቂ እንዲሆን አድርጓል። ለምሳሌ
በ2005 የሐይቅ ከተማ ፖሊስ የሺሻ ማጨሻ ቤቶችን እና
ጫት መቃሚያ ቦታዎችን ሊያሽግ ሲንቀሳቀስ በወያኔ አለቆች
ተከልክሏል።
18. አካባቢው በማዕድን በተለይም በብረት ማዕድን የበለፀገ
እንደሆነ ቢታወቅም እስከአሁን ጠላት ወያኔ “የሕዝቡ
ኢኮኖሚ ከተሻሻለ አይገዛልኝም” በማለት ሕዝቡ ተጠቃሚ
መሆን አልቻለም።
19.በሻምበል አሊ ሙሳ አማካኝነት ደሴ ላይ ተተክሎ የነበረ ጄኔሬተር ነቅው ወስደዋል!!
20. አበርገሌን በሙሉ የነሱ ለማድረግ ወያኔ አሰፍስፈዋል።
21. ከ4 ዓመት በፊት ኮምቦልቻ ላይ አላህሙዲን
የብረታብረት ፋብሪካ ልሥራ ቢል ወያኔ “ቆይ አሁን ሃይል
የለም፤ አባይ ሲጠናቀቅ” አሉት። ከዚያ በሗላ ግን እነሱ
–ውቅሮ ላይ በ6 ቢሊዮን ብር ብረት ማቅለጫ ገነቡ።
–መቀሌ ላይ በ4.5 ቢሊዮን ብር ኢንጅን ፋብሪካ ገነቡ
–መቀሌ ላይ በ200 ሚሊየን ዶላር የፔጆ መኪና ፋብሪካ
ገነቡ።
–አዲግራት ላይ በ2.5 ቢሊዮን ብር ማርብል ፋብሪካ ገነቡ።
–መቀሌ ላይ በ5 ቢሊዮን ብር የጀርመን ከባድ መኪና
መገጣጠሚያ ገነቡ።
–መቀሌ ላይ በ800 ሚሊየን ብር የኢንደስትሪ ኮሌጅ
እየገነቡ ነው።
–መቀሌ ላይ በ9.5 ቢሊዮን ብር የኬሚካል እንዱስትሪ
ከ70% በላይ አጠናቀዋል።
–መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን አስፋፉ
–መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂኔሪንግን በእጥፍ አስፋፉ።
አሳዛኙ ነገር ይህ ሁሉ የሚሆነው ኮምቦልቻ ላይ ሃይል የለም
አባይ ሲጠናቀቅ ይሰራል ብለው አንዲት ፋብሪካ እንዳይሰራ
ከከለከሉ በሗላ መሆኑ ነው።
22. ወሎ ውስጥ ከፍተኛ የሆነው ስረዓት ሰራሽ ድህነት በሰፊው ከገጠር እስከ ከተማ ተንሰራፍቶ ይገኛል። ወጣቶች ዘንድ የድህነት እና ተስፋ መቁረጥ ተከትሎ ወጣቱ ትምህርት እያቋረጠ አረብ ሀገራት እንዲሰድ የበርሀ ፣ የውሀ እና የህገወጥ ደላላ ሰለባ እንዲሆን ውድ ህይወቱ እንዲቀጠፍ ተደርጓል።
23. እድል ቀንቶት አረብ ሀገር የደረሰ ወጣት ደግሞ በወያኔ የሚላኩ ዋልጌ ዱርዩዎች በሚላኩ ሰዎች አረብ ሀገራት ውስጥ ህገወጥ ስራ ላይ አሰማርቶ ኢትዮጵያኖችን እንዲባረሩ፣ እንዲጎሳቆሉ አድርገዋል።
ይሄ ሁሉ ያለፈውን ሰሳንረሳ የወደፊቱን እንድናስብበት ያስፈልጋል …..
በክፍል 2 ይቀጥላ
Filed in: Amharic