>

እየፈራረሰ ያለውን የህወሃት የበላይነት በአስቸኳይ አዋጅ ስም ለማስቀጠል የተጀመረውን ዘመቻ ለመቆራረጥ ወቅታዊና ወሳኝ ጥሪ ቀርቧል!!!

ጃዋር መሃመድ
እንደሚታወቀው ለመውደቅ እየተንገዳገደ ያለው የህወሃት አገዛዝ በህዝቦች ላይ የጫነውን የጭቆናና የጭፍጨፋ ቀንበር ለማራዘም በሚያደርገው መፍጨርጨር ለሁለተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ሞክሮ በትናንትናው እለት ራሱ በሚቆጣጠረው ፓርላማ አባላት ውድቅ ሆኖበታል። ሆኖም ግን አገዛዙ ህገ መንግስቱን ለመጠበቅ ታስቦ ነው የወጣው የተባለውን ግን ደሞ ህገ መንግስቱን ራሱን በሚጥስ መልኩ ሁለት ሶስተኛ የህዝብ ተወካዮች ምቤት አባለት ድምጽ ሳያገኝ ጸደቀ የተባለውን አዋጃ ስራ ላይ ለማዋል እየፍጨረጨረ መሆኑን እየታዘብን ነው። የወያኔ አገዛዝ ይሄንን ኢ-ህገመንግስታዊ (unconstitutional) የሆነ አዋጅ ውድቅ መሆኑን ለህዝብ እንዲያሳውቅ ቢጠየቅም እስካሁን ጆሮ ዳባ ብሎ ጭራሽ ወዳ አፈጻጸም ለመግባት እየሞከረ ነው።  ይሄ አዋጅ ኢ-ህገመንግስታዊ ስለሆነ አንቀበለውም ባለው ህዝባችን ላይ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ጦርነት ከፍቶ ጭፍጨፋ እያካሄደ ነው። ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነውን ይሄን አዋጅም ሁሉንም የፌዴራል ስርዓቱ አባላት የሆኑትን የክልል መንግስታት መዋቅር አፍርሶ ህዝብ ላይ በጉልበት ለመጫን እየሰራ ነው።
አገዛዙ ይሄን አደገኛ አካሄዱን ትቶ እስከ ነገ ማታ ማለትም እሁድ የካቲት 25, 2010 ድረስ ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነው ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውድቅ መሆኑንና ኮማንድ ፖስት የሚባለውም መፍረሱን በሚዲያ ለህዝብ መግለጽ አለበት። ይሄ ካልሆነ ግን ራሱን ከእልቂት ሃገርንም ከመበተን ለመከላከል ህዝብ ያለው አማራጭ ትግሉን በመቀጠል ይሄን የጭፍጨፋ እቅድ በትግሉ ውድቅ ማድረግ ነው። በዚሁ መሰረት ተከታታይነት ያላውቸውና በስትራቴጂ የተቃኙ የትግል ስልቶች የተነደፉ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር የግብይት ተዓቅቦና የስራ ማቆም አድማ ይሆናል። ይህም በመላ ሃገሪቱ ከሰኞ መጋቢት 26 እስከ ረቡዕ መጋቢት 28, 2010 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
ስለሆነም፥
1) በነዚህ ቀናት ግብይት አይኖርም፣ ሁሉም የንግድ ተቋማት ዝግ ይሆናሉ። የመንግስት ሰራተኞችም ስራ አይገቡም የትራንሶፕርት አገልግሎቶችም አይኖሩም።
2) ሃገሪቱ የገቢና ወጪ ንግድ እቃዎች የምታጓግዝባቸው ዋና ዋና መንገዶች ጨምሮ ሁሉም የንግድ መስመሮች ይዘጋሉ።
ስለዚህ በመጪዎቹ ሁለት ቀናት ህዝባችን አስፈለጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ከወዲሁ ጥሪ እናስተላልፋለን። ተቃውሞው በሚቆይባቸው ሶስቱ ቀናት ከዚህ በፊትም እንደተለመደው የመደበኛም ሆነ የድንገተኛ ህክምና ግልጋሎቶችን የሚሰጡ የጤና ተቋማት ስራዎቻቸውን አያቋርጡም።
በተጨማሪም፥
1) ህዝባዊው ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ ይሆናል። ሆኖም ግን አገዛዙ የጉልበት እርምጃዎችን ወደ መውሰድ የሚሄድ ከሆነ ጠንካራ የአጸፋ እርምጃዎች የሚወሰዱበት ይሆናል። በዚ ላይ ትግሉን መሬት ላይ የሚያስተባብሩት በሂደት የሚያሳውቁት ነገር ይኖራል።
2) የክልል ፖሊሶች እንደተለመደው የህዝቡን ሰላምና ጸጥታ እንደሚጠብቁ ተስፋ እናደርጋለን። ህዝቡ ጎን ተሰልፎ ህዝቡን እንዲከላከሉም ጥሪ እናስተላልፋለን።
3) ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የየክሉን መንግስታት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ከጫወታ ውጪ ያደረገ ነው። ስለሆነም የየክሉ መንግስታት የተጠራውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማደናቀፍ ወይም ሌላ ማናቸውም ዓይነት ትዕዛዝ ለማስተላለፍ መብትም ሆነ ግዴታ የላቸውም። በዚሁ መሰረት ካቢኔም ሆነ በየትኛውም ያስተዳደር መዋቅር ያለ አመራር ወይም ሰራተኛ ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ተባብሮ ህዝባዊውን ተቃውሞ ለማደናቀፍ መስራት አይችልም። ይሄን ማድረግ የህዝብ ክህደት ስለሆነ ይሄን በሚያደርጉት ላይ ህዝቡ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል። በተጨማሪም ህዝባዊውን ተቃውሞ የሚያጨናግፉ ማናቸውም አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል። እርምጃም ይወሰድባቸዋል።
4) አጋዚ ይሄን ኢ-ህገመንግስታዊ አዋጅ ህዝብ ላይ ለመጫን በሚል የጉልበት እርምጃ በሚወስድባቸው ቦታዎች ሁሉ ህዝብ ራሱን ለመከላከል ባለው ተፈጥሮኣዊ መብት በመጠቀም በራሱ መንገድ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አጥብቀን በድጋሚ ማሳሰብ እንወዳለን።
ድል ለህዝባችን!
Filed in: Amharic