>

የፋሽስት ወያኔን የግድያ አዋጅ  ያጸደቁት 346ቱ ነገ በታሪክና በትውልድ ፊት ለፍርድ  የሚቀርቡ ወንጀለኞች ናቸው!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የፋሽስት ወያኔን የግድያ አዋጅ የተቃወሙት 88ቱ ተወካዮች  ባርነትን እምቢኝ ያሉ የአድዋ መንፈስ የወለዳቸው እውነተኛ ጀግኖች ናቸው!
ከዛሬ 122 ዓመታት በፊት  ጀግኖች የኢትዮጵያ አርበኞች እስካፍንጫው የታጠቀውን የጥሊያንን  ጦር  በትክሻቸው፣ ባህያና  በበቅሎ የተያዘ በሶ፣ቆሎና ጥሬ እየበሉ፤ በወጣ ገባው አስቸጋሪ የአገራችን  መልክዓ ምድር እየተንገላቱ፤ ባህር አቋርጦ ከመጣው  የማይመጣጠን ጦር ጋር  በመግጠም  ክቡር መስዕዋትነት ከፍለው ፤ በደምና በመከራ የዋጀች፤ በቅኝ በተያዘው የአፍሪካ  አህጉር መካከል  የምትገኝ ብቸኛ የነፃነት ደሴት አቆይተውናል።
ከ122 ዓመታት በኋላ ፋሽስት ወያኔ በኢትዮጵያውያን ሞት፣ መከራና ፍዳ ላይ ቅጥ ያጣውን የትግራይ የበላይነት ለማደላደል ያወጣውን የግድያ፣ የዘረፋና የባርነት አዋጅ የፋሽስቱን አገዛዛ  ኮማንድ ፖስት ማስፈራሪያ፣ዛቻና መከራ ተቋቁመው፤ ልክ እንደ  አድዋ ጀግኖች አቅማቸው  ውስን ቢሆንም በቆራጥነት ግን የማይመጣጠን ኃይል ከታጠቀው  ከፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ  ጋር ከቆሙት  የላቀ  ቁጥር ካላቸው 346 ሕሊና ቢስ ባንዶች ጋር በመጋፈጥ እንደ ፊታውራሪ ገበየሁ ጉሩሙና ፊታውራሪ ተገኘ ወርቄ  ሁሉ ለሕዝብና ለአገር መስዕዋት ከፋይ  መሆናቸውን በታሪካዊቷ የአድዋ እለት አስመስክረዋል።
የአድዋ እለት በነጻነት ለመኖር የተከፈለ መስዕዋትነት መታሰቢያ ነው። 88ቱ የፓርላማ አባላት  በነጻነት ለመኖር ድል በተቀዳጀንበት የአድዋ  ድል መታሰቢያ ቀን  የፋሽስት ወያኔን የባርነት አዋጅ በመቃወም ከእልቆ ቢስ ባንዶች ጋር  ተጋፍጠው እየነደዱ የነጻነት ብርሃን ለመሆን ተጋድለዋል። ለነዚህ ጀግኖች  የላቀ ክብር ይገባቸዋል!
እናንተ ዛሬ  ከሕዝብ ቆን በመቆማችሁ በፋሽስቶ ዘንድ ወንጀለኛ ተደርጋችሁት   88ቱ የፓርላማ አባላት ነገ ታሪክ  ጀግና አድርጎ የሚያወሳው እናንተን ነው። አድዋ በተከበረ ቁጥር የናተንም ጀብዱ አብሮ  ለዘላለም ሲወሳ ይኖራል። እጅግ ከፍ ያለ ክብር ይገባችሁኋል።
ህግ አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!!!
በኢፌድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 93 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከምክር ቤቱ አባላት በሁለት ሶስተኛው መደገፍ ይኖርበታል።  ይህም ማለት ከ547 ውስጥ 364 የድጋፍ ድምጽ ማግኘት አለበት። ዛሬ የቀረበው የእስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያገኘው የድጋፍ ድምጽ 346 ብቻ በመሆኑ እዋጅ አልጸደቀም።
የዚህ ውጤት ደግሞ ካዛሬ የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ አዋጁ የተሻረ በመሆኑ ከዚህ ቀን እና ሰዓት ጀምሮ የትኛውም የመከላከያ ሰራዊት አዛዥም ሆነ አባል ማንኛውንም ሰው መያዝ ማሰር መደብደብ ጥያቄ መጠየቅ መግደል አይችልም። በአጭሩ የመከላካያ ሰራዊቱ በአዋጁ የተሰጠው ስልጣን በአሁኑ ሰዓት የለውም ማለት ነው።
ከዚህ በተጨምሪም የየክልል የፖሊስ አባላት ተጠሪነታቸው ለመደበኛው አዛዥ ብቻ ነው።
ከዚህ ውጭ ከመከላከያው ትእዛዝ መቀበልም ሆነ መፈጸም በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል።
ከዚህ ቀን በኋላ ማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አባል ሰውን ቢያስር ቢገድል ወይም ቢደበድብ ታዝዤ ነው ማለት ወይም ፋና ብሮድ ካስቲንግ ወይም የተወካዮዥ ምክር ቤት ወይም አፈጉባኤ አባዱላ ወይም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ አሳስቶኝ ነው የሚል ምክንያት ከተጠያቂነት አያስጥልም።
ይህንን መልእክት  ለሰራዊቱ አባላት እንዲያውቁት ማድረግ ያስፈልጋል።
ይህንን ጉዳይም ለማ መገርሳ እና ገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ በመስጠት የክልላቸውን የጸጥታ አካላት ህግ እንዳይጥሱ ተጠሪነታቸውም ለክልሉ መንግስት ብቻ መሆኑን አሁኑኑ ማወጅ ይኖርባቸዋል።
የፋሽስት ወያኔን የግድያ አዋጅ  ያጸደቁት 346ቱ ሆዳም ባንዶች  ግን  መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በሰራው ወንጀል እንደተከሰሱቱ 106ቱ  የደርግ አባላት ሁሉ  ነገ በታሪክና በትውልድ ፊት ተዋድረው ለፍርድ  የሚቀርቡ ወንጀለኞች ናቸው።
Filed in: Amharic