ቁ
ከ547 የፓርላማ መቀመጫ ኦህዴድ ያለው 179 መቀመጫ ነው፡፡179/547×100=32.7 በመሆኑም ኦሆዴድ ከፓርላማ መቀመጫ ያለው ፐርሰንት 33.7 ነው፡፡ቀሪው 67.3 የሌሎች ነው፡፡ለምሳሌ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የሚፀድቀው በ2/3ኛ ድምፅ ነው፡፡ይህ ማለት 66.7% ድምፅ ካገኘ አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ይፀድቃል ማለት ነው፡ኦህዴድ ሙሉ በሙሉ የተቃውሞ ድምፅ ቢሰጥ ሌላው የምክር ቤት አባል ሙሉ በሙሉ ድጋፋን ከሰጠ 67.3%(2/3 ድምፅ በላይ ነው) ስለሚሆንopdo ይሸነፋል ማለት ነው፡፡በመሆኑም opdo ብቻዋን እንድታሸንፍ የፓርላማ መቀመጫ ቁጥሩ መጨመር አለበት ወይንም ከሌሎች እህት ድርጅቶች አጋርነት ማግኘት አለባት፡፡ጠዋት የጠፋችው አህያ ቁጥር አንድ በሉልኝ፡፡
180የኢህአዴግ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ ድምፅ ይሰጣል፡፡45ከopdo,45 ከህወሓት,45ከአማራ,45 ከደቡብ፡፡ሌላ አጋር ድምፅ ካላገኘች በስተቀር ኦህዴድ በዝረራ መሸነፍ ብቻ ሳይሆን ላትገኝ ጠልዘው ከሀገር ሊያስወጧት ይችላሉ(ይታያችሁ በፓርላማ ከፍተኛ የመቀመጫ ቁጥር ያለው opdo በፓሪላማ እጅግ ዝቅተኛ ቁጥር ካላቸው ክልሎች እኩል በ45 ድሞፅ ይወከላል፡፡ለኔ ይኸ ስድብ ይመስለኛል)::ጠዋት የጠፋችው አህያ ቁጥር ሁለት በሉልኝ፡፡የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ 36 ሰዎች ናቸው፡(፡9መከረኛው ኦህዴድ፤9ብአዴድ፥9ደህዴን፡9ህወሓት)በድምፅ በሚወሰን የስራ አስፈፃሚ ውሳኔ አሁንም ኦህዴድ በዝረራ ይሸነፋል፡፡ተመልከቱ የነቲለማ ቅርቃር ውስጥ መግባትና በየመድረኩ መሸነፍ ሚስጥሩ ይህ ነው፡፡ለነለማ ግዜ ይሰጣቸው የምንለው ለዝህ ነው፡፡የዶ/ር አብይ ከፓርላማ ሽሽት ሚስጥሩ ይህ ነው፡፡የአስቸኳይ ግዜውን ውሳኔ ማስቀረት ያልተቻለበት ሚስጥሩ ይኸ ነው፡፡የነለማ ሽንፈት ሚስጥሩ ይህ ነው፡፡ጠዋት ያኔ ግምባሩ ሲመሰረት የተበላሸ ቀመር፡፡ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ በእኩል ድምፅ ከሌሎች ጋር የማስተሳሰር ቀመር፡፡ጠዋት የጠፋች አህያ ማታ ማግኘት ችግር ነው ያልኩት ሰምና ወርቁ ይኸው ነው፡፡እነአባዱላ ያኔ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን አብይና ለማ እንዴት አድርገው ያውርዱት፡፡በመሆኑም ቲም ለማ ያለው አማራጭ አንድና አንድ ነው፡፡ቄሮ መሆን፡፡አዎ ቄሮ መሆን፡፡እሰልሰዋለሁ ቄሮ መሆን፡፡ከህዝባቸው ጋር፡መከራ መቀበል፡፡ለዝህ ህዝብ መድማት፡፡ካስፈለገም መሞት፡፡ለዝህ ህዝብ እስከሞት መታመን፡፡አራት ነጥብ!!!
ሀሬ ጋናማ በዴ ገልገላ ኩሪን ህንዴብስቱ" ትርጉም ''ጠዋት የጠፋች አህያ ማታ ላይ ፈልጎ ማግኘት ይከብዳል'' (አበባየሁ ደሜ)
Filed in: Amharic